Get Mystery Box with random crypto!

CHRISTIAN MINDSET

የቴሌግራም ቻናል አርማ christian_mindset_eth — CHRISTIAN MINDSET C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christian_mindset_eth — CHRISTIAN MINDSET
የሰርጥ አድራሻ: @christian_mindset_eth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 630
የሰርጥ መግለጫ

✞Destiny:- መንግስተ ሰማይ
☞ባለንበት የዘመን መጨረሻ እንጥፍጣፊ ሰዓት
በጥብቅ ከሚፈለገው ሀይል የመጀመሪያው የሆነው የወጣቱን ሀይል ካየበት ግብ የሚያሰናክሉትን ነገሮች በመለየት በመፍትሔው ላይ የተለያዩ መወያያ መድረኮች እና መንፈሳዊ ሰዎች በጉዳዩ ላይ የሠጡትን ምክር የምንዳስስበት እና የምንፈትሽበት መንፈሳዊ Channel ነው፡፡ ✔CHRISTIAN MINDSET ETHIOPIA

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-10-07 20:08:55 #worship_zone #ዘማሪ_ትግስት_ኮራብዛ #ያላንተ #ተመስገን_አበራ #ቤቲ_ተዘራ #ምህረት_ኢተፋ #live_worship |MARANATHA DIGITAL NETWORK|
@maranatha_fellowship
@maranatha_fellowship2
https://www.instagram.com/maranatha_fellowship/
https://www.facebook.com/MARANATHAFELLOSHIPETHIOPIA፧
https://www.tiktok.com/@maranatha_fellowship


400 views፪°, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-28 12:30:12
" እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል።"
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:3)

" እንቢ ለኢየሱስ "

ልዪ የስነ ፅሁፍ ምሽት በሀዋሳ ገነት ቤተክርስቲያን በያህዌ ንሲ ድራማ እና ስነ-ፅሁፍ ህብረት የተዘጋጀ ቅዳሜ መስከረም 22 ከ 11 ሰዓት ጀምሮ

በ እለቱ የሚኖሩ ፕሮግራሞች
ድራማ
ግጥም
ኬሮግራፊ እና ሌሎች የተለያዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል MARANATHA DIGITAL NETWORK|
@maranatha_fellowship
@maranatha_fellowship2
https://www.instagram.com/maranatha_fellowship/
https://www.facebook.com/MARANATHAFELLOSHIPETHIOPIA፧
https://www.tiktok.com/@maranatha_fellowship


447 views፪°, 09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-09 21:10:50
ልጆቼ፣ “የተኛነው ዳይፐር ሳናደርግ ነው፡፡ ሽንታችንንም አልጋ ላይ አልሸናንም” እያሉ በየማለዳው “በራሳቸው ድል” ይጨፍራሉ፡፡

በመሠረቱ፣ ማታ ማታ ዳይፐር እንዲያቆሙ ያበረታታኋቸው እኔ ነኝ፡፡ ሌሊት ሽንታቸው እንዳያመልጣቸው ከድርብርብ አልጋቸው ተሸክሜ እያወረድኩ ፖፖ ላይ የማስቀምጣቸውም እኔ ነኝ፡፡ እንቅልፍ አሸንፎኝ ሳላሸናቸው እንዳልቀር በመሥጋት፣ ማታ ውሃ በደንብ ጠጥቼ ነው የምተኛው - ሽንቴ እንዲቀሰቅሰኝ፡፡ ለሽነቴ ስነሣ በዚያው እነርሱንም አሸናቸዋለሁ፡፡ እነርሱ ግን በዕንቅልፍ ዓለም ተወስደዋልና ስለሚካሄደው ነገር ምንም አያስታውሱም፡፡ ስለዚህም ጠዋት ሲነቁ “በገዛ ድላቸው” ይፎክራሉ፡፡

ያኔ ሁኔታቸውን እያየሁ በውስጤ ፈገግ እላለሁ፡፡

ምክንያቱም በሕይወቴ እንደ ገዛ ድሌ እየቆጠርኩ የምፎክርባቸው ብዙ ነገሮችም እንደዚሁ ናቸውና ነው፡፡ እያወቅሁም ሆነ ሳላውቅ እግዚአብሔር እየደገፈኝ የተሻገርኳቸውን ዘመናት፣ የዘለልኳቸውን መሰናክሎች፣ የደረስኩባቸውን ከፍታዎች ሳስብ የራሴ ብርታትና ጥሩነት ነው የሚታየኝ፡፡ ለመሆኑ በእነዚህ ሁሉ ዘመናት የደገፈኝ፣ የተሸከመኝ፣ ያሻገረኝና ያሳለፈኝ እርሱ አይደለምን!? ከእኔ የሆነ ምን አለ? በራሴ የሆንኩት፣ በራሴ የደረስኩበት አንዳች ነገር በሕይወቴ ኖሮስ ያውቃልን? ለሞት፣ ለስንፍና፣ ለከንቱነት ከተኛሁበት የነቃሁት እርሱ ደግፎኝ ብቻ ነው፡፡ ያልጠፋሁትም ምሕረቱ ስላላቀብኝ ነው፡፡ ታዲያ በየማለዳው “ዳይፐር አላደረግሁም፤ አልጋ ላይ አልሸናሁም” እያልኩ “በገዛ ድሌ” ስፎክርና ለራሴ ሳጨበጭብ ምን ይለኝ ይሆን?
ጌታ ሆይ አድነኝ!

አመቱን በምህረቱ ያስጨረሰን አምላክ ይባረክ።

(ጳውሎስ ፈቃዱ)

CHRISTIAN MINDSET ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
700 views፩°, edited  18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-09 08:04:45
ይህ ህፃን 26 አመቱ ነው!
.******
ከተወለደ ጀምሮ እድሜው ሲቆጠር 26 ነው ግን እድገቱ እና ያለበት ሁኔታ የ 1 አመት ህፃን ልጅ ያለበትን ሁኔታ እና ድርጊት ያደርጋል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ብዙ ጊዜ ለምን ብዬ ጠይቄ መልስ ባላገኝም ከታሪኩ ግን ብዙ ነገር ተምሬአለሁኝ። እናት እና አባቱ እንደዚህም ታናሽ ወንድሙ የሚያወሩትን ስሙ ብዙ ትማራላችሁ። በተለይ ወላጅ እናቱ ለ 26 አመት የከፈለችው ዋጋ ይገርማል።

CHRISTIAN MINDSET ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
413 views፩°, edited  05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-07 20:20:25
ለሀገሬ በፀሎት እዘምታለው #CHALLENGE #pp #SHARE ለ10 ሰው

የክተት ጥሪ ለኢትዮጵያውያ

ሀገሬ በመከራ በጭንቅትና በነውጥ ላይ ትገኛለች ሀገሬን ለማዳን እኔ እዘምታለሁ እንደ ኢትዮጵያዊም እንደ ክርስቲያን ከሀገሬ ጎን የመቆም ሞራላዊም መጽሐፍ-ቅዱሳዊ ግዴታ አለብኝ፡፡ ሀገሬ በአሁኑ ሰዓት በጦርነት ተወጥራ ብዙሃኑ እያነቡ እየተፈናቀሉ እየሞቱ ይገኛሉ በዚህ ለሀገሬ ፈታኝና አስቸጋሪ በሆነ ወቅት ለሀገሬ እንዳለሁላት ከጎኗ ስለመቆሜ የማሳየው በመዝመት ነው ይህም ዘመቻ በጦርነት ግንባር አፈ-ሙዝ በመማዘዝ ሳይሆን እንደ ክርሰቲያን በመጸለይ ነው በመጽሐፍ-ቅዱሳችን በትንቢተ ዳንኤል መጽሐፍ በምዕራፍ 9 ላይ እንደምናነበው ነብዩ ዳንኤል ስለሀገሩ ስለምድሩ ሲጸልይ እናነባለን ለሀገራችን መጸለይ ግዴታችን ነው፡፡ ክርስቲያን ነንና በመንፈስ እንመራልን ቃሉም እንደሚለው ''መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል'' ይላልና በሀገሬ አየሆነ ስላለው ነገር በመንፈሳዊ አይን ልንመረምር ይገባል፡፡ ሀገሬን እየወጋ ያለው ጠላት ከመንፈሳዊው ከጠላት የመጣ ፍላፃ ነው ፍላጻን ለመቃወም ቃሉ እንደሚለው ‹የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ›ኤፌ.6፡11 ልንለብስ ያሻል፡፡ ደግሞም በእግዚአብሄር ፊት እንደ ነብዩ ዳንኤል ስለ ምድራችን ማንባት አለብን ስለሚፈሰው ደም እግዚአብሔር ምሕረት እንዲያደርግልን ጦርነት ነውና ከሁለቱም ወገን ደም ይፈሳል ደም ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት ይጮሃል፡፡ ስለሆነም እየሆነ ስላለው ሁሉ ንስሃ እየገባን መጸለይ አለብን፡፡
''አቤቱ፥ ስማ፤ አቤቱ፥ ይቅር በል፤ አቤቱ፥ አድምጥና አድርግ፤ አምላኬ ሆይ፥ ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና ስለ ራስህ አትዘግይ።''
ዳን.9፡19
.|MARANATHA|.
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
366 views፩°, 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-23 21:50:06
ስለ ሀገራችን እንጸልይ
በመከራችን ረድኤትን ስጠን
—መዝ.60፡11
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የሀገሬ ልጆች!!
ቤተክርስቲያን(የቅዱሳን አንድነት) ለሀገር ፍቅር ያላቸውን ስሜት የሚገልጡት ስለ ሀገራቸው በመጸለይ ነው፡፡ ለሀገር መጸለይ እንደ ክርስቲያን ግዴታ ቢሆንም የሀገር ወዳድነት ነው፡፡ ለሀገራችን መፍትሄው ጸሎት ሆኖ ሳለ ከቤተክርስቲያን የሚሰማው ግን ይህ አይደለም፤ የዓለም መፍትሄ የሆነውን በለው ደምስሰው ማለት ከተጀመረ ሰነባብቷል ይህ አይነቱ ምድራዊ መፍትሄ እንጂ ሰማያዊ አይደለም፡፡ ከሰማይ የሆነው መፍትሄ ሚገኘው በጸሎት ብቻ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳችን እንደምናነበው ነብዩ ዳንኤል በትንቢተ ዳንኤል ም.9 ላይ ስለ አባቶች ኃጢአት ንስሃ እየገባ ስለ ምድሩ ሲጸልይ እናገኛለን፡፡ ማነኛችንም አይመለከተንም ማለት አንችልም በምድራችን እየሆነ ስላለው ነገር መጸለይ ግድ ይለናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን የተለያዩ ውጥንቅጦችን እያስተናገደች ትገኛለች በአንድ በኩል በሀገር ውስጥ ጦርነት በጦርነትም መፈናቀል፣ ረሃብ፣ ጾታዊ ጥቃት፣ የሴቶችና ህፃናት ሞት፣ የምጣኔ-ሀብት(Economy) ድቀት፣ የማህበራዊ መስተጋበር መቃወስ፤ በሌላ በኩል የኃያላኑ ሀገራት ጫና በጫናው ማዕቀብና የግንኙነት መሻከር ይህን ሁሉ በሀገራችን ላይ ያለ ሸክም ነው፡፡ ይህን የኢትዮጵያን ሸክም እንደ ክርስቲያን ልንሸከመውና በእግዚአብሔር ፊት እንጮኽ ዘንድ ይገባናል፡፡ ለሀገራችን መድኃኒት፣ ፈውስና ረድኤት ሊመጣ የሚችለው ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ነው፤ ስለሆነም ለሀገራችን አጥብቀን ልንጸልይና ልንቃትት ይገባል፡፡
እግዚአብሔር ለምድራችን ረድኤትን ይስጠን!
.|MARANATHA|.
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship
#Share
420 views፩°, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-20 06:55:32 ለካ እሞታለው....


ለካ እሞታለሁ እሄዳለሁ እላይ
ፍርዴን ለመቀበል ከዳኛው ከበላይ
ለካ እሞታለሁ ፥ ድንኩዋን ተጥሎልኝ
በ ሜትር በ ልኬት ሳጥን ተገዝቶልኝ
ለካ እሞታለሁ! መሬት እገባለሁ
ወይ ሲኦል ገነትን ለካ አያታለሁ።
.....

ለካ እሞታለሁ ፥ ጥቁር ለብሠውልኝ
ሠው እያበሉ በ ዓመት ዘክረውኝ
ለካ እሞታለሁ ፥ጥያት ይችን ዓለም
እናት የለ አባት ፣ እህት የለ ወንድም፣
ሀገር የለ ወገን ፣ ልጅ የለ ሚስት
ያለ በዚህ ዓለም...
ሁሉን እተወዋለው ሄጄ ለዘላለም።
.....
ለካ...እሞታለሁ ያለኝን ነገር አይቼ
ወደ ሞት ስሄድ ባዶዬን ትቼ
ለካ እሞታለሁ!
የላይኛውን መንገድ ትኬት እቆርጣለሁ።
.....
መሞቴ ሆኖብኝ የማይፈታ ቅኔ
ፍቺው ጠፍቶብኝ አሁን ታዲያ እኔ
ሞትን እረሣሁት እያየሁት ባይኔ
.....
ምነው ታዲያ መሞቴን እረሳሁ
ሁሉን ትቼ እኔ ፥ እንደ አዳም ዘነጋሁ
ለካ ለካ ለካ... ለካ እሞታለሁ
ሁሉን ነገር ትቼ ካለም እርቃለሁ።

CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
423 views#KAL, 03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-16 22:08:38 Ante Bicha "አንተ ብቻ" - The only one. For great is the Lord & greatly to be praised - by Dawit Getachew
sʜᴀʀᴇ ◈JOIN◈ sʜᴀʀᴇ
▷◈@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSE ◈◁
── ❖ ── ✦ ── ❖ ──
424 views፩°, edited  19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-16 22:08:24
Ante Bicha "አንተ ብቻ" - The only one. For great is the Lord & greatly to be praised - by Dawit Getachew
sʜᴀʀᴇ ◈JOIN◈ sʜᴀʀᴇ
▷◈ ◈ @CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
── ❖ ── ✦ ── ❖ ──
372 views፩°, edited  19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-10 23:28:49
መንፈሳዊ ህይወት ከፊት ታላቅ ነፋስ እንደሚመታው የመርከበኛ ጉዞ ነው።

ወደፊት ለመዝለቅ ታላቅ ተጋድሎ ማድረግን ይጠይቃል

ወደኋላ ለሚመለሱት ግን ልክ እንደመዝናኛ ነው ሳያስቡት ራሳቸውን ከባህሩ ዳርቻ ያገኙታል

CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
@CHRISTIAN_MINDSET_ETH
530 views#KAL, 20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ