Get Mystery Box with random crypto!

ባንካችን አቢሲንያ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን የአፖሎ የተማሪ አምባሳደ | Bank of Abyssinia

ባንካችን አቢሲንያ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን የአፖሎ የተማሪ አምባሳደር በማድረግ፣ አፖሎን ለደንበኞች በማስተዋወቅ እና በምዝገባ ባሳኩት መጠን የኮሚሽን ክፍያ ለመክፈል አስፈላጊውን ዝግጅት ጨርሷል፡፡ ስለሆነም የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን ፍላጎት ያላቸውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አወዳድሮ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል፡፡ ከተጨማሪ የገቢ ምንጭ ባለፈ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ሲወጡ የሥራ ልምድ ይሆናቸው ዘንድ ያላቸውን ችሎታ የሚያሳድጉበት፤ እንዲሁም እንደሚያሳዩት ውጤትና ተነሳሽነት ሌሎች ሽልማቶችን የሚያገኙበትን አጋጣሚ አቢሲንያ ባንክ ፈጥሯል፡፡
የዚህ እድል ተሳታፊ ለመሆን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ነጥቦች፣
የከፍተኛ ትምህርት እየተከታተላችሁ መሆኑን የሚገልፅ የተማሪ መታወቂያ፤
የአፖሎ አካውንት ባለቤት መሆን፤ ከ150 ቃላት ባልበለጠ ራሳችሁን የሚገልፅ አጭር ፅሁፍ እና
በቀላሉ ለመሙላት በተዘጋጀው የማመልከቻ ገጽ ከ150 ቃላት ባልበለጠ ለምን የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን እንደፈለጋችሁ መግለፅ ብቻ ናቸው፡፡ ስለሆነም ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጠቀም ይመዝግቡ፡፡

https://apolsup.bankofabyssinia.com/studentAgent


ከአፖሎ ጋር ተፍ ተፍ በሉ፡፡
ከስራ በፊት ስራ ጀምሩ፡፡
ጠቀም ያለ የሪፈራል ኮሚሽንም አግኙ!