Get Mystery Box with random crypto!

የልጆችዎን ትምህርት ቤት ክፍያ በጊዜ ለመፈጸም ተቸግረው ነበር? ቡና ባንክ በዘመናዊ ዲጂታል አገ | Bunna Bank

የልጆችዎን ትምህርት ቤት ክፍያ በጊዜ ለመፈጸም ተቸግረው ነበር?

ቡና ባንክ በዘመናዊ ዲጂታል አገልግሎቶች በመታገዝ ለተማሪዎችና ለወላጆች እንዲሁም ለትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ክፍያዎችን ቀላል በማድረግ ላቅ ያለ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

በዚህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የየትምህርት ቤቱ የተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እና ክፍያ የብር መጠን ፣ የክፍያ ጊዜ ሲያልፍም የቅጣቱን መጠን ጨምሮ በቀላሉ በባንኩ ሲስተም ላይ በመጫን ለተማሪዎች ወይም ለወላጆች ወቅቱን ጠብቆ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት እንዲደርሳቸው በማድረግ ወላጆች ወይም ደንበኞች ክፍያቸውን በባንካችን መፈፀም እንዲችሉ አድርገናል።

በአሁኑ ወቅት ክፍያቸውን በቡና ባንክ ቅርንጫፎች መፈጸም የሚችሉ ትምህርት ቤቶች ቁጥር እየጨመረና አገልግሎቱም ለብዙሃኑ በቅልጥፍና እየተዳረሰ ይገኛል።

በቀጣይም ሌሎች በርካታ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ክፍያቸውን በቡና ባንክ ቅርንጫፎች ያደርጋሉ። ወላጆች በስልካቸው የክፍያ መጠን እና ጊዜ በወቅቱ ስለሚደርሳቸው ከቅጣትና አላስፈላጊ መጉላላት ይድናሉ፣ ጊዜያቸውንም ትምህርት ቤት ድረስ በመሄድ አያባክኑም።

ቡና ባንክ
የባለራዕዮች ባንክ!