Get Mystery Box with random crypto!

ደንጌሳ ጎመን (የሰማሪዎ ጎመን ቢሆን ይመረጣል) ጎመኑን ቀንጥሶ አጥቦ መቀቀል ሲበስል በደ | Coffee meets ፍርፍር - Food Blog

ደንጌሳ
ጎመን (የሰማሪዎ ጎመን ቢሆን ይመረጣል)
ጎመኑን ቀንጥሶ አጥቦ መቀቀል
ሲበስል በደንብ ማንጠፍጠፍ
እስኪበርድ ጠብቆ እጅን በደንብ ከታጠብን በኋላ በእጃችን ልክ እያደረግን መጭመቅ
ካለን በመፍጫ ከሌለን በ እጃችን ድቅቅ አድርጎ መክተፍ
ዘይት አግለን በጣም የደቀቀ ሽንኩርት መጨመር (እንደፍላጎት) የተፈጨ ሀብሽ ጨምሮ በደንብ ማቁላላት
የደቀቀውን ጎመን ጨምረን በደንብ ማሸት
በመቀጠል ጨው ሚጥሚጣ ኮረሪማ እና የቀለጠ ቅቤ (ብዙ ቅቤ ይፈልጋል) ጨምሮ ሁሉም በደንብ እስኪዋሀድ ድረስ በደንብ ማሸት ይፈልጋል
እሳት ላይ ትንሽ አቆይቶ ማውረድ
ለአይቤው
ቀደም ብለን የአይቤው ውሀ ጠፍጠፍ እንዲል በፌስታል አይቤውን አድርገን ፌስታሉን በሹካ በሳስተን ማንጠፍጠፊያ ላይ አድርጎ ማስቀመጥ
ጠፈፍ ካለልን በኋላ ወደ መቀላቂያ እቃችን ገልብጠን የተቋጠረ አይብ ካለ በሹካ መበታተን በመቀጠል የቀለጠ ቅቤ ሚጥሚጣ ኮረሪማ ትንሽ ጨው እና ካሼ(ያልበሰለ ጎመን ምጣድ ላይ አድርቆ በእጅ ማድቀቅ) እነዚን ግብአቶች ጨምሮ ማዋሀድ
በመጨረሻም ጣባ ላይ ትንሽ ቅቤ አድርጎ በ አንዱ ጎን ጎመኑን በአንዱ ጎን ደግሞ አይቡን አድርጎ ከላይ የቀለጠ ቅቤ ፈሰስ በማድረግ አንቀፎ(መመገቢያ) ከጎን በማድረግ ለመብል ማቅረብ


#Tsi

@coffeemeetsfirfir