Get Mystery Box with random crypto!

ነሐሴ 25፤2014-የሶቪየት ንብረት የመጨረሻው መሪ ሚካሂል ጎርባቾቭ በ91 አመታቸው ዜና እረፍታቸ | Bisratfm101.1

ነሐሴ 25፤2014-የሶቪየት ንብረት የመጨረሻው መሪ ሚካሂል ጎርባቾቭ በ91 አመታቸው ዜና እረፍታቸዉ ተሰማ

የቀዝቃዛው ጦርነት ሰላማዊ ፍጻሜ እንዲያገኝ ያደረጉት የቀድሞ የሶቪየት መሪ ሚካሂል ጎርባቾቭ በ91 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።ጎርባቾቭ እ.ኤ.አ በ1985 ወደ ስልጣን የመጡ ሲሆን በስልጣን ዘመናቸዉ በርካታ ማሻሻያዎችን ጨምሮ የሶቪየት ህብረትን በር በመክፈት ከአለም ጋር ያላትን ግንኙነት ከፍ አድርገዋል፡፡

ነገር ግን የሕብረቱን ቀስ በቀስ ውድቀት መከላከል አልቻለም በርካታ ሩሲያውያን ለዓመታት ለተከሰቱት ብጥብጥ ተጠያቂ ያድርጓቸዋል፡፡ከሩሲያ ውጭ ከፍተኛ ከበሬታ የነበራቸዉ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ "የታሪክን ሂደት ቀያሪ" ሲሉ ይገልጿቸዋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሚካኢል ጎርባቾቭ ዓለማችን ከፍ ያለ ዓለም አቀፋዊ መሪ አጥታለች፣ ቁርጠኛ ባለ ብዙ ወገን እና ለሰላም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሰሩ ናቸዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ህይወታቸዉ ያለፈበት በሞስኮ የሚገኘው ሆስፒታል ለረጅም ጊዜ በከባድ ህመም ሲሰቃይ እንደነበር አስታዉቋል።

ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የሻከረ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ቢነገርም ፑቲን ግን በህልፈታቸዉነ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል ሲል ቃል አቀባያቸዉ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ

https://bit.ly/3To2bgR

#BisratNews #BisratFM #Soviet_Union

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv