Get Mystery Box with random crypto!

Jabir mustefa official 💡

የቴሌግራም ቻናል አርማ brighhhttt — Jabir mustefa official 💡 J
የቴሌግራም ቻናል አርማ brighhhttt — Jabir mustefa official 💡
የሰርጥ አድራሻ: @brighhhttt
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.44K
የሰርጥ መግለጫ

👉"ወዳጅ አህባብ ተከታይ ለአላህ ብየ እወዳቹሃለው ♥ ይሄ የጃቢር የግል ገፅ ነው 👍

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-30 07:09:30
የፌስቡክ ፔጄን ተቀላቀሉ

10k tnx

https://www.facebook.com/Jabirim/
462 viewsJabir Mustefa, 04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 17:21:37
... « ዒሽሩነ ሷቢሩን…» መሆንና መፅናት ብቻ ነው መፍትሄው!

... ሲጥ ትላለህ እንጂ እኔ እንደሆነ ከትምህርት ገበታዬ አልቀርም በላቸው። እንደ ትናንቱም እንደው ልማርና ወደፊት ልቀይር ብዬ አልለማመጥም። በሀይማኖቴና በእኔነቴ የምትደራደረኝ ሀገር የለችኝም።

ይህችን ሀገር በጋራ እሴታችን ተዋደን፣ የግል እሴቶቻችንን ተማምነንና ተከባብረን እንሰራታለን እንጂ ሁለተኛ አማራጭ የለንም። በቀረፅከው ፓሊሲ ስር አጎንብሰን አናልፍም። የጋራ ፓሊሲያችንን ተማምነን እንቀርፃለን። አራት ነጥብ

የነገ ተስፋዎቼ! ፍፁም መንፈሳዊ ለመሆን ጣሩ፤ አድምታችሁ ተማሩ፤ ለሀገር ብልፅግና ዋልታ ትሆኑ ዘንድ ትጉ። ትናንት እኔ ያየሁትን ግን ፈፅሞ አታስተናግዱም። የሚከፈለውን ሁሉ እከፍላለሁ።

"በእኔነቴና በእምነቴ የማታከብረኝ ሀገርም ሆነ ስርኣት የለችኝም፣ አትኖረኝም!" ኢንሻአላህ ሊተህቂቅ!

Dr. Semhar Tekle
472 viewsJabir Mustefa, 14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:31:37
┏━━ ━━━━━┓
彡 @ikhwanel_muslimin
┗━━ ━━━━━┛
453 viewsJabir Mustefa, 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 19:07:00 ይህ የረሱል ሰ.ዐ.ወ ታላቅ ምክር ነው።
* አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መጣና "ለዱንያም ሆነ ለአኼራ የሚጠቅም ንግግር ለመጠየቅ መጣው" አላቸው። እሳቸውም ደግሞ "የመጣልህን ጠይቅ "አሉት። * "ከሰው ሁሉ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለው?" # እሳቸውም "አላህን ፍራ" አሉት * "ከሰው ሁሉ ሀብታም ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው። # "ባለህ ነገር ተብቃቅተሕ አላህን አመስግን" አሉት * "ትክክለኛ ፈራጅ እና ታማኝ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል # "ለራስህ የምትወደውን ለሰዎች ውደድ አሉት። * "ከሰው ሁሉ ብርቱ ለመሆን እፈልጋለ ው?" ሲል # "በአላህ ተወከል" አሉት * "በአላህ ዘንድ ብቸኛ ተመራጭ ለመሆን እፈልጋለው" ሲላቸው? # "ዚክር አብዛ" አሉት።
* "ከሰው ሁሉ በላጭ ለመሆን እና ጥሩ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል # "ለሰው ጠቃሚ ሁን" አሉት።
* "የተከበረና ቸር ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው # "ችግርህን ለፍጡር አትንገር" አሉት። * "ረሱል እና አላህ እንዲወዱኝ እፈልጋለው?" ሲል # "አንተም እነሱ የወደዱትን ውደድ" አሉት::
* "ከወንጀል የጠራው ሁኜ አላህን መገናኘት እፈልጋለው" ሲል # "ጀናባህን በደንብ ታጥበ እስቲግፋር አብዛ ማልቀስ መተናነስ አለብህ"
አሉት።* "ከበጎ ሰሪወች ለመሆን እፈልጋለው" ሲላቸውም # "አላህን ልክ እንደምታየው ሁነክ ተገዛው" አሉት። *"ኢማኔ እንዲሞላ እፈልጋለው" ሲል # "ፀባይህን አሳምር" አሉት። * "እርዝቄ እንዲሰፋ እፈልጋለው" ሲል # "ተዋዱዕ አዘውትር" አሉት።
*"ዱዓዬ ሙስተጃብ እንዲሆንልኝ እፈልጋለው?" ሲላቸው
# "ሀራም አትብላ" አሉት:* "አላህን ከሚታዘዙ ሰዎች ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል #"ግዴታዎችህን ፈፅም" አሉት። * "በአላህ ዘንድ ትልቁ ሀሠና ወይም ደግ ሥራ የቱ ነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው #"መልካም ፀባይ መተናነስ እና በበላ ላይ ሰብር ማድረግ ነው" አሉት። * "በአላህ ዘንድ የትኛው ስርዓት ነው መጥፎ ሥራ?" ሲል ሲጠይቃቸው # "መጥፎ ፀባይና ፍላጎትን መከተል ናቸው" አሉት * "በዱንያም ሆነ በአኼራ የአላህን ቁጣ የሚያበርድ ምንድነው" ሲል ጠየቃቸው? # "ድብቅ ሰደቃ እና ዘርን መቀጠል ናቸው" አሉት። * "የቂያማ ቀን በአላህ ኑር ለመሰብሰብ እፈልጋለው?" ሲል #"ሰውን አትበድል" አሉት *"የቂያማ እለት አላህ እንዲያዝንልኝ እፈልጋለው?" #"ለአላህ ባርያዎች እዘን" አሉት። *"የቂያማ ቀን የጀሀነም እሳት የሚያጠፋው ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው # "በችግር ላይ ወይም በሙሲባ ላይ ትህግስት ማድረግ ነው" አሉት። * "የቂያማ እለት ነውሬ እንዲሸፈንልኝ እፈልጋለው?" ሲል #"የወንድምህን አይብ ሸፍን" አሉት። * "የቂያማ ቀን ከአላህ ቁጣ ሰላም ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል #"በአንድም ፍጡር አትቆጣ" አሉት። አላህ(ሱወ) ባወቅነው በስማነው የምንስራ ያድርገን አሚን!!!!
489 viewsJabir Mustefa, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 18:05:49 ያለምነው አልቀረም፤ ‹ጥበብ› ተሞሸረች

‹የጥበብ ቤት› ዳግም ወደ መድረክ ተመልሳ በአፊቃሪዎቿ ታጅባ ትሞሸር ዘንድ መሰናክሎች ጥቂት አልነበሩም፡፡ ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድሩን ጨምሮ በርካታ የቀጠሮ ማራዘሚያ ሰበቦች፤ ሰኔ 12 የመንገድ መዘጋጋት ያጀበው እክል በአላህ መልካም ፈቃድ ፉርሽ ሆነው ድግሱ እውን ሆኗል፡፡ መሳቅ፤ ማልቀስ፤ መዝናናት፤ መማር፤ መደንገጥ፤ ማኩረፍ፤ መባነን፤ መጫዎት፤ ማሰላሰል፤ መገረም፤ መጨነቅና ሌሎች አያሌ ስሜቶች በግጥሞች፤ ወጎች፤ እንጉርጉሮ፤ ዳዕዋ፤ ተውኔት፤መነባነብ፤ ነሺዳ፤ አነቃቂ ንግግር፤ ካሊዮግራፊና በድንቅ ታዳሚውን ያሳተፉ ፈጠራዎች ተኮርኩረዋል፡፡ ለአዘጋጆች ጭምር እንግዳ የሆኑ አስደናቂ የመድረክ ትሩፋቶች በአዕምሯችን የሳልነው ሁሉ ስጋ ለብሶ እንዲታይ መሆኑ ይህንን የፈቀደው የነገሮች ሁሉ አስተናባሪ የተመሰገ ነው፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡ እሁድ ዕለት የተሞሸረችው ‹ጥበብ› የቀጣይ ወር ጫጉላዋን ታስናፍቀናለች፡፡ አክብራችሁን የተገኛችሁ ሁሉ አላህ ያክብራችሁ፡፡ የዕለቱ ድግስ ያለፋችሁ በቀጣይ እንገናኛለን፡፡ ኢንሻአላህ!

የጥበብ ቤትን ድግስ በአካል ተገኝታችሁ መቋደስ ላልቻላችሁ፣

የጥበብ ቤት ዩ ቲዩብ ቻናል:–https://youtube.com/channel/UCCCWT7rEvbkTjFe8IceV2-w
የጥበብ ቤት ቴሌግራም ቻናል:– https://t.me/yehulubet
የጥበብ ቤት የፌስቡክ ገፅ : https://www.facebook.com/የጥበብ-ቤት-Yetebeb-Bet-106187998793025/

ለወዳጆቻችሁ ብታጋሩ ሁላችሁም ታተርፋላችሁ!
367 viewsJabir Mustefa, 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 18:05:49
329 viewsJabir Mustefa, 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 06:46:41
ጀሀነም የሚገባው ወደ ጀሀነም፣ ጀነት የሚገባውም ወደ ጀነት ከገባ በኋላ አንድ ተጣሪ እንዲህ ሲል ይጣራል!

አንተ ሙሐመድ ተደሰተክ ወይ?

እርሳቸው እንዲህ ይለሉ«ጌታዬ! ወላሂ አልተደሰትኩም። ከኡመቶቼ እሳት ውስጥ የቀረ አለ»

አላህም ለመላኢኮች «ቅንጣት ታክል ኢማን በቀልቡ ያለውን ሁሉ ከእሳት አውጡ» በማለት ያዛቸዋል።ከዚያም ጀሀነም በሯ ይከፈትና የተወሰነው የሙስሊሙ ክፍል ወጥቶ ወደ ጀነት ይተማል።

አላህ በድጋሚ «አንተ ሙሐመድ ሆይ! ተደሰትክ?» ይላቸዋል።

«ጌታዬ ባንተ እምላለሁ! አሁንም ከህዝቦቼ የቀሩ አሉ» ብለው ያለቅሳሉ!
አላህም ለመላእክቱ «አይኑ የትንኝ ራስ የምታክል እንባም ብትሆን እኔን ፈርታ ያነባችን ሁሉ አውጡ» በማለት ያዛል።

ከዚያም «አንተ ሙሐመድ ሆይአሁንስ ተደሰትክ?» ይላቸዋል።
«ወላሂ አልተደሰትኩም። አሁንም ከኡመቴ የቀሩ ሰዎች አሉ። ይላሉ ረሱላችን ﷺ»

አላህም ለመላኢኮች «ላኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሐመዱን ረሱሉላህ ያለውን በጠቅላላ ከጀሀነም አውጧቸው» በማለት ያዛል። ጀሀነም በሮቿ ተከፍተው ሁሉም ወደመስካሪዎች ጎራ ይነጉዳሉ።

ከዚያም ወደ ጀነት እንዲገቡ ይደረጋል። ይሄኔ ለመጨረሻ ጊዜ ጀሀነም ትዘጋለች!!

አላህ የርሳቸውን ሸፈዓ የምናገኝ ያድርገን ሰ.ዐ.ወ
752 viewsJabir Mustefa, 03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ