Get Mystery Box with random crypto!

ወሲባዊ_ቴክስት [Sex_Chat] ጥያቄ : እኔና እጮኛዬ እስከዛሬ በአካል ስንገናኝ እጅ ለእጅ ከ | Marriage Tube

ወሲባዊ_ቴክስት [Sex_Chat]

ጥያቄ :
እኔና እጮኛዬ እስከዛሬ በአካል ስንገናኝ እጅ ለእጅ ከመያያዝ ያለፈ ምንም ነገር ባናደርግም በቴክስት ግን በጣም ወጣ ያሉ ነገሮችን( ስለ ሴክስ ጭምር) በጣም እናወራለን::ከጋብቻ በፊት ወደምንም ነገር መግባት እንደሌለብን በግልፅ አውርተናል::ነገር ግን አንዳንዴ በቴክስት የምናወራው ነገር በእውን ያን ነገር የፈፀምኩ እስኪመስለኝ ፀፀት ውስጥ ይከተኛል::
ይህ ነገር ችግር ይኖረው ይሁን?

መልስ:-
ከእጮኛሽ ጋር በግልፅ ስለ ወደፊታቹ አውርታቹ በየጊዜው ስትገናኙ ራሳቹን መጠበቃቹ የሚያኮራ ተግባር ነው:: ቃላቹን ለመጠበቅ ያላቹ ቆራጥነትም አስደንቆኛል::
ነገርግን የቴክስታቹ ነገር ግራ አጋብቶኛል::እንደሚመስለኝ ራሳቹን እያሞኛቹ ነው::ሁሉንም ነገር ከጋብቻ በፊት ላለመፈፀም ወስናችሁ ነገር ግን በቴክስት እንደዛ ማውራታቹ የፍቅር ግንኙነታቹን ንፁ የሚያደርገው አይመስለኝም::ይህ ድርጊት ከሴክስ ውጪ ከጋብቻ በፊት ምንም ነገር ብናደርግ ጣጣ የለውም ከሚሉት ጎራ እንዳስቀምጣቹ አድርጎኛል ያ ደግሞ ጤናማ እና መፅሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም::
ስለ ሴክስ አብዝታቹ ማውራታቹ በግንኙነታቹ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ከክርስቶስ ይልቅ የምታወሩት ነገር እንዲነግስ ያደርጋል::በነገርሽኝ አይነት ፍጥነት ከቀጠላቹ ከጋብቻ በፊት አናደርግም ያላቹት ቃል ላለመፍረሱ ምንም ዋስትና የላቹም::
አዕምሯን ከየትኛውም የሰውነት ክፍል በላይ ለሴክስ sensetive ነው::ስለዚህ በሀሳባቹ አዕምሯቹን ስለዚህ ነገር ሞላቹ ማለት የበለጠ አደጋ ላይ ናቹ::
ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር በሀሳብ የፈፀምናቸው ሀጢያቶች በተግባር ከምንፈፅመው ጋር አቻ እንደሆነ ነው::

እስቲ ይህን ክፍል በማስተዋል ተመልከቺ!

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5)
27፤ አታመንዝር እንደ ተባለ ሰምታችኋል።

28፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።

29፤ ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና።

30፤ ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና።

           ስለዚህ አስተውሉ!!


                 ይቀላቀሉን

    [ https://t.me/sozo_purity ]