Get Mystery Box with random crypto!

ህዝብ አርግዞና አምጦ እንደወለደን ለህዝብ ኖረን በህዝብ እንዘልቃለን! በዕድሜ የ4 ዓመት ለጋ በም | Bonga University

ህዝብ አርግዞና አምጦ እንደወለደን ለህዝብ ኖረን በህዝብ እንዘልቃለን!
በዕድሜ የ4 ዓመት ለጋ በምግባሩ ግን የወገንና የሃገር ኩራት በመሆን አንቱታን ያተረፈዉ የኛና የናንተ የጋራችን ብርሃን የሆነዉ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተወለደዉ ከህዝብ ነዉ፤ ጥረቱ፣ ህልሙና አበርክቶዉም ለህዝብ ነዉ፤ ዘላቂነቱ የሚረጋገጠዉ፣ ዉጤቱ የሚለካዉና መንገዱ የሚያበራዉም በህዝብ ነዉ፡፡ከህዝብ እንደተወለድን ለህዝብ እንተጋለን በህዝብ እንፀናለን፡፡ ለዚህም ነዉ ገና ከዉልደታችን “በጋራ እንችላለን!” ብለን ጀምረን በጋራ ችለን በጋራ እየተሻገርን ያለነዉ፡፡
በተቋማችን የናንተን ልጆች ስንቀበል ፍፁም የሰዉ ልጆች ፍፁም ኢትዮጵያዊ ናቸዉ ብለን እንጂ በብሄራቸዉ በሃይማኖታቸዉና በቋንቋቸዉ ለይተን አይደለም የምንቀበላቸዉ፡፡ ልጆቻችሁን እንደ ልጆቻችን ቆጥረን ስንረከብ ከእኛ ጋር በሚኖራቸዉ ቆይታ ከሰብዓዊነትና ከኢትዮጵዊነት ስያፈነግጡ መክረን ገስፀንና ቀጥተን እናስተካክላለን፤ በሰብዓዊነታቸዉ አርዓያ ሆነዉ በኢትዮጵያዊነታቸዉ ጀግነዉና በትምህርታቸዉ ያኮሩንን ደግሞ ግንባራቸዉን ስመን ሸልመንና መርቀን ከተረከብነዉ በብዙ አሻሽለን ከእናንተ አልፎ የሰዉ ልጆች ኩራት የሃግር መከታ አድርገን እንሸኛቸዋለን፡፡ እንዲሻሻሉ የተሰጣቸዉን ብዙ ዕድሎችን ያመከኑትን ደግሞ የሃገርና የወገን ኩራቶችን እንዳይመርዙብን በጊዜ ወደየቤታቸዉ እንሸኛቸዋለን፡፡ በፍፁም ለሃገርና ለወገን ተድላ እንጂ ሸክምና ዕዳ የሆነ ትዉልድ አናበረክትም፡፡ እንደ መማር ማስተማሩ ሁሉ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎቻችንም ሃገርን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያሻግሩና የሰዉ ልጆችን ኑሮ በእጅጉ የሚቀይሩ ሆኖ የተቃኙ ናቸዉ፡፡ የተቋማችን የአመራር፣ የአካዳሚክና የአስተዳደር ሰራተኞች ስብጥርም የሃገር ቅርፅ የያዘ፣ በሰዉኛ የሚመዘንና ብቃትን መሰረት ያደረገ ነዉ፡፡
እዉነታዉና ማንነታችን ይህ ሆኖ ሳለ ሰሞኑን በተቋማችን በድንገት ያጣነዉ ተማሪ ሃዘኑ ከቤተሰቡ በማይተናነስ የኛንም ልብ የሰበረ ቢሆንም አንዳንድ እኩይ አጀንዳ ያነገቡ ተማሪዎች በምንም ምክንያት ከተማሪዉ ሞት ጋር ግኑኝነት የለለዉ አጀንዳ በማራገብ የተቋሙን ንብረት በማዉደም፣ የተቋሙን ሰራተኞች በመደብደብና የመማር ማስተማር ስራዉ እንድስተጓጎል በማድረግ በተቋሙ ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ ይህንንም ለመቆጣጠርና ለማስተካከል እንደ ቤተሰብ ተመክሯል፣ ብዙ ዕድሎችን ለመስጠት ተችሏል ስያልፍም በይቅርታ ለማለፍ ተሞክሯል፡፡ ነገር ግን እኔዚህ ዉስን ተማሪዎች የተሰጣቸን ዕድል ከመጠቀምና ከመሻሻል ይልቅ ትኩረታቸዉ ያነገቡት እኩይ አጀንዳ ላይ በመሆኑ አሻፈረኝ በማለታቸዉ እንደወትሮ ሁሉ ለተቋም፣ ለሃገርና ለወገን ህልዉና በማሰብ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመናበብ በህግ መጠየቅ ያለባቸዉን ለህግ በማቅረብ፤ በአስተዳደራዊና በድስፕሊን እርምጃ መጠየቅ ባለባቸዉ ላይ እርምጃ በመዉሰድ፤ በምክርና በተግሳፅ ዕድላቸዉን ለመጠቀም ዝግጁ የሆኑትን በይቅርታ ወደ ትምህርታቸዉ በመመለስና ያለጥፋታቸዉ የተረበሹትን በማረጋጋት የተለመደዉን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ ለማስቀጠል ተችሏል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ይህ ጥረታችን እንደወትሮ ሁሉ የተሳካ እንዲሆን የዘወትር አጋርነታችሁ ያልተለየንን የፈደራል የክልል የዞንና የከተማ ፀጥታ አካላት፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአከባቢና የተቋሙ ማህበረሰቦች ሁሉ ያለናንተ እኛ ምንም ነንና እጅግ አድርገን እናመሰግናለን!
ከህዝብ እንደተወለድን ለህዝብ እንተጋለን በህዝብ እንፀናለን አንጂ ለህዝብ ሸክም አንሆንም!
በጋራ እንችላለን!

@BongaUniversityCommunication