Get Mystery Box with random crypto!

( አሰላስሎ ) ለሚበዙ አመታት በታላቁ ተልዕኮ (Great commotion ) በተባለው ወንጌ | በክርስቶስ ( in christ)

( አሰላስሎ )


ለሚበዙ አመታት በታላቁ ተልዕኮ (Great commotion ) በተባለው ወንጌልን ግብ ባደረገ አገልግሎት ውስጥ በማስተባበር የሚታወቁት በቀለ ሻንቆ Never alone በሚል የህይወት
ጉዞአቸውን ዘግበው አሳትመዋል ። ከእሳቸው የማክሰኞ ምሳ የሚለውን
ሀሳብ ለዚህ ፅሁፍ መንደርደሪያ ተጠቅሚያለሁ ።
የማክሰኞ ምሳ !! የማክሰኞ ምሳ ጋሽ በቀለ ከተለያዩ በከተማው ያሉ
የቤተክርስቲያን መጋቢዎች እና አገልጋዬችን በመቅጠር በማክሰኞ ምሳ ላይ እንዴት ወንጌል ማድረስ እንዳለባቸው ይመክራሉ ዘዴ ያበጃሉ ። ይሔን ዘዴ ብዙ ፍሬ አፍርቷል ።

ይሔን የማክሰኞ ምሳ ወንጌል ለመስራት ዓላማ እና ግብ የሚቀመጥበት እንደሆነ እረዳለሁ ። የማክሰኞን ምሳ አይነት መሰባሰብ ለወንጌል ለማድረስ ዕቅድ ለማውጣት እና ለመነጋገር እንደዛ ያሉ ስልቶች ያስፋልጉናል ። በአውላላ መሬት ላይ ቁሞ ወንጌል እስራለን የሚል ፉከራ ብቻ የትም አያደርስም ።በፀሎት በታገዘ እና ዘመኑን ባማከለ መልኩ እንደ ማክሰኞ ምሳ ያሉ የማቀጃ መርሃ ግብር ግድ ይሉናል ።
የማክሰኞ ምሳ ብዙ ፍሬ እንዳፈራ እንገነዘባለን ። በተለይም ከዛ በኋላ የተሰራው ዘመቻ ፊሊጶስ የተባለው ዕቅድ ነው ። ዘመቻው ለ50 ቀናት በአዲስ አበባ ወንጌል መስራት ነበር ..በዚህ ግልፅ እቅድ ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ክርስቶስ እንደ ግል አዳኝ አርገው ተቀብለዋል ። ተራ ግብ ሳይሆን ያስቀመጡት ግልፅ መቼ ፣የት፣ምን የሚለውን የሚመልስ ትግበራ ነበር ።

ከሰሞኑን (leadership training ) ላይ ካስተዋልኩት ነገሮች መካከል ይሔ ነው ። ግልፅ የሆነ ወንጌል የምንሰራበት እና የምንናደርስበት እቅድ በቅዱሳን በተለይም ወጣቶች መሰባሰብ ያስፈልጋል ። የማክሰኞ ምሳ አይነት ፕሮግራም ወደ ወጣት እቅዶች መቅዳት (Adopt ) ማረግ ሳይኖርብን አይቀርም ።

ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd