Get Mystery Box with random crypto!

ፈረስ ትራንስፖርት ቢላሉል ሐበሺ ለሚያከናውናቸው በጎ ተግባራቶች ድጋፍ አደረገ፡፡ ========= | Bilalul Habeshi Community 🌻 ቢላሉል ሐበሺ - ኑ ወደ ደግነት

ፈረስ ትራንስፖርት ቢላሉል ሐበሺ ለሚያከናውናቸው በጎ ተግባራቶች ድጋፍ አደረገ፡፡
==================================

ፈረስ ትራንስፖርት ከሚሰጠው ትራንስፖርት ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ሁሉም የፈረስ ቤተሰብ ያደረገውን መልካም ድጋፍ ለተለያዩ በጎ አድራጎት ተቋማትና ግለሰቦች አበርክቷል፡፡ ከነዚህም ተቋማት ውስጥ አንዱ ቢላሉል ሐበሺ የልማትና የመረዳጃ እድር ይገኝበታል፡፡

የፈረስ የማይልስ ልገሳ ፕሮግራም ላይም የቢላሉል ሐበሺ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሙስጠፋ መሐመድ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡-

“የሰሩትን ገንዘብ ለበጎ ስራ ማዋልና በጎ ስራ ላይ ያሉ ወገኖች መደገፍና ማገዝ ቅን ልብ ይፈልጋል፡፡ እንዲህ አይነት በጎ ስራ የሚሰሩ ተቋማትን ደግሞ ሁላችንም መደገፍ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መምታት ነው፡፡ ከፈረስ ማይልስ ጋር በአጋርነት መስራት የራሳችንን ምድራዊና ሰማያዊ የሆነን ሥራን ነው የምንሰራው፡፡'' በዚሁ ዝግጅት ላይ ቢላሉል ሐበሺ የሚያከናውናቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያስተዋወቁ ሲሆን እነዚህን በጎ ስራዎች ከመደገፊያ ስልት አንዱ በሆነው የ6833 አባል እንዲሆኑ ጥሪያቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በቦታው የነበሩ ተሳታፊዎችም አባል እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም ለሁሉም የፈረስ ቤተሰብ ላሳያችሁት መልካምነት ከልብ እናመሰግናለን በማለት ንግግራቸውን ጨርሰዋል።