Get Mystery Box with random crypto!

46 በመቶ ምዕመናን ብቻ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን 'ታላቁ ተልዕኮ' እንደ ‘አደራ’ እንደሚ | CALVARY gospel ministry

46 በመቶ ምዕመናን ብቻ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን 'ታላቁ ተልዕኮ' እንደ ‘አደራ’ እንደሚያዩት አንድ ጥናት ገለጸ፡፡
በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28፡19 ላይ ‘“ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤” የሚለውን ጌታ ኢየሱስ የሰጠውን ታላቁን ተልዕኮ በተመለከተ በመጋቢዎችና በሌላው ምዕመን መካከል ሰፊ የአመለካከት ልዩነት እንዳለ ባርና የተባለ አጥኚ ተቋም ያወጣው አዲስ መረጃ አሳይቷል፡፡
በዚህ ጥናት ውጤት መሰረት ታላቁ ተልዕኮ ለሁሉም ክርስቲያን የተሰጠ አደራ መሆኑን 85 በመቶ መጋቢዎች ሲያምኑ ከምዕመናኑ ግን 46 በመቶዎቹ ብቻ ተልዕኮው የሁሉም አማኝ 'አደራ' እንደሆነ ያምናሉ ብሎዋል፡፡
ሚሽን ኢንዲያ ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር የተደረገው ይህ የባርና አዲስ ጥናት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠ 'ታላቁ ተልዕኮ” የማን ሃላፊነት ነው? እና በምን አይነት መልኩ ሊተገበር ይገባል? በሚለው ላይ የቤተክርስቲያን መጋቢዎችንና የሌላውን ምዕመን ግንዛቤ ለማወቅ የተደረገ ሲሆን በርካታ መጋቢዎችና ምዕመናን ተካተውበታል፡፡
የጥናቱ ትንታኔ እንደሚያሳየው በአገልጋዮችና በሌላው ምዕመን መካከል ያለው ይህ ሰፊ የአመለከከት ልዩነት ለምን እንደተከሰተ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሊፈትሹት ይገባል ብሏል፡፡
የቤተክርስቲያን መሪዎች ምዕመናኑ ይህንን ተልዕኮ በተገቢው ሁኔታ እንዲረዱትና ተሳትፏቸው በምን መልኩ ሊሆን እንደሚችል እንዲገነዘቡ ማስተማር እንዳለባቸው ጥናቱ ጠቁሟል፡፡