Get Mystery Box with random crypto!

«እምቢ» ማለትን ተማር ጠቃሚ ላልሆነ ነገር ይሁንታህን በምትገልጽ ጊዜ ሁሉ ጠቃሚ ለሆነ ነገር | መርጌታ ይሃንስ የባህል መድሀኒት ቀማሚ

«እምቢ» ማለትን ተማር

ጠቃሚ ላልሆነ ነገር ይሁንታህን በምትገልጽ ጊዜ ሁሉ ጠቃሚ ለሆነ ነገር እምቢተኛ ትሆናለህ፡፡ ‹‹እሺ›› ብቻ ከአፋቸው የሚወጣ ሰዎች ታላቅ የሆነ ነገር ሊፈጽሙ አይችሉም፡፡ ‹‹እምቢ!›› ማለት ታላቅ እሴት ነው፡፡

ለሀሜተኛ ሰው ፊት አትስጥ፡፡ በሥራ ቦታ አሉታዊ መንፈስና ጨለምተኛነት እንዲሰፍን ከሚፈልግ ባልደረባ ጋር አትወዳጅ። በሕልሞችህ ከሚሳላቅና ራስህን እንድትጠራጠር ከሚያደርግህ ዘመድህ ራቅ፡፡ የሥራ ጊዜህን ከሚያጣብቡ የማህበራዊ ሕይወት ግዴታዎች ተቆጠብ፡፡

ለሁሉም ሰው ሁሉንም ነገር ልትሆን አትችልም፡፡ ከእኛ መካከል ምርጥ የሆኑት ይህን ያውቁታል፡፡ ለምን ቅድሚያ መስጠት እንዳለብህ እወቅ፡።ግቦችህን እወቅ፡፡ ሕይወትህን በአግባቡ ለመምራት በመጪዎቹ ሳምንታት፣ ወራትና ዓመታት ምን ማድረግ እንደሚኖርብህ በሚገባ እወቅ፡፡ ከዚያ ውጭ ለሆነው ለተቀረው ነገር ሁሉ ‹‹እምቢ!» በል። እርግጥ ነው በእምቢተኛነትህ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ቅሬታ ሊሰማቸው ይችላል። ነገር ግን ሕይወትህን ለመምራት የምትርጠው ለሌሎች ፈቃድ ተገዢ ሆነህ ነውን ወይስ የራስህን እውነትና ሕልም ተከትለህ?

ሮቢን ሻርማ
በየቀኑ አዳድስ ምክሮችን፣ ጥቆማዎች እና መረጃዎችን ለማግኘት የቻናሌን ቤተሰብ ይሁኑ
@PETER_AF
@PETER_AF