Get Mystery Box with random crypto!

ይጠንቀቁ urgent በቅርቡ በድርጅታችን በበሬዳ አረቢያን መጅሊስ ላይ ከተፈፀመ የማጭበርበር ወ | Bereda Arebiyan mejliss በሬዳ አረቢያን መጅሊስ

ይጠንቀቁ urgent

በቅርቡ በድርጅታችን በበሬዳ አረቢያን መጅሊስ ላይ ከተፈፀመ የማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ ለሌሎችም ትምህርት እና ጥንቃቄ ይሆናል ከሚል ሃሳብ የመነጨ ፅሁፌን ላጋራችሁ

በ online shopping ላዬ ተሰማርታችሁ ንግድ ለምትሰሩ ነጋዴዎች በሙሉ!!!

በከተማችን በአዲስ አበባ እና ሌሎች አከባቢዎች ላይ የተለያዩ ሀሰተኛ ደረሰኝ በማዘጋጀት እና ሀሰተኛ ቴክስት በመላክ ነጋዴዎችን የሚያጭበረብሩ የተደራጁ ወንጀለኞች ከሰሞኑ ተበራክተዋል።
የተለያዩ ባንኮችን ደረሰኞች አስመስለው በመስራት እና ፎቶ በማንሳት ለነጋዴዎች ብሩን ገቢ እንዳደረጉ በማሳየት እንዲሁም በስልካቸው ሀሰተኛ ከባንኩ የተላከ ሜሴጅ በማስመሰል በመላክ እቃውን ተረክበው የሚሰወሩበትን ማጭበርበሪያ ተጠቅመው በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም መንግስት አካላት፣የባንክ አገልግሎት ሰጪዎች፣እንዲሁም ኢትዮቴሌኮም በጋራ እንደነዚህ አይነት አጭበርባሪዎችን ለህግ በማቅረብ ከዚህ የማጭበርበር ስራ ነጋዴውን እና ማህበረሰቡን እንዲያድኑ ለመጠየቅ እንወዳለን!
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦንላይን ግብይት ሲገበያዩ በመጀመሪያ
➠ የደረሰኙን ትክክለኛነት
➠ ከባንክ የሚላከውን ቴክስት ምንጭ መመልከት
➠ እንዲሁም ከስምምነት በኋላ ቢቻል የክፍያ አፈፃፀሙ በአካል(face to face) የሚሆንበትን መንገድ መፈለግ ራስን ከአጭበርባሪዎች ለመከላከል የመጀመሪያ እርምጃ ነው።

ይህን ፖስትም ሼር በማድረግ ሌሎች ተመልክተው ጥንቃቄ እና ትምህርት እንዲወስዱ የበኩሎዎን እንዲወጡ እንጠይቃለን አንዱ ቤት ያንኳኳ ወደሌላውም መምጣቱ አይቀርምና በእንጭጩ ማስቀረት እንዲቻል ላልሰሙ ሼር በማድረግ ድምፅ ይሁኑ!!!!