Get Mystery Box with random crypto!

የሐምሌ ወር ተገባዶ ነሐሴ ሲገባ ከዛሬ ሁለት አሥርት ዓመታት በፊት እኔና የሠፈር ጓደኞቼ በጉጉት | Bored Cellphone

የሐምሌ ወር ተገባዶ ነሐሴ ሲገባ ከዛሬ ሁለት አሥርት ዓመታት በፊት እኔና የሠፈር ጓደኞቼ በጉጉት የምንጠብቀው የቡሄ በዓል ሁሌም ትዝ ይለኛል።
ምንም እንኳን በዓሉን ለማክበር የእናቴ ተግሳጽ እና የፍልስለታ ፆም እንቅፋት ቢሆኑብኝም ያገኘኋትን ቀዳዳ በመጠቀም ባልተጻፈውና መንግሥት በማያውቀው የቀን መቁጠሪያችን የፀደቀውን የአምስት ቀናት የቡሄ በዓል ለማክበር የፒያሳን ሱቆች እናካልል ነበር፡፡
በዓሉ ለመድረስ 15 ወይም ከዚያ በላይ ቀናት ሲቀሩት እኔም ሆንኩ የዕድሜ እኩዮቼ ዜማችንን ለማድመቅ የምንጠቀምበትን «ኪሽኪሽ» ለመሥራት
«በደቦ» ቆርኪ ለመልቀም በየመጠጥ ቤቱና በየቆሼው ስንርመጠመጥ እንከርማለን። መቼም አንባቢው እንደሚረዳው የቆሼው ትሩፋት ለጉንፋንና ለአልጋ የሚዳርገው ብዙዎቻችንን ነበር።
ቆርኪ ለቀማው ከተከናወነ በኋላ አቅማችን የፈቀደልንን ጉልበት በመጠቀም ቆርኪዋ (
እግረመንገዳችንን ጣታችንን) ቀጥቅጠን «ኪሽኪሽ»
እናዘጋጃለን።
የፒያሳ ሆያ ሆዬ ከሌሎች አካባቢዎች ለየት የሚያደርጉት በርካታ ባህርያት ቢኖሩትም ትዝ የሚሉኝን ልጠቃቅስ።
በዓሉ ሊደርስ አንድ አምስት ቀናት ሲቀሩት ጭፈራችንን እንጀምራለን። የጭፈራችን ዋና ዓላማ ግን «ሽቀላ» ነው። በየሱቁ እየዞሩ ሳንቲም መልቀም ሰሞነኛ ሥራችን ይሆናል።
ለጭፈራው የምንመርጣቸው ቦታዎች ወርቅ ቤቶችን ሲሆን፤ መኪና ውስጥ የተቀመጡ ግለሰቦችንና በአካባቢ ለመገበያየት የመጡ የውጭ ሀገር ዜጐች ላይ እናተኩራለን፡፡ በአብዛኛው ግን ይህ ዕቅዳችን የሚሳካው በአካባቢ የፀጥታ አስከባሪዎች ወይም ደግሞ የሠፈሩ «ጉልቤዎች» ከሌሉ ነው።

https://www.facebook.com/2007797192851865/posts/pfbid036NFFJKS3H2ZLEpmysnXApJiKBA8Ldg7S9eJtp3YwLAs7SiUSHAH4Kjsc7n3DQJE8l/