Get Mystery Box with random crypto!

3ኛ ዙር እችላለሁ! የሴቶች የሥራ ፈጠራ፣ የሙዚቃ፤የቲክቶክ ቪዲዮና እያሳተፉ ይሸለሙ ውድድር ! | Bank of Abyssinia

3ኛ ዙር እችላለሁ!

የሴቶች የሥራ ፈጠራ፣ የሙዚቃ፤የቲክቶክ ቪዲዮና እያሳተፉ ይሸለሙ ውድድር !
ባንካችን በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ በያዝነው የአውሮፓውያን ወር ከማርች 8-31, 2024 ድረስ በሁለት የተከፈሉ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ክፍት አድርጓል፡፡
1) የሙዚቃ እና የቲክቶክ ቪዲዮ ተሰጥዖ ውድድር
ይህ ውድድር የሚከናወነው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓም. ሲሆን ባንካችን የሙዚቃ ተሰጥኦ ያላቸውን ሴት ተሳታፊዎችን በማወዳደር በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ የተለዩ አሸናፊዎችን በየደረጃው ይሸልማል፡፡ በዚህም መሰረት
1ኛ 100,000 ብር
2ኛ 75,000 ብር
3ኛ 50,000 ብር ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡
በዚህም መሠረት በመርሃ-ግብሩ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴት ተወዳዳሪዎች አስቀድማችሁ የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ገፅን https://www.facebook.com/BoAeth/ መወዳጀት ይኖርባችኋል፡፡ በመቀጠልም በሙዚቃው ዘርፍ ተሰጥኦዬን ያሳያል የምትሉትን ከሶስት (3) ደቂቃ ያልበለጠ የሙዚቃ ሥራ ያለ ሙዚቃ መሣሪያ በቪዲዮ ሰርታችሁ ከዚህ በታች በተቀመጠው ቴሌግራም መላክ ይኖርባችኋል፡፡
በተመረጡ ቲክቶከሮች መካከል ባንካችን ለሴት ደንበኞቻችን ያዘጋጃቸውን አደይና ዘሃራ የቁጠባ ሂሳቦችን በተለየ መንገድ የማስተዋወቅ ውድድር ይካሄዳል፡፡
የቴሌግራም አድራሻ------------0942-728501
2) የሥራ ፈጠራ ውድድር
የሥራ ፈጠራ ውድድር የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታት ባንኩ ካሉት 10 ዲስትሪክቶች ከእያንዳንዱ አምስት(5) የስራ ፈጣሪዎችን በአጠቃላይ 50 የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን በመምረጥ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቶችን የምታሟሉ የሥራ ፈጣሪዎች አቅራቢያችሁ ባሉ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ፅ/ቤቶች በመቅረብ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓም. ባሉት ቀናት ብቻ በፁሑፍ ጥያቄያችሁን እንድታቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
2) እያሳተፉ ይሸለሙ
በዚህ ውድድር ደግሞ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሴቶች የሚሳተፉበት ለባንካችን አዳዲስ ደንበኞችን በመመልመል በመለመልዋቸው የደንበኞች ብዛት መጠን ተሳታፊዎች የገንዘብ ሽልማት የሚሸለሙበት ውድድር ይከናወናል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለሴቶች ደንበኞቻችን የተዘጋጁትን የመደበኛ አደይና የወለድ አልባ ዘሃራ አገልግሎቶችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቅሞችን እንድታገኙ እንጋብዛለን፡፡ ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ከዚህ በታች ያግኙ፡፡
መልካም የሴቶች ቀን!