Get Mystery Box with random crypto!

#የበገና_ታሪካዊ_አጀማመር በገና በትክክል መቼና እንዴት ተጀመረ የሚለው ጥያቄ መልሱ ከባድ ቢሆ | የበገና መዝሙራት

#የበገና_ታሪካዊ_አጀማመር

በገና በትክክል መቼና እንዴት ተጀመረ የሚለው ጥያቄ መልሱ ከባድ ቢሆንም የጥበባት ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገልጾ የምናገኘው የምስጋና ወይም የዜማ መሣሪያ በገና መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡

በገናን ለመጀመሪያ ጊዜ የደረደሩት የላሜህ ልጅ የዩባል /ኢዮቤል/ ልጆች ነበሩ። (ዘፍ.፬፡፲፱-፳፬)

መምህር ሙሴ ኃይሉ የአንድምታ ትርጓሜ
ምጮችን በማከል ይህን ታሪክ ስለ በገና ይበልጥ ሊያስረዳን በሚችል መልኩ እንደሚከተለው አብራርተውታል።

•••
"በገና ለመጀመሪያ ጊዜ የደረደሩት የላሜህ ልጅ ዮባል/ኢዩቤል/ ልጆች ነበሩ። ይኸውም አይነ ስውር የነበረ ላሜህ አያታቸው በበረሃ እየሄደ እያለ ቃኤል ተቅበዝባዥ ነበረና ለብቻው በዱር ተሰውሮ ሲንኮሻኮሽ ሰምቶ መንገድ ይመራው ለነበረው ለረድዕ(መንገድ መሪ)”እጄ ይሞቅብኛል፣ቅጠሎች ሲንኮሻኮሹ እሰማለሁ፣ አራዊት መጥቶብናል መሰለኝ እና ድንጋይ አቀብለኝ።” ካለው በኋላ ድንጋዩን ተቀብሎ በሰማው አቅጣጫ ቢወረውር ቃኤልን ግባሩን መትቶ ገደለው። ቀርበውም ሲመለከቱ ቃየል ሆኖ ሲያገኘው መሪር የሆነን ለቅሶ አለቀሰ።ከዚህ በኋላ ሁለቱ የላሜህ ሚስቶች፤ ላሜህ ይህን ጸጸቱን በነገራቸው መሰረት ለልጆቻቸው ነግረዋል። ይህ ሁኔታ በተዋረድ እየተነገረ መጥቶ የላሜህ የልጅ ልጆች(የዮባል ልጆች) ይህ ታሪክ እነርሱ ጋር ሲደርስ ከአቤል ጀምሮ በአባቶቻቸው ላይ የሆነውን ከባድ የመገዳደል ታሪክ በማሰብ እና በማዘናቸው “ከደረቁ ቁሳቁሶች በገናን አበጅተው በመስራት እያንጎራጎሩ (በማኅዘኒ) ሃዘናቸውን ገልጸዋል።" በዚህ መሰረት በገና ከአዳም ዘጠነኛ(፱) ትውልድ ላይ መደርደር ጀምሯል።የትውልድ ሰንሰለቱም እንዲህ ነው

አዳም ፡- ቃኤልን ይወልዳል
ቃኤል፡- ሄኖሕን ይወልዳል
ሄኖሕ፡- ጋይዳድን ይወልዳል
ጋይዳድ፡- ሜኤልን ይወልዳል
ሜኤል፡- ማቱሣኤልን ይወልዳል
ማቱሣኤል፡- ላሜሕን ይወልዳል
ላሜሕ፡- ዮባልን ይወልዳል
ዮባል፦ በገና ለሚደረድሩ አባት ነበር።(ስማቸው በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አልተገለጸም።)

በመሆኑም ከአዳም ዘጠነኛ ትውልድ የሆኑ የላሜሕ የልጅ ልጆች በሆኑት በእነዚህ አበው ምክንያት በገናን ተዘጋጅቶ መደርደር ተጀመረ፡፡

@begena1221