Get Mystery Box with random crypto!

ነሐሴ 25፤2014-ጫማውን ከወራጅ ውሃ ለማውጣት የሞከረው የ8 ዓመት ታዳጊ በጎርፍ ተወሰዶ ህይወቱ | Bisratfm101.1

ነሐሴ 25፤2014-ጫማውን ከወራጅ ውሃ ለማውጣት የሞከረው የ8 ዓመት ታዳጊ በጎርፍ ተወሰዶ ህይወቱ አለፈ !!

ወራጅ ውሃ ውስጥ ጫማው የገባበት የ8ዓመት ታዳጊ ጫማውን ከወራጅ ውሃ ለማውጣት ሲሞክር በጎርፍ መወሰዱን የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ትላንት ማክሰኞ ማምሻዉን በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ቆሬ አካባቢ በሚገኝ ወራጅ ወንዝ ጫማዬን ጎርፍ ወሰደብኝ በሚል ጫማዉን ለማዉጣት ሲሞክር የነበረዉ የ8 ዓመት ታዳጊ በጎርፍ ተወስዷል።

የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች ባደረጉት ፍለጋ የታዳጊው አስክሬን በዛሬው እለት ረፋድ 3፡30 ላይ በተለምዶ ስያሜ ቆሬ ኮንዶሚኒየም ታቦት ማደሪያ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ላይ መገኘቱ ተነግሯል፡፡


በዘንድሮው የክረምት ወቅት በአዲስ አበባ በተመሳሳይ ሁኔታ እድሜያቸዉ ከስምንት እሰከ አስራ አራት የሆኑ አምስት ታዳጊዎች ህይወታቸዉ በጎርፍ አደጋ ማለፍን አቶ ንጋቱ ጨምረው ነግረውናል።


መረጃዎችን መሰረት ተደርጎ የጥንቃቄ መልእክቶችን ኮሚሽኑ በተደጋጋሚ ቢያስተላልፍም የታዳጊዎችን ሞት ማስቆም አልተቻለም ያሉት ባሙያው ወላጆች እና ማህበረሰቡ ታዳጊዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


ትግስት ላቀው

https://bit.ly/3q0oRpX

#BisratNews #BisratFM #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv