Get Mystery Box with random crypto!

'ፍርዱ በህግ ላይ ያለን አመኔታ የሚያሳጣ ነው!' - ሚኪያስ (የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል) እኔ የ | HerEthiopia

"ፍርዱ በህግ ላይ ያለን አመኔታ የሚያሳጣ ነው!" - ሚኪያስ (የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል)

እኔ የህግ ባለሙያ ነኝ። ዛሬ በወጣው መረጃ በጣም አዝኜአለው። እንዴት አባት ልጁን ደፍሮ 9 አመት ብቻ ሊቀጣ እንደቻለ ሊገባኝ አልቻለም።

ወንጀሉ እንደ ህጉ አንድ ወንጀል ብቻ አይደለም። ይልቁንም ተደራራቢ ወንጀል እንጂ ፦

1ኛ/ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል
2ኛ/ ተጠቂዋን በመደብደብ ወንጀል
3ኛ/ በዘመዳሞች የሚፈፀም ወንጀልን መጥቀስ ይቻላል።

የእነዚ ወንጀሎች ቅጣት ከወንጀሉ አፈፃፀም አንፃር ብንደምረው እና ሊነሱ የሚችሉ የወንጀል ማክበጃዋችን ብናይ፦

1ኛ/ የህዝብ አደራ የተጣለበት ዋና ሳጅን በመሆኑ

2ኛ/ እራሷን መከላከል በማትችል ልጅ ለይ ወንጀሉ መፈፀሙ ከዛም በላይ በቅርብ የስጋ ዝምድና (ልጅ) ለይ መፈፀሙ በየትኛውም ሒሳብ የትኛውም ያክል የወንጀል ማቅለያ ቢኖር 9 አመት ተገቢም ፍትሀዊም ህጋዊም አደለም።

ይህ ፍርድ እኮ ምን ያክል በህግ ላይ ያለን አመኔታ የሚያሳጣ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia