Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም አቀፍ የብስክሌት ቀን World Bicycle Day ============== ዓለም አቀፍ የብስ | Commercial Bank of Ethiopia - Official

ዓለም አቀፍ የብስክሌት ቀን
World Bicycle Day
==============
ዓለም አቀፍ የብስክሌት ቀን በየዓመቱ ግንቦት 26 ቀን (ጁን 3) በመላው ዓለም በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡

ብስክሌት ቀላል፣ በአንጻራዊነት አነስተኛ ወጪ ያለው፣ ንጹህ እና ላካባቢ ጥበቃ ተስማሚ እንዲሁም ጤናን ጨምሮ ሌሎች ጥቅሞች ያሉት አማራጭ የትራንስፖርት ዘዴ መሆኑን ከግንዛቤ ወስጥ ያስገባው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እ.ኤ.አ ከ2018 ጀምሮ ጁን 3 ዓለም አቀፍ የብስክሌት ቀን ሆኖ እንዲከበር ወሰነ፡፡

ብስክሌትን ለትራንስፖርት መጠቀም አካላዊ እንቅስቃሴን ስለሚጨምር እንቅስቃሴ ካለማድረግ የሚመጡ የልብ ህመም፣ ግፊትና ስኳር የመሳሰሉ በሽታዎችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ብስክሌት የነዳጅ አጠቃቀምንም ስለሚቀንስ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ለአካባቢ ጥበቃ የጎላ ሚና ያለው ሲሆን፣ እንዲሁ የመተንፈሻ አካላት በሽታን ለመከላክል ያስችላል፡፡

ሀገራችንን ጨምሮ በርካታ የዓለም ሀገራት ዜጎች ብስክሌትን ተመራጭ የትራንስፖርት ዘዴ አድርገው እንዲጠቀሙ መንገዶችን ከማስተካከል ጀምሮ ሌሎች ማበረታቻዎችን እየተገበሩ ነው፡፡