Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ መጻሕፍት

የቴሌግራም ቻናል አርማ betemetsihaf — ቤተ መጻሕፍት
የቴሌግራም ቻናል አርማ betemetsihaf — ቤተ መጻሕፍት
የሰርጥ አድራሻ: @betemetsihaf
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.49K
የሰርጥ መግለጫ

"መጻሕፍት፡ ለሰው ልጅ መድኀኒት የታዘዘባቸው የማዘዣ ወረቀት መኾናቸዉን ተገንዝባችኊ አንቡቧቸው።"
('ርጢን' ገጽ ፲፫)፧፧፧፧
የ'ቤተ መጻሕፍቱ' ሊንክ
https://t.me/betemetsihaf
ለማንኛውም አስተያየት https://t.me/getnetfekadu

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 10:02:39 ከክፉ ሰዎች እና ከሰይጣን ወጥመድ የምናመልጥበት መፍትሔ [መንገድ]፦

ጸሎት
ትሕትና
ንስሓ ናቸው።
371 viewsጌትነት ፈቃዱ, 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:05:05 " የምትማርበትን እንጂ፣ የምትማረርበትን ቀን አታብዛ!"


. ችግርህን መማሪያ እንጂ ማማረሪያ አታድርገው፤ ጥሩ ለማግኘት ጥሩ ከማሰብ ጀምር፤ መልካም አሳቢ፣ ጥሩ ሰብሳቢ ይሆናል።

. ጥሩዎችን ስላጣህ፣ ለጥሩነት አትጨክን፤ ትንሽ አስቦ ትልቅ ሰብስቦ አይኖርም፤ ለትልቅነት ያልህን ዕድል፣ በትንሽ አስተሳሰብ አታጫጨው።

. ውጤት አልባነት የተግባረ ቢስነት ሽልማት ነው፤ ከገባህበት የሕይወት አጠብቂኝ መውጪያ መንገድ እንደሌለ ቢሰማህ እንኳን፣ 'ጭንቀትን' ዕጣ ፈንታህ አድርገህ አትውሰድ።

. የማይነጋ ሌሊት እንደሌለ ካመንክ፣ የማይቀር ችግር እንዳለ ማሰብ አቁም።

. ለጊዜ ጊዜ ከሰጠኸው፣ በምሽቶችህ ላይ ብርሃን ይነግስባችኋል፤ ጭልመትህንም ማፍኪያ ማፍኪያ ንጋት ያወጣልሃል።

. በወጉ አስብ፤ ነገር ግን አብዝተህ አትብሰልስል፤ ...


[ ሐዋዝ ፤ በከፈለኝ ዘለለው፤ ገጽ 1፤ 2014 ዓ.ም.]
380 viewsጌትነት ፈቃዱ, 04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 22:00:22 ዲያብሎስ በእኛ ላይ ሲኾኑ ማየት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ዋናው እና የመጨረሻው፦
በእግዚአብሔር
መግቦት፣ ጥበቃ እና ማዳን ተስፋ ስንቆርጥ ነው።


ከሚመጡብን ፈተናዎች የበለጠ፣ ለገጠመን ጒዳይ በምንሰጠው ትርጒም የበለጠ ይዋጋናል።


"ፈተናዎች"፦
. እኛን የተሻሉ አድርጎ ለመቅረፅ፣
. ከድካማችን ለማበርታት፣
. ቆርጠን ልንጥለው የሚገባንን ለማሳየት፣
ወይም
. በጸጋው ለማደግ እንድንችል ሊኾን ይችላል፤
. ...


ጠላት ፦
የመጣብንን ፈተና፣ አዛብቶ እኛን ለማጥፋት አስመስሎ ያሳየናል።


[ ተስፋ መቁረጥ የክህደት መግቢያ በር ነው ]


ደዌም ኾነ የተለያየ ዐይነት መከራሥጋ ሲከበን፦
ታግሰን ድል ከማድረግ
እና
አጋጣሚውን ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር ከመጠቀም
ይልቅ፣
የበለጠ ከርሱ የሚያርቀንን መንገድ ባንከተል


https://t.me/betemetsihaf
https://t.me/getnetfekadu
666 viewsጌትነት ፈቃዱ, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:48:28 የአባቶቻችን የሐዋርያት ትእዛዝ ነው፤
. ሰው በልቦናው ቂም እና በቀለን
. ቅንዓትን እና ጠብን
በባልንጀራው ላይ፥
በማንም ላይ ቢኾን አይያዝ።

[መጽሐፈ ቅዳሴ (ሥርዐተ ቅዳሴ)]
457 viewsጌትነት ፈቃዱ, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 21:07:14 "ቅዱስ ኤፍሬም ኤዴሳ እንደ ገባ ራሱን ሰውሮ፣
ከጎዳና ጠራጊዎች ጋር፣ ጎዳና እየጠረገ፣ ከተማዋን እያጸዳ ችግረኛ መስሎ መኖር ጀመረ፤

. በዚህ ሕይወቱ ሲኖር፣ ሲስቅም ሆነ ሲናደድ ያየው ሰው የለም፤

ፍጹም ራሱን የሚገዛ ሰው ስለ ነበረ፣ [ሕይወቱ] በትዕግሥት የተሞላ ነበር፤

. በውበቱ የሚማረኩ እና በአኗኗሩ የሚደነቁ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡

. ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ሴተኛ አዳሪ በቅዱስ ኤፍሬም ውበት ተማረከች፤ ቅዱሱን ማሳሳት እንደማይኾንላት ብታውቅም፣ ሲናደድ ለማየት ብላ ሲወጣ እና ሲገባ ታጠምደው ጀመር፤

. አንድ ቀንም አብሯት እንዲተኛ ጠየቀችው፤ ቅዱሱም “እሺ፤ ነገር ግን እዚህ ሊሆን አይችልም፤ ሌላ ቦታ እንሒድ” ብሎ ይዟት ሔደ፤

. ሕዝብ የተሰበሰበበት አደባባይ ዘንድ ሲደርሱም “በይ እንግዲህ አሁን የፈለግሽውን እንፈጽም አላት፤ ሴትዮዋም “በሕዝብ ፊት እንዴት እንደዚህ ዓይነት ነገር እንፈጽማለን?፤ ይኽንስ ነውር አይደለምን?፤ በሰው ፊትስ ኃፍረት መፈጸም እንዴት ይሆናል? ” አለቸው፡፡

. ቅዱስ ኤፍሬምም “በሰው ፊት ማድረግን ያፈርሽ፣ እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ማድረግን አታፍሪም!!፤ ሰውስ በገሃድ ያለዉን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን የተወረዉን ሁሉ ይመለከታ ” አላት።

. ሴትዮዋም በዚህ ተጸጸታ ንስሓ ገባች፤ የዝሙት ሥራዎንም ትታ መንኵሳ ገደም ገባች፡፡


[ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ፤ ቅጽ ፩/1፤ ትርጕም እና ሐተታ በዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው፤ ገጽ ፳፫/23፤ ፳፻፲፪/2012 ዓ.ም.]
585 viewsጌትነት ፈቃዱ, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 17:22:11 ...
ከቤት ወደ ሥራ እና
ከሥራ ወደ ቤት ስትጓዝ
[ወይም በሌሎች ጉዞዎች ላይ]
አእምሮህ ምን ያስባል?

. አእምሮህ ሥራ ካልሰጠኸው፣ መንገድ ላይ ስለምታያቸው ነገሮች ያስባል፤

. ሆቴል ሲያይ ስለ ሆቴል፤
ክሊኒክ ሲያስ ስለ ክሊኒክ፤
ትምህርት ቤት ሲያይ ስለ ትምህርት ቤት፤
ሕጻናትን ሲያይ ስለ ሕጻናት፤
ትራፊክ ፖሊስ ሲያይ ስለ ትራፊክ ፖሊስ፤
...
አእምሮህ ስላየቸው ብዙ ነገሮች ጥቂትም ብትኾን ያስባል፤

. ከቤት እስከ ሥራ ቦታ በትንሹ 40 ደቂቃ ቢወስድ40ው ደቂቃ በከንቱ ይባክናል፤
ስትመለስም እንዲኹ፤ በቀን አንድ ሰዓት ከሃያ ደቂቃ በላይ በከንቱ ታሳልፋለህ፤

. አእምሮህ በማይጠቅሙ እና ትኩረት ልታደርግባቸው በማይገቡ ጉዳዮች እንዲባክን አትፍቀድ

. መጽሐፍ ብታነብ፤ ጠቃሚ ቪድዮዎች እና ኦዲዮዎችን እያየህ እና እያዳመጥክ ብትጓዝ ብዙ ታተርፋለህ


[ "ክፈተው" በመስፍን ብርሃኑ ገጽ 16፤ 2013 ዓ.ም.]
708 viewsጌትነት ፈቃዱ, edited  14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 08:04:33
አምስቱ አዕማደ ምስጢር

በምኑን በኀበ ሰብእ

ገጽ ብዛት፦ ፪፻፳/220

፳፻፲፬/2014 ዓ.ም.
639 viewsጌትነት ፈቃዱ, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 08:02:59
ጽዋዔ
የማኅበረ ፖለቲካዊ ቀውስ ምንጭ፣ ተገብሮት፣ ክትያ እና ምላሽ
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በዲይቆን ታደሰ ወርቁ

ገጽ ብዛት ፬፻፲፭/415

፳፻፲፬/2014 ዓ.ም.
543 viewsጌትነት ፈቃዱ, 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 06:23:23 "ራስኽን በሐሰት አትውቀስ፤
ራስን መክሰሱ ትሕትና አይደለም፤
ታላቁ ትሕትና ሰዎቹ ሲወቅሱኽ መታገስ ነው
"
(ቅዱስ ሰራፕዮን)

"የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትሥራው፤
ከሠራኸው እንደምትጠፋበት ዕወቅ
"
(መጽሐፈ ምክር)
803 viewsጌትነት ፈቃዱ, 03:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 21:41:58
578 viewsጌትነት ፈቃዱ, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ