Get Mystery Box with random crypto!

ሰላማችሁ ይብዛ ። ባለማቋረጥ ስለምትከታተሉ አመሰግናለሁ መጽሐፍ በግልጽ እንደምነግረን ውጊያችን | Biblical Doctrine 🇪🇹

ሰላማችሁ ይብዛ ። ባለማቋረጥ ስለምትከታተሉ አመሰግናለሁ

መጽሐፍ በግልጽ እንደምነግረን ውጊያችን ከስጋና ከደም ጋር አይደለም። ያ ማለት ከላይ እንዳነበብነው ሥጋና ደም ስንል ሰዎች ማለታችን ነው ። ስለሆነም ጠላታችን ማን እንደሆነ ለይተን ማወቅ አስፈላጊ ነው ። ወደተሳሳተ አቅጣጫ እየተኮስን ዘመን እንዳንጨርስ ማለት ነው ። ብዙ ጊዜ እኛ ጠላታችን ስጋና ደም ያለው ይመስል በማያዋጣን ነገር ስንታገል እራሳችንን እናገኛለን። መጽሐፉም እንዳስቀመጠልን ግልጽ የሆነ ጠላታችን ሰይጣን(ዲያብሎስ )ነው ።
በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች እኛን በመጥላት የእኛ ጠላቶች ልሆኑ ይችላሉ ። ግን ከበስተጀርባቸው የምሰራ በአይናችን የማይታይ እርሱም እውነተኛ ጠላታችን ሀሳባቸውን ልቆጣጠር ይችላል ። ከሰው ጋር በሰላም መኖርን የሚከለክል እመኑኝ ሰይጣን ብቻ ነው ። መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ሀሳቦች በግልጽ ያስቀምጥልናል። “ይልቁንስ፣ “ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም አጠጣው። ይህን በማድረግህም የእሳት ፍም በራሱ ላይ ትከምራለህ።” ሮሜ 12፥20 (አዲሱ መ.ት)
እዚህ ስፍራ የምናነበው ጠላት ሰው ሆነው በግል ጥቅምም ሆነ በአንዳች ምክንያት ለሚጠሉን ሰዎች ነው ። እነዚህን እንድንወዳቸው መጽሐፍ ያሳስበናል። ነገር ግን ለሰይጣን ወይም ለዲያብሎስ “እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ ከእናንተም ይሸሻል።”
— ያዕቆብ 4፥7 (አዲሱ መ.ት) ይለናል ። በአንድ በኩል ዲያብሎስን ተቃወሙ ስለን በሌላ በኩል ለእግዚአብሔር ተገዙ እያለን ነው ። ጠላትን ማሸነፍ ማለት ለእግዚአብሔር መገዛት ማለትም ይሆናል። ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ሳንገዛ ልናሸኖፈው የምቻለን ጠላት የለም ።
እውነተኛ ጠላትን ማወቅ ለእውነተኛ ድል ያበቃል ። አለ ጥርጥር ጠላታችን ሰይጣን ወይም ዲያብሎስ ነው ።
ሰይጣን ፦ማለት የግርክ ቃል ስሆን ተቃዋሚ ወይም ጠላት የሚል ትርጓሜ አለው ።
ዲያብሎስ ፦ ማለት የዕብራይስጥ ቃል ስሆን ከሳሽ የሚል ትርጓሜ አለው ።

አንድ አማኝ ማወቅ ያለበት ሦስት ዋና ዋና ጠላቶች አሉት
1,ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን
2, ዓለም 1ዮሐ 2፥15-17
3, የኃጢአት ተፈጥሮ ገላ 5፥16-26
አሁን የሚናጠናው ትምህርት ስለ መንፈሳዊ ውጊያ ስለሆነ በጣም ትኩረት የሚናደርገውም በመንፈሳዊ ውጊያ ላይ ነው ። ከላይ እንደተመለከተትነው ሦስቱ የአማኞች ጠላት ዓላማቸው እኛን ከርስት ማስወጣት ነው ።
ሁሉንም ነገር ማብራራት የትምህርታችን ዓላማ ባለመሆኑ ለጊዜው የሚጠቅመንን ብቻ እንወያያለን ።
ዓለምና የኃጢአት ተፈጥሮ የዲያብሎስ ዋና መሣርያዎች ናቸው ።

የጠላት ሥልቶች
የሰይጣንን ስልት ማወቅ አስፈላጊ ነገር ስሆን በኤፌሶን መጽሐፍም ሆነ አጠቃላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ታርክ ስንመለከት ሰይጣን የተጠቀማቸው ስልቶች ተመሳሳይነት አላቸው ።ስልቱም የተንኮል ሽንገላ ነው ። ሰይጣን ማንንም አስገድዶ ኃጢአት እንዲሰራ አድርጎ አያውቅም ። ነገርግን የእኛን ሀሳብ በመጠቀም በተንኮል ያሸንፈናል ።ለዚህም ትልቁ ምሳሌ የሚሆነን የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ናቸው ። አዳም እና ሄዋን

ሰይጣን አሁን የሰው ልጆች እየቀመሱ ያሉትን መከራና ውድቀት ያመጣው በዛቻ፣በጉልበትና በኃይል ሳይሆን ሰዎችን አታሎ በማሳሳት ነው ። የእርሱን አሠራር በጥልቀት ከተረዳን በቀላሉ ማሸነፍ እንችላለን ።ዛሬም ብሆን አንድም ቀን ሰይጣን ኃጢአት ካልሰራህ እገድለሀለሁ በሚል ዛቻ አለመጠቀሙን ልብ ይሏል ።
Join Us
@BiblicalDoctrine
@BiblicalDoctrine
@BiblicalDoctrine
#share