Get Mystery Box with random crypto!

ሙህተላ በሆነቺው የፍልስጥኤም ምድር غዛ ላይ የሰማነው ኸበር እጅግ የሚደንቅ ነው። ከቀናቶች በፊት | Jabir mustefa official 💡

ሙህተላ በሆነቺው የፍልስጥኤም ምድር غዛ ላይ የሰማነው ኸበር እጅግ የሚደንቅ ነው። ከቀናቶች በፊት ከ580 በላይ የሚሆኑ የአላህን ቃል የተሸከሙ(ሁፋዞች) በአንድ መስጂድ ጥላ ስር ተሰብስበው ከፈጅር ሰላት አንስተው እስከ መغሪብ ድረስ በአንድ ጀልሳህ ሁለት ሁለት እየሆኑ ቁርዐንን ሙሉ ለሙሉ ተደማምጠው በግማሽ ቀን ማጠናቀቅ ችለዋል። ሱብሀነላህ! የሚገርመው በዚህ ፕሮግራም ወንዱም ሴቱም፣ ትልቁም ቲኒሹም የተካፈሉ ሲሆን፣ ከ12 አመት ታዳጊ አንስቶ እስከ 63 አመት የሚደርሱ ትልልቅ አባቶች ጭምር ተሳትፈዋል።

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቁርዐን ኮፒዎች ሙሉ ለሙሉ ከምድረ-ገፅ ቢጠፉ በቀናቶች ውስጥ አንዲት ነጥብ ሳያጓድሉ እራሱን የሚመልሱልን ሁፋዞች አሉን። አልሀምዱሊላህ ይሄን እስልምና ውስጥ እንጂ የትም አታገኘውም። ሱብሀነላህ!!!