Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና የኢትዮጵያ መከላከያ ' ቆቦ ' ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ። የ | Betty Tafese Official

ሰበር ዜና


የኢትዮጵያ መከላከያ " ቆቦ " ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብሏል።

በዚህም ፤ " የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል " ሲል አሳውቋል።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል " ብሏል።

ምንም እንኳን ከተለያየ አቅጣጫ ሰላም እንዲሰፍን እና መሳሪያ ወርዶ ንግግር እንዲጀመር ጥሪዎች ቢቀርቡም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል። #ሼር ይደረግ

ለፈጣንና ታማኝ መረጃዎች @emsmereja ን join ማድረጎን አይርሱ
@emsmereja
@emsmereja
@emsmerej