Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀ። = | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀ።
=========================================

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ2014/15 ዓ.ም የምርት ዘመን ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አስታውቀዋል።

በጦርነትና ተያያዥ ምክንያቶች ዓለም ላይ የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጭማሪ ማሳየቱን የገልጹት አቶ አቤ፣ በአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት ምክንያት በግብርናው ዘርፍ የተያዘው አገራዊ እቅድ እንዳይስተጓጎል ለሌሎች ዘርፎች ሊውል የነበረ ገንዘብ ጭምር ወደ ግብርናው በማዞር ከፍተኛ ገንዘብ ለማዳበሪያ ግዢ ወጪ መደረጉን ተናግረዋል።

ባንኩ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ ከሚያደርግባቸው ዘርፎች አንዱ ግብርና መሆኑን የጠቀሱት አቶ አቤ፣ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ትልቅ ድርሻ እንደሚይዝ አስረድተዋል።