Get Mystery Box with random crypto!

የሚሳካልኝና የማይሳካልኝ የሚሳካልኝንና የማይሳካልኝን መለየት ማለት ብርቱ ጎኔን በሚገባ ለይቶ ማ | መርጌታ ይሃንስ የባህል መድሀኒት ቀማሚ

የሚሳካልኝና የማይሳካልኝ

የሚሳካልኝንና የማይሳካልኝን መለየት ማለት ብርቱ ጎኔን በሚገባ ለይቶ ማወቅ ማለት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ወደዚህች አለም ሲመጣ ቢያንስ ከአንድ ዝንባሌንና ስጦታን ጋር ነው የሚመጣው፡፡ ይህንን ዝንባሌ ወይም ስጦታ በመለየት እነሱ ላይ ማተኮር አስፈላጊ የስኬት ቁልፍ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች በብዙውን ጊዜአቸውን የሚያሳልፉት ፈጽሞ ዝንባሌአቸው ያልሆነውን ነገር ለማዳበር በመታገል ነው፡፡ አስተዋዮችን ዝንባሌአቸውና ስጦታቸው የቀደደላቸውን ፈር በመከተል ከስኬት ወደ ስኬት ይሸጋገራሉ፡፡

በሚሳካልኝና በማይሳካልኝ መካከል ለመለየት መውሰድ የምችላቸው እርምጃዎች፡-

1. ሁሉን ነገር እንደማትችል አምነህ ተቀበል

ምንም ብንታገል የማንችላቸው ነገሮች እንዳሉ በማመን መቀበልና ራስን ማረጋጋት የብስለት ምልክት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የማይችሉትን አምኖ መቀበልን እንደ ሽንፈት ስለሚቆጥሩት ካልተሰጣቸው ነገር ጋር ሲታገሉ ራሳቸውን ያደክማሉ፡፡

2. የሚያታግልህን ነገር ልቀቀው

ሳደርገው የሚያታግለኝንና ውስጤን የማያጓጓውን ነገር በመለየት ቀስ በቀስ መልቀቅ የአስተዋይነት ምልክት ነው፡፡ የማይሳካልህ ነገር ላይ ብዙ ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ስትሰዋ የሚሳካልህን ነገር እየጣልከው እንደሆነ ማስተዋል አለብህ፡፡

3. የሚሳካልህን ነገር አሳድገው

ስታደርገው የሚሳካልህንና ውስጥህን የሚያነሳሳውን ነገር በመለየት የበለጠ ጊዜን በመስጠት ማሳደግ ታላቅ የስኬት ቁልፍ ነው፡፡ ምንም አደረግህ ምንም፣ በብርታትህ ላይ እንጂ በድካምህ ላይ በፍጹም አትገንባ፡፡

ብሩህ ቀን ይሁንልን
ⒿⓄⒾⓃ: @BrilliantsAcademy 
ⓙⓞⓘⓝ: @BrilliantExams
Ⓙⓞⓘⓝ @BrilliantsMindSet