Get Mystery Box with random crypto!

ቴዎድሮስ አብ (የትዝታው ወጣት)

የቴሌግራም ቻናል አርማ casting113 — ቴዎድሮስ አብ (የትዝታው ወጣት)
የቴሌግራም ቻናል አርማ casting113 — ቴዎድሮስ አብ (የትዝታው ወጣት)
የሰርጥ አድራሻ: @casting113
ምድቦች: ቪዲዮዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 251
የሰርጥ መግለጫ

ሠላም ወዳጆቼ የትዝታዉ ወጣት ነኝ
#ሙዚቃዎቼን
#ግጥሞቼን
# የተለያዩ ፅሁፎቼን በዚህ ቻናል ይከታተሉ
ለማንኛዉም አስተያየት @meryjan65
@casting113

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-16 23:26:26 አንድ ቀን ባአካል አይቼዉ የማላዉቀዉ ልጅ ምን እዳደረገኝ ተመልከቱ!!! - YouTube


165 views20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 03:21:56 ሠላም ወዳጆቼ
በልምምድ ወቅት.......

መልካሙ ተበጀ (ስትወደኝ ስወዳት)
149 views00:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-04-16 16:28:12 ሲበርደን ኡ ኡ ታ
ሲሞቀን ኡ ኡ ታ
ሲርበን ኡ ኡ ታ
ስንጠግብ ኡ ኡ ታ
ስንጠማ ጩኸት
ስንጠጣ ጩኸት
ስንፋቀር ጩኸት
ስንጣላ ጩኸት
በድለንም ለቅሶ
ሲበድሉን ለቅሶ
ግራ ግብት አለው
እግዜሩ ጨርሶ
643 views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-04-06 11:59:47 የመጠበቅ ቅኔ

የጽኑ ጎጆዬ ግድግዳው ፈራርሶ ፤
ባ'ጥ አሳቃይ ጠፍቶ ጣራው ተደርምሶ ፤
ጨረቃና ፀሐይ እንደ ጤዛ ሟምተው ፤
ሕፃን የነበሩት ከዋክብት አርጅተው ፤
የምድር አለቶች ......
ከመቆየት ብዛት ሆነው ደቃቅ አፈር ፤
ነፋስ አቅም አጥቶ ቆሞ ሲንፈራፈር ፤
የሊባኖስ ዝግባ ከስቶ ሳር አክሎ ፤
ውቅያኖስ በሚራዥ በውኃ ጥማት ከስሎ ፤
መላእክቶች ጃጅተው አክናፋቸው ዝሎ ፤
ይህን ሁሉ ችዬ...
ያንችን መምጣት ዘመን ስጠባበቅ እኔ ፤
እግዜር በመደመም ዓይኑን ጥሎ ካይኔ ፤
<<ፍቅር>> ብሎ ጻፈው....
ያለመታከትን የጥበቃን ቅኔ፡፡
596 viewsedited  08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-04-06 11:56:32 የቀረብሽኝ ጊዜ

የሞቴ ጥላ ሸሽቶ እንትንፋሴ ተመለሰ፣
የወደኩበት ዳገት ሜዳማ ሆኖ ታረሰ፣
የሚያዳልጠኝ ሁሉ ሆኖልኝ መደገፊያ፣
ሆንሽልኝ ውብ ድልድዬ ጥላቻዬን ማለፊያ!!
እናም ንግሰቴ ሆይ ነሽና የልቤ ወደብ፣
ካ'ለሽበት አልቀርም ቢያንገላተኝም ወጀብ!!

የጠላሁሽ 'ለት

ሐገር ሁሉ ይጥላኝ ይትፋኝ አሽቀንጥሮ፣
ሞት ቀድሞ ያግኘኝ በሕይወት ቀጠሮ፣
ምርኩዝ ያልኩት ሁሉ ይሁነኝ እንቅፋት፣
ስንገዳገድ እንድኖር ይብዛብኝ መገፋት።

"ለምን?" ያልሽኝ እንደኹ

እኔ አንችን ጠልቼ ወደ ሌላ ስሄድ፣
ቀድሞ ነው 'ሚጥለኝ ያቀናኹት መንገድ።

የኩለ ሌ'ት ጥሪ

በጽልመት ድንኳኔ ብርሐን ለኩሰሽ፣
ለማቅ ደበሎዬ ግማጃሽን አልብሰሽ፣
በደውልሽ ውግረት ነፍሴን አስነቅተሽ፣
በካሕንሽ መረግድ ጥሞናዬን ነስተሽ፣
''ተነስ!'' ብትይኝም መ'ተሽ በ'ኩለ ሌ'ት፣
ግና አላወኩሽም ቅድስት ትሆኝ ማኅሌት!!

የሆነ ዘመን ላይ...

አእዋፋት 'ረበው በደመና ጣሪያ፣
ፍስኃ ሲደመጥ በሠማያት ዙሪያ፣
የፍቅር ቄጤማ በም'ድር ሲነሰነስ፣
እርግቦች ሲንሩ በእባቦች ማነስ፣
አበቦች ለንቦች በሃሴት ሲያብቡ፣
ንድፊያውን የቻሉ ማሩን ሲመገቡ፣
ኩሬዎቹ ሰፍተው ሲሆኑ ውቅያኖስ፣
ለፀሐይ ስትታጭ የጎጆይቱ ፋኖስ፣
ግርምታ ፈጥሮብሽ እንዳትጨነቂ፣
ይህ በሆነ ጊዜ...
የትንሳኤሽ ዘመን መቅረቡን እወቂ።
574 viewsedited  08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-03-14 09:31:15 የህይወቴ ተስፋ ዛሬ ይኸው መክኗል
የድሮ ደስታዬ በሙሉ ጨልሟል
ከዛች ቀን በኋላ ማንባት ነው ስራዬ
ሀዘን በኔ ነግሶ በቤት በጓዳዬ
...
የድሮግዜዬን በትዝታ እያየው
በናፍቆትህ ብዛት እየተሰቃየው
ኑሮ በማይሉት ህይወት እኖራለው
....
ተስፋዬንአጥቼ ሞት እየናፈቀኝ
ያሳለፍኩት ሁሉ ህልም እየመሰለኝ
ደግሞም በትዝታ ስጓዝ ወደ ኋላ
በጎጇችን ውስጥ ስንጠጣ ስንበላ
ድቅን ይልብኛል የሚያምረው ፍቅራችን
እንደዛ ተዋደን አብረን መኖራችን
....
ግን....ማዘንብቻ ነው ከ ሀሳቤ ስነቃ
አጠገቤ የለህ ነፍሴ እንዲ ተጨንቃ
መቼም ላትመጣ ዘውትር ምትናፍቀኝ
በ ኦናው ቤቴ ውስጥ ባዶ ቅኔ የምቀኝ
.....
ግንእስከመቼ ነው እንደዚህ ምኖረው
ባልኖረው አካልህ አንተን የማልመው
እስከመች ድረስ ነው???
509 views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-02-16 13:19:26 ባገኝሽ ብዬ ነው አንቺን መጠበቄ
ልብሽ ጠፍሮ ይዞኝ ባንቺ መወሰኔ
ሌላ ላያሳየኝ በጨለማ ጋርዶ
ልቤ አንቺን ይላል በሰመመን ነጉዶ
ካሰኘው በሀሳብ ውቅያኖስ ወርውሮኝ
ዘልቆ ከጥልቀቱ ከአፈር ቀላቅሎኝ
መንጥቆ ይወጣል ከትዝታ ፈረስ
እኔም ከቅዘቴ ከሀሳቤ ስመለስ
ልብህ ያነገሳት ፈፅሞ ላታይክ
ለምንስ ማሰብህ ጭንቀትን ማብዛትክ
ብዬ አስባለው ግራ ቢገባኝ
ልቤን ለማስመለስ ድፍረት ቢያጥረኝ
ባይተዋር አረኩት ልቤን ገለልተኛ
ከሰውም አርቄ አረኩት ብቸኛ
ሰዎች ንገሩልኝ በሏት ታሞልሻል
ልቡን ወስደሽበት ለሞት ጫፍ ተቃርቧል
ግነትም አይደለም ሀቅ አለው በውስጡ
አይኖርም ተንፍሶ ልብን አንዴ ካጡ
653 views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-02-16 13:15:25 ማን ነኝ ልበላቸው ማን ብልስ ያምኑኛል
አንተ ማን ነው ያልከው ንገረኝ ጨንቆኛል
የአክስቴ ልጅ ናት ዘመድ ናት ባባቴ
ወይስ የልጅነት አብሮ አደግ ናት ጓዴ
ንገረኝ ማን አልከኝ ምንህስ አረከኝ
ዛሬ ደሞ ምን አልክ ማን ብለክ ሰየምከኝ
ለአንተ ባለኝ ፍቅር ባሪያክ አደረከኝ
ከትብያ ቆሻሻ በታች አሳነስከኝ
አጥቼ መስሎክ ነው ካንተ የበለጡ
ክብር ለሴት ማለት ጠንቅቀው የሚያውቁ
አንተን የመረጠክ ምክንያት ነው ልቤ
ፍቅርህን አገዘፍኩ ክብሬን ወዲያ ጥዬ
ለሰጠው ፍቅር ምላሽ ቢኖር መልስህ
አይቆጨኝም ነበር ምንም ብሆንልህ
ግና ላፈቀረ ልቤ ለሰጠህ ክብር
ረግጠህ ጥለ ሄድክ የወደዋላህን
አሁን ቢል ቤተሰብ አምጣልኝ እጮኛ
ያከበረው ወስዷል ከናቀው ክብረኛ
በማለት መልስ ስጥ እባክህ አደራ
647 views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ