Get Mystery Box with random crypto!

የኮንደምንየም እጣው ነገ ከሰዓት በኋላ ይወጣል በቅርቡ በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ምክንያት | ብሩህ ወቅታዊ ዜና

የኮንደምንየም እጣው ነገ ከሰዓት በኋላ ይወጣል

በቅርቡ በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በጉዳዩ ላይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሽመልስ ታምራት ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት ፦

- በነገው ዕለት 25 ሺህ 791 የ40/60 እና 20/80 ቤቶች ዕጣ ይወጣባቸዋል።

- በነገው እጣ 146 ሺህ 892 እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በቂ ቁጠባ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ይሳተፋሉ።

- በነገው እጣ አወጣጥ ነባርና በ2005 ዓ.ም በባለሶስት መኝታ ቤት የተሰሩ 300 ቤቶችም ይተላለፋሉ።

- በእጣ አወጣጡ ላይ ከዚህ ቀደም የገጠሙ ችግሮች እንዳይደገሙ አዲስ የእጣ አወጣጥ ስርዓት ተዘርግቷታ።

- የመረጃ ማጥራት እና ማደራጀት ስርዓቱ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ተከናውኗል።

- የእጣ ማውጫ መተግበሪያውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ያለማው ሲሆን ከፌደራል ተቋማት እና ከከተማ አስተዳደሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

- የእጣ አወጣጡ በቆጣቢዎች የቅድመ ግምገማ ወይም የእጣ አወጣጥ ሙከራ የተካሄደበት ነው።

- ነገ ከሰዓት ላይ የሚካሄደው የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱም በቴሌቪዠን #በቀጥታ_ስርጭት ይተላለፋል።

Credit : FBC