Get Mystery Box with random crypto!

Campus life

የቴሌግራም ቻናል አርማ campus_life3 — Campus life C
የቴሌግራም ቻናል አርማ campus_life3 — Campus life
የሰርጥ አድራሻ: @campus_life3
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.60K
የሰርጥ መግለጫ

እኛ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ብለን እናምናለን!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-20 17:10:56
#AddisAbaba

ቦሌ አትላስ አካባቢ የደረሰው አደጋ 9:20 አካባቢ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ዛሬ ከሰዓት 8 ሰዓት አካባቢ ቦሌ አትላስ አካባቢ የሚገኙት የግንባታ ዕቃዎች መጋዘኖች ላይ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋው በቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስትያን እና በአትላስ እንዲሁም በፀጋ ሆስፒታል መሃል ላይ በሚገኙት የንግድ ሱቆች መጋዘኖች ላይ የደረሰው።

የአደጋው መነሻ እስካሁን አልታወቀም።

ቁጥራቸው 7 የሚደርስ የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን እሳት አደጋ መከላከል ተሸከርካሪዎች የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች አንዳይዛመት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

እሳቱ 9፡20 አካባቢ ማጥፋት ተችሏል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች እሳቱን ለማጥፋት ያደርጉት የነበረው ርብርብ የሚደነቅ እንደነበር ተገልጿል።

Credit : ETHIO FM 107.8
ቪድዮ : አቤል

@campus_life3
@campus_life3
2.8K viewsedited  14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-20 17:09:29 ኢራን የዘመናዊ የጦር መሳሪያ ግንባታ ጥበቤን ለጎረቤቶቼ እና ለወዳጆቼ ለማጋራት ተሰናድቻለሁ አለች፡፡

ፋርሳዊቱ አገር የታላላቅ ጦር መሳሪያዎች ጥበቧን ለወዳጆቿ እና ለጎረቤቶቿ ለማጋራት መሰናዳቷን የተናገሩት የወታደራዊ ትብብር ምክትል ኃላፊው ሐቢቦላህ ሳያሪ እንደሆኑ ስፑትኒክ ፅፏል፡፡

ኢራን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ እቀባዎች እና ክልከላዎች ውስጥ ብትሆን ወታደራዊ ኢንዱስትሪዋ ታላቅ እርምጃ እያሳየ መሆኑ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

የተለያዩ አገር በቀል ክሩዝ እና ባልስቲክ ሚሳየሎችን ሰርታ እያወጣች ነው፡፡ተደጋጋሚ ሙከራዎችንም ታደርጋለች፡፡

የኢራንን የታላላቅ ጦር መሳሪያዎች ግንባታ በሥጋት ዓይኖች የሚያዩት ምዕራባውያን ኃያላን በዓይነ ቁራኛ እየተከታተሏት መሆኑ ይነገራል፡፡በአሁኑ ወቅትም በኒኩሊየር ነክ ጉዳይ በኦስትሪያ ቬየና ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር እያደረጉ ነው፡፡

@campus_life3
@campus_life3
1.9K views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 16:54:26 ሩሲያ፣ ካናዳ እና ቤልጄም የጥምቀት በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!

በኢትዮጵያ የሚገኙ የሩሲያ፣ካናዳና እና ቤልጄም ኢምባሲዎች በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን የጥምቀት በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡በዓሉ የደስታና የፍቅር እንዲሆንም ኢምባሲዎቹ ተመኝተዋል፡፡
@campus_life3
@campus_life3
1.7K views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 09:54:21 ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች እንካን ለብረሀነ ጥምቀቱ አደረሰን አደረሳቹ።

ጥምቅትን በምታከብሩበት ቦታ ያለውን ድባብ ፎቶ
በዚህ @Ethio_send_bot ላኩልን
1.6K views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 09:41:55 እንኳን ለከተራ በዓለ አደረሳችሁ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የከተራ በዓልን እያከበሩ ይገኛሉ። ከተራ የጥምቀት ዋዜማ ላይ የሚከበር ሲሆን የእምነቱ ተከታዮች ከየአድባራቱ ታቦታትን በማጀብ ወደ ጥምቀተ ባህር እያመሩ ነው።
መልካም በዓል
@campus_life3
@campus_life3
1.5K views06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 18:13:48
#Update

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ የመማር ማስተማር ሥራውን እንዲጀምር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።

በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ውድመት በደረሰበት ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ላይ አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ እና መልሶ በማቋቋም የመማር ማስተማሩን ሥራ ለማስጀመር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አበበ ግርማ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ቡድኑ ወረራ በፈፀመበት ወቅት ማሽኖች፣ የመብራት፣ የውሃ እና ሌሎች የተቋሙ ንብረቶች ላይ ውድመት መፈጸሙን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲውን መልሶ ሥራ ለማስጀመር መንግስት እና አጋር አካላት ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

መንግስት ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሰጡ መመደቡንም ገልጸዋል።

ኢዜአ

@campus_life3
@campus_life3
1.6K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 16:51:50 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

ጥር 9/2014 (ዋልታ) ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ የሚሆን ከ9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ከፍተኛ የንብረት ውድመት ከደረሰባቸው የትምህርት ተቋማት አንደኛው ነው።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ አብርሃም ቦሻ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በማኅበራዊ ተቋማት በተለይም በትምህርት እና ጤና ተቋማት ላይ ያደረሰው ውድመት እጅግ አሳፋሪ ድርጊት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ውድመቱ የደረሰባቸውን ተቋማት መልሶ በማቋቋም ሁሉም አካል የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ነው የገለጹት፡፡
@campus_life3
@campus_life3
1.5K views13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 19:59:51 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 581 ተማሪዎች አስመርቋል።

258ቱ የ2014 ዓ.ም የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂዎች ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች በዕረፍት ቀናት መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 308 ተማሪዎችንም አስመርቋል።
@campus_life3
@campus_life3
1.5K views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-17 18:48:54 #ArbamichUniversity

በ2014 የትምህርት ዘመን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ #አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት የሚደረግበት ቀን #ኅዳር 12/2014 ዓ.ም ሲሆን ምዝገባ የሚካሄድበት ቀን #ኅዳር_13 እና 14/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

፨መደበኛ ትምህርት የሚጀመረው ኅዳር 15/2014 ዓ.ም በመሆኑ፡-

•አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ
•አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስና የስፖርት ትጥቅ
•ስምንት 3 x 4 የሆነ ጉርድ ፎቶ እና
•ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) ይዛችሁ
እንድትመጡ እያሳወቅን ከተጠቀሰው ቀናት ውጭ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እንገልጻለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
https://t.me/campus_life3
https://t.me/campus_life3
2.7K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-04 13:52:42 አዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ከአፍሪካ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ከአፍሪካ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠ።የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ዛሬ በሰጡት መግለጫ ዩኒቨርስቲው በርካታ ደረጃዎችን በማሻሻል ከአፍሪካ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ብለዋል።ታይምስ ሃየር ኤጁኬሽን የተባለው ዓለም አቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ደረጃ አውጪ ተቋም ትላንት ይፋ ባደረገው መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደረጃው መገለጹንም ጠቅሰዋል።

በተቋሙ ደረጃ አሰጣጥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ በዓለም አቀፍ ደረጃ 402ኛ ደረጃ ላይ ማስቀጠኑንም ፕሮፌሰር ጣሰው ገልጸዋል።

በመማር ማስተማር፣ ዩኒቨርስቲው የሚያስገባው ገቢና የጥናትና ምርምር ስራዎች ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለውድድሩ መስፈርት እንደነበሩ ተገልጿል። በዚህም ከ1 ሺ 600 በላይ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ተወዳድሮ በአፍሪካ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ብለዋል። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

"ዩኒቨርስቲው በዓለም አቀፍና በአህጉር ደረጃ ያሳየው መሻሻል በታሪኩ ትልቅ አፈጻጸም ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለውጤቱ መገኘት አስተማሪዎች፣ ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ሚና ጉልህ እንደሆነ አስታውሰዋል። የደረጃው መሻሻል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ያላትን ገጽታ ከማጉላት ባለፈ የበለጠ በመስራት ያነሳሳል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር እመቤት ሙሉጌታ በበኩላቸው ተቋሙ ደረጃውን የበለጠ ለማሻሻል በስትራቴጂ ተደግፎ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።በተለይም ጥናትና ምርምሮችን ማብዛት በስትራተጄው ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ቀዳሚው መሆኑን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የዩኒቨርስቲው አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ማቲዎስ ኢንሰርሙ እንዳሉትም ዩኒቨርስቲው ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በመሸጋገር ላይ መገኘቱ በዓለምና በአህጉር አቀፍ ደረጃ ራሱን ተወዳዳሪ ለማድረግ አወንታዊ አስተዋጽኦ አለው። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እኤአ 2020 በዩ ኤስ ኒውስ በተደረገ ዓለም አቀፍ ግምገማ በአፍሪካ 10ኛ ከዓለም ደግሞ 553ኛ ደረጃን ይዞ እንደነበር ይታወቃል።
@campus_life3
@campus_life3
3.7K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ