Get Mystery Box with random crypto!

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ። በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ | ብሩህ ወቅታዊ ዜና

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ

በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በገዛመን ቀበሌ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳስከተለ የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ መንግሥት ኮሚኒኬሽን አስታውቋል ።

ህዳር አራት ቀን 2015 ዓ.ም ከለሊቱ 6 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት ድረስ ያለማቋረጥ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል። በደረሰ የጤፍ እና የስንዴ ሰብል  እንዲሁም በጓሮ አትክልቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽ /ት ቤት ሀላፊ የሆኑት አ/ቶ አምባቸው አዲስ ተናግረዋል ።

@BruhDailyNews