Get Mystery Box with random crypto!

ነሐሴ 24፤2014-በብራዚል ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ክርክር ላይ ተቀናቃኞቹ ቦልሶናሮ እና ሉላ ስድብ አ | Bisratfm101.1

ነሐሴ 24፤2014-በብራዚል ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ክርክር ላይ ተቀናቃኞቹ ቦልሶናሮ እና ሉላ ስድብ አዘል ንግግር ማድረጋቸዉ ተሰማ

የብራዚሉ የቀኝ ዘመም ፕሬዝደንት ጃየር ቦልሶናሮ እና የግራ ክንፍ የቀድሞ መሪ ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ በጥቅምት ወር ከሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ በፊት የመጀመርያውን የቴሌቪዥን ክርክር አድርገዋል፡፡የወቅቱ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ የቀድሞ ፕሬዝዳንቱን በብራዚል ታሪክ ውስጥ እጅግ ሙሰኛ የሆነ መንግስትን መርተዋል ሲሉ ከሰዋል።

ሉላ በተራቸው፣በቦልሶናሮ አመራር ብራዚል ጠፋች ሲሉ ተናግረዋል፡፡ከ2003 እስከ 2010 በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት ሉላ በምርጫው ፉክክር ሊያሸንፉ እንደሚችሉ አስቀድመዉ እየወጡ ያሉ የአስተያየት ሰጪዎች መረጃ ይጠቁማሉ።

በሁለቱ እጩዎች መካከል ያለው ልዩነት ግን እየጠበበ ይመስላል።በግንባር ባደረጉት ክርክር ሁለቱን ጨምሮ ሌሎች አራት ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች በሳኦ ፓውሎ በቲቪ ተከራክረዋል፡፡ክርክሩ እንደተጀመረ የ67 አመቱ ቦልሶናሮ የ76 ዓመቱን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሉላን ለማጥቃት ጊዜ አላባከኑም።"የእርስዎ መንግስት በብራዚል ታሪክ እጅግ ሙሰኛ ነበር" ብለዋል፡፡

በ2018 ሉላ በሙስና ወንጀል ተከሰዉ በእስራት መቀጣታቸዉንን በመጥቀስ "የቀድሞ ወንጀለኛ" በማለት ደጋግመዉ ጠርተዋል።ሉላ የጥፋተኝነት ውሳኔው በጠቅላይ ፍርድ ቤት መሻሩን በመግለጽ የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት ሞክረዋል፡፡ነገር ግን ቦልሶናሮ በሉላ አስተዳደር ላይ ያላቸውን ትችት አላቋረጡም። የብራዚል መንግስት ግዙፍ የነዳጅ ዘይት ኩባንያ ፔትሮብራስን በማንሳት የሙስና ቅሌት ያስታወሱ ሲሆን "በዝርፊያ ላይ የተመሰረተ መንግስት ነበር" ብለዋል።"ለምን ወደ ስልጣን በድጋሚ መምጣት ይፈልጋሉ? በፔትሮብራስ ላይ እንደገና ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ?" በማለት አክለዋል።

ሉላ በበኩላቸው መንግስታቸው በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከድህነት ለማላቀቅ ላደረገው ጥረት መታወስ አለበት ያሉ ሲሆን ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ሀገሪቱን እያፈራረሱ ነው ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ

https://bit.ly/3KuMro2

#BisratNews #BisratFM #Brazil

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

https://bit.ly/3mIehRv