Get Mystery Box with random crypto!

BULBULA NEWS⏰

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbn_info — BULBULA NEWS⏰ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbn_info — BULBULA NEWS⏰
የሰርጥ አድራሻ: @bbn_info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 897
የሰርጥ መግለጫ

#Info Makes Chanege
#አንድ_ላይ_ኾነን_ለውጥ_እንፈጥራለን!
ማንኛውንም ቡልቡላ ነክ ወሬ፥ መረጃ እና ሐሳብ @Bulbula_bot ላይ ልታደርሱን አልያም #ልትጠይቁን ትችላላችሁ።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-08 07:33:18 ጠቃሚ ምክሮች !

1."የሰው ልጅ ታላቅነት የሚገለፀው በሚያገኘው ነገር ሳይሆን ለማግኘት በሚያሳየው ፅናት ነው።" -ካህሊል ጂብራን

2.የጅረቶች ብዛትና የዝናብ መዓት የውቅያኖስ ጣዕም እንደማይበርዙት ሁሉ የመከራ ውርጅብኝም የቆራጥ ሰው ህሊናን በድን አያደርገውም እንዲህ ያለ ሰው የህያውነት ሚዛኑን ይጠብቃልና። - ሴኒካ

3.የደስታ ምንጭ የምትሞላውና ሳታቋርጥ የምትፈሰው ከውስጣችን በሚፈልቁ ብሩህ አስተሳሰቦችና ስሜቶች ነው። -ዊሊያም ላዩምፊሊፕስ

4." እራስን ሁን፣ የሚሰማህንም ተናገር፣ ምክንያቱም እራስህን በመሆንህ ቅር ለሚላቸዉ ሰዎች ቦታ/ደንታ መሰጠት የለብህም፤ የሚበጁህ ስዎች ደግሞ እራስህን በመሆንህ ቅር አይሰኙምና"- ዶ/ር ሱስ

5.እንቅፋቶች እንደ ቢላዋ ናቸው፡፡ በስለቱ ከያዝናቸው ይቆርጡናል፡፡ በእጀታቸው ከያዝናቸው ደግሞ ይጠቅሙናል። - ጂምስ ራስል ሐዌል

6. እስካመንክበት ድረስ አንድ ትልቅ እርምጃ ለመውሰድ አትፍራ። አንድ ሸለቆ ለመዝለል ሁለት አነስተኛ እርምጃዎችን ለመጠቀም አትችልምና። - ዴቪድ ሎይድ ጆርጅ

7.በመጣላት የምንፈልገውን ያህል አናገኝም። አውቀን በመተው ግን ያልጠበቅነውን ያህል እናገኛለን፡፡ ስለዚህ ከሰዎች ጋር ተስማምተህ ለመኖር መሳሳትህን ካወቅህ ሳታወላውልና ቅር ሳትሰኝ ስህተትህን አርም። - ዴል ካርኒኔ

8. ቅንዓት ሲመገብ ያደገ ፍቅር አሟሟቱ ከባድ ነው። - ላቭስ ኩዩር

9.የራስህ ቤተ መንግሥት ሁን አለበለዚያ ዓለም እስር ቤት ትሆንብሀለች። - ጆን ዶ.

10.መታጠፊያ መንገድ ሲያገኝ የሚታጠፍ ፍቅር ፍቅር አይደለም። - ሼክስፒር

11.መናጢ ደሀና የናጠጠ ቱጃር ምክንያት የሚሰሙበት ትዕግሥት የላቸውም። - በፈረዲን

12.የህይወት ትግሎችና ሩጫዎች ደስታዬን እንዳይነጥቀኝ በእጅጉ እጠነቀቃለሁ። - ኤልሲን

13.ዕውቀትህን እንደኪስ ሰዓትህ ሲያስፈልግህ አውጥተህ ተጠቀምበት እንጂ በማያስፈልግህ ጊዜ ሁሉ ለታይታ አታውለው። - ፊሊፕ ዳርመር ስታንሆፕ

14.ሌሎችን የሚያሸብር ሁሉ እርሱ ራሱ በማያቋርጥ ፍርሃት የተዋጠ ነው።- ክላውሲያ

15. ወገንን ረስቶ ለግል ጥቅም ብቻ መጣር /መስገብገብ በተፈጥሮ ህግ ላይ የሌብነት ተግባር መፈጸም ነው። - ጅካሳ ፔሬቤሪስት

16.ለወንድ ልጅ ከመንግሥት ይልቅ ሚስት የበለጠ ጉልበተኛ ናት። - ራልፍ ኢመርሰን

17.ነጻ ሰዎች ነጻ ሆነው ነው የሚኖሩት በቀላሉ የሚገዛቸው ገንዘብና ሀይል ስለሌ ነው። - ሼክስፒር

18. የወደፊቱን የእርካታ ጊዜ የምታገኝበት የተሻለ መንገድ ያለህበትን ዕለት በሳቅና በፈገግታ ስታሳልፈው ነው። - ቻርለስ ደብሊው

19.የሰው ልጅ ዲሞክራሲን አይጠግብም መጀመሪያ በትንሽ ሳህን ቀጥሉ በጆንያ ይፈልጋል። -ኢድ አሚን ዳዳ

20. እያንዳንዱ ሰው ልክ እንደጨረቃ ነው፡፡ ለማንም የማያሳየው ግማሽ ጎን አለው - ማርክ ትዌይን


#መልካም_ቀን

@BBN_info
110 views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 22:52:16 መራር ቀልዶች…

መንግሥቱ ሀይለማርያም ፣አንድ አዳራሽ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ እንዳለ ጋዜጣዊ መግለጫው የሚሰማበት አዳራሽ ውስጥ አንድ ሰው #አስነጠሰ፡፡

መንግሥቱ ሀይለማርያም ማስታወሻ ማንበቡን ትቶ፤ ቀና አለና ፡- ‹‹አሁን ያስነጠሰው ማን ነው?›› ሲል ጠየቀ፡፡ ማንም መልስ አልሰጠም፡ ፀጥ ፀጥ ሆነ፡፡

‹‹ማነው ያስነጠሰው ተናገሩ?››

አሁንም መልስ የለም፡፡ መንግሥቱ ሀይለማርያም ወደ ግል ጠባቂዎቹ ዞሮ፤‹‹ከአዳራሹ የመጨረሻ ረድፍ የተቀመጡትን ሰዎች አስወጡና ረሽኑልኝ!›› አለ፡፡

#ጠባቂዎቹ_የታዘዙትን_ፈፀሙ፡፡

መንግሥቱ ሀይለማርያም፤ ‹‹አሁንስ አታወጡም?” አለ

ሰው ፀጥ አለ፡፡ መንግስቱ ወደ ጠባቂዎቹ ዞሮ፤ “ከኋለኛው መስመር አንድ ረድፍ አውጥታችሁ ረሽኑ›› አለና አዘዘ፡፡

ትዕዛዙ ተፈጸመ ለሦስተኛ ጊዜ፤“አሁንስ ያስነጠሰውን ሰው አታወጡም?” ሲል ጠየቀ፡፡

ይሄኔ አንድ ሰው እጁን አውጥቶ፤
“ #እኔ_ነኝ_ያስነጠስኩት ”

መንግሥቱ ሀይለማርያም፤

“ይማርህ!”

@BBN_info
213 viewsedited  19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 15:24:13 የዲኤስ ቲቪ ገጠመኜ

ጌቱ

ባለፈው እሑድ የነበረው የአርሰናልና ማንችስተር ጨዋታ እጅግ ግሩም ነበር፡፡ ለኔ ደግሞ ለየት የሚደርገው በልጅነቴ የዱርዬዎች ማዋያ እንደሆነ እየተነገረኝ እንዳልሔድ ወደምከለከልበት " DSTV ቤት" ከረዥም ጊዜ በኋላ የምሔድ መሆኑ ነው፡፡

ልጅ እያለሁ የአርሰናል ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የድጋፌ ምክንያት ምንም አይነት ሎጂካዊ ምክንያት የለውም፡፡ በቃ ምናልባት በአጋጣሚ የአርሰናል ማልያ ተገዝቶልኝ ስለነበረ ሊሆን ይችላል፡፡ በተረፈ በአውሮፓ የእግርኳስ እንቅስቃሴ ላይ ብዙም ትኩረት አልነበረኝም፡፡

ሰሞኑን ግን የአርሰናልና ማንችስተር ደጋፊ የነበሩ ጓዶቼ በየዕለቱ ሲያደርጉት የነበረው የጋለ ክርክር ሠላም ሲነሳኝ እነዚህን ሰዎች ስሜታዊ ያደረግው መንፈስ እኔንም በጉጉት እንድሞላ አደረገኝ፡፡ ጭራሽ አንዳንዶቹ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ መድበው መወራረድ ሲጀምሩ ነገርዬው ይበልጥ መጦዝ ጀመረ፡፡

"… በአንድ ሰው ላይ የተንጠላጠለ ክለብ ይዛችሁ ታወራላችሁ እንዴ፡ ሮናልዶ ቢወጣኮ ገደል ነው የምትገቡት ዝም ብላችሁ በድሮ ዝና ታወራላችሁ" ይላል የአርሰናሉ ደጋፊ፡፡ " ዝም በል ባክህ ወሬያም ትልቅ ክለብ ሁሌም ትልቅ ነው፡ አንድ ሲዝን አቋም መውረድ ያለ ነው- እስኪ እናንተ ጋር ከጄሱስ ውጪ እስኪ አንኳ ሚጠራ ተጫዋች ንገረኝ፤ ደህና ተጫዋች የላችሁምኮ፡ እሑድ እንተያይ የለ" ይላሉ ማንቼዎቹ፡፡

“እኛ” “እናንተ” እያሉ ሲያወሩ ከክለቡ የባለቤትነት ሼር የገዙ ነው ሚመስሉት፡፡ ራሳቸውን ለዚህ ስሜት ከልብ የሰጡበት መንገድ በጣም ስቦኝ ይህን ጨዋታ ማየት አለብኝ አልኩ፡፡

ሔድኩ፡ አብዛኛው Open air/ክፍት ያልሁኑ ዲኤስ ቲቪ ቤት ስትገቡ መጀመርያ ከውጪው ነፋሻማ ኣየር በተቃራኒ ወበቅ ውስጥ የሚገኝ ሙቅ አየር ከትነፋሽ ጥርቅም፣ ከጫማና ከሌሎች ጠረኖች ጋር ተዋሕዶ እንደመጋኛ ከውስጥ ሊጠልዛችሁ ይችላል፡፡ወድያው ግን ተላምዳችሁት ለሙቀቱ የራሳችሁን ሚና ማዋጣት ትጀምራላችሁ፡፡

12፡30 አናቱ ላይ ጨዋታው ጀመረ፡ ጭብጨባው ሌላ ነው፡፡ ተመልካቾቹ ስለተጫዋቾቹ በጥልቀት የሚውቀበት መንገድ ይገርማል፡፡ ካሜራው እያንዳዱን ተጫዋች ሲያሳይ “ትችላለህ አንተ፣ ብራቮ” እያሉ ተጫዋቹ ይሰማቸው ይመስል ያበረታቱታል፡፡ በጣም ልዮ ጨዋታ ነበር፡ በዛ ላይ በዙርያዬ ያለው ድባብ ደግሞ ቃናውን ይበልጥ እጥፍ አደረገው፡፡ አንዱ ቡድን ሲሞክር ደጋፊው በሞራል የጨበጭባል፤ የባላንጣውም ብድን ኳሱ ስላልገባ ያጨበጭባል፡፡ ዞሮ ዞሮ ጭብጨባው ስለማይቀር የደራ ስሜት ይፈጠራል ኦ አምላኬ! በጣም ልዩ ስሜት ነበረው፡፡

በአርሰናል ተከላካዮች "ነቅሎ በመውጣት" ክፍተት መፍጠርና በአንዳንድ ምክንያቶች ማንችስተር 3 -1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ነጥብ ይዞ ወጣ፡፡ ሲያንቀለቅለኝ የአርሰና ደጋፊ መሆኔን ተናግሬ የማንቼ ደጋፊዎች ተረብና ፉገራ ዘነበብኝ፡፡ አርሰናል መዝናኛዬ እያሉ ጨፈሩብኝ፡ ገና መች አያችሁ፡ ትወቀጣላችሁ እያሉ ዛቱብኝ፡፡ ኦ አምላኬ እስከዛሬ ይሄን ስሜት ሳላጣጥመው ነው የኖርኩት ተመልካቾቹ በግድ የአርሰናል ውጤት የእኔ ሕይወት ላይ ተጽዕኖ እንዲኖረው ለማሳመን ገፋፉኝ፡፡

ሳልፈልግ ቤት ገብቼ ኢንተርኔት ላይ የመድፈኞቹን የስከዛሬ ጉዞ የሚያስቃኙ ዶክመንተሪዎች፣ ትንታኔዎችን ስለተጫዋቾቹ ብቃትና ቀደምት ታሪክ ስራዬ ብዬ ማጥናት ከመጀመሬም በላይ ቀጣዩን ጨዋታ እስክታደም ቸኮልኩኝ፡፡

ይህን ያራሴን ስሜት የማጋራችሁ ዝም ብዬ አይደለም፥ አንድ ጠቃሚ ነገር ስላገኘሁበት ነው፡፡ ሰዉ ጡዟል፡ ሚዲያውም እንዳለ ሽብርና ችግር ችግሩን ብቻ በማውራት ተጠምደዋል፡፡ ውዱ አእምሮኣችን የሆነ እፎይ የሚልበት አንዳች ነገር ያስፈልገዋል፡፡ ቲሽ! ስንት ሺሕ ዓመት ልትኖሩ ነው ምትጨነቁት፡፡ የምሬን ነው፡ በደንብ አስቡበት በቀጣዩ ዓመት የሆነ ትኩረት የምትሰጡትን ተከታታይ ድራማ፣ መዝናኛ ሾው ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መርጣችሁ ወደሕይወታችሁ ቀላቅሉ፡፡ እመኑኝ ታ! ተ! ር! ፉ! በ! ታ! ላ! ች! ሁ!!

መልካም አዲስ አመት!!

ስለምወዳችሁ

@BBN_info
356 viewsedited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 13:05:30
The Last Mud Festival
ቻው ቻው ትልና..


ነገ ጥሩ ዝናብ ከዘነበ ወረዳ አጠገብ በሚገኘው ሜዳ ዓመቱን የመጨረሻ የመሰናበቻ ጨዋታ በመጫወት /የጭቃ ፌስቲቫል/ ለማዘጋጀት ታስቧል።

በጨዋታው ላይ የቀድሞ ሴት ተጫዋቾቻችንን ጨምሮ ሌሎች ጊዜያቸውን ስፖርቱ ላይ እያሳለፉ የማይገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል። እዚያው በሚመሰረቱ ቲሞች በሚደረጉ ግጥሚያዎችና የማስታወሻ ፎቶ የመነሳት ፕሮግራም ይኖረናል።

ፕሮግራሙን አዝናኝ የሚያደርገው በአስቸጋሪው የጭቃው ሜዳ ውስጥ ለመጫወት የሚደረግ መሆኑና ስለመቆሸሽ ማንም የማይጨነቅ መሆኑ ነው።

ነገ ጨዋታው የሚካሔድ ከሆነ በጥዋት የጨዋታ ሰዓቱን ይፋ እናደርግላችኋለን።

ቡልቡላ፡ ሁሌም አዲስ ነገር!!
351 viewsedited  10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 10:06:19 ይህ ከወራት በፊት ሰፊ ዝግጅት ተደርጎበት ኮንዶሚኒየም መሐል ላይ በድምቀት ለማክበር እየተጠበቀ ያለው የመስቀል በዓል ፕሮግራም ማስታወቂያ ነው፨
359 viewsedited  07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 08:30:26 GOOD MORNING BULBULA

አንድ በሚስቱ በጣም የተማረረ ባል ሳይኮሎጂስት ጋር ይሄዳል

#ሳይኮሎጂስት ፡- እሺ ጌታው ለመኖር ምንድ ነው ምትሰራው
#ባል፡-ባንክ ቤት ውስጥ ማናጀር ነኝ፡

#ሳይኮሎጂስት፡-እሺ ባለቤትህስ ምንድ ነው ምትሰራው
#ባል፡- እሷ ባክህ ምንም አትሰራም የቤት እመቤት ነች፡፡

#ሳይኮሎጂስት ፡-ጠዋት ለቤተሰቡ ቁርስ ሚሰራው ማነው?
#ባል፡- ሚስቴ ነቻ ምክንያቱም ምንም ስራ የለባትም

#ሳይኮሎጂስት፡- ሚስትህ ጠዋት ከእንቅልፏ ስንት ሰአት ነው ምትነሳው
#ባል፡-ለሊት 11፡00 ሰአት አካባቢ ነው ምትነሳው ቁርስ ከመስራቷ በፊት ቤት ስለምታጸዳ ቀደም ብላ ነው ምትነሳው

#ሳይኮሎጂስት፡- ልጆችህ ትምህርት ቤት ሚሄዱት እንዴት ነው
#ባል፡- ሚስቴ ስራ ስለሌላት እሷ ነች ምትወስዳቸው

#ሳይኮሎጂስት፡- ልጆችህን ትምህርት ቤት ከወሰደደች በኋላ ምን ትሰራለች
#ባል፡- ከወሰደቻቸው በኋላ ያው ስራ ስለሌለባት መደብር ሄዳ ምሳ የሚሰራበትን ነገር ትገዛዛና ምሳ
ከሰራች በኋላ ልብስ ታጣጥብና በቃ እረፍት ታረጋለች በቃ ምንም ምትሰራው ስራ የላትም፡፡

#ሳይኮሎጂስት ፡- አንተ ማታ ከስራ ስትመለስ ምን ታረጋለህ?
#ባል ፡- እኔ ስራ ደክሜ ስለምገባ በቃ ሻወር እወስድና ረጋ ብዬ ከልጆቼ ጋር እቀመጣለሁ፡፡

#ሳይኮሎጂስት፡- የዛኔ ሚስትህ ምን ትሰራለች
#ባል ፡- ለቤተሰቡ ራት ታቀርብና እቃ ታጣጥብና ልጆቹን አስተኝታ ወደ እንቅልፍ ትሄዳለች

#ሳይኮሎጂስት፡- እሺ ከአንተና ከሚስትህ ማን በጣም ሚሰራ የመስልሃል የሚስትህ ውሎ ከጠዋት 11 ሰአት የጀመረ እስከ ማታ ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡ ታዲያ ይሄንን ነው ስራ ስለሌለባት ምትለው!!
አዎ በርግጥ የቤት እመቤት ለመሆን ትምህርት ቤት ገብቶ ሰርተፊኬት መቀበል ላያስፈልገው ይችላል ግን በሂዎታችን ውስት የነሱ አስተዋጽኦ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ስለ ሴቶቻችን
ፀጥ ስትል ብዙ ሚሊዮን የሚሆኑ ሃሳቦችን እያሰበች እያብሰለሰለች መሆኑን ይግባህ፡፡
• አፍጣ ስታይህ ለምን እንደዚ እንደምትወድህ እና ይህን ሁሉ መስዋትነትን እንደምትከፍልልህ እያሰበች ነው፡፡
• አብሬህ እቆማለው ስትልህ ማእበል እንኳ ቢመጣ አልንቀሳቀስም ማለት ነው፡፡
• አትጉዳት ወይም በተሳሳተ መንገድ አታስባት አንተ ስትራብ ተርባ ስትቸገር ተቸግራ ስትራቆት ተራቁታ ገበናህን ሸፍና ምትኖረው ሚስትህ የልጆችህ እናት ሚስትህ ናት፡፡ ስለዚህ አክብራት ውደዳት ፍቅርን ስጣት፡፡

#መልካም_ቀን!

@BBN_info
387 viewsedited  05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 21:13:49 << የቡልቡላ ራዕይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰራተኞች ፣ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ስለነበረን ተከታታይ መልካም ሁለት ዓመታት ላሳያችሁኝ ፍቅድ አንድነት እና ክብር ከልብ እያመሰገንሁ 2015ዓ.ም መልካም የትምህርት እና የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ፡፡ >>

መምህር ታገል ጋሻዬ

@BBN_info
425 views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 21:12:29 ዜና ትምህርት ቤት

የቡልቡላ ራዕይ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት የነበረው ተወዳጅ ዳይሬክተር በዝውውር ትምህርትቤቱን መልቀቁን ይፋ አድርጓል።
423 views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 18:26:47 አዲስ አመትን በበጎ ተግባር
#አብረን

ቡልቡላ ውስጥ ገና ከዛሬ 9 ዓመት በፊት አካባቢ ጀምሮ ሁለትም ሶስትም እየሆኑ በተለያዩ በዓላት ወቅት አቅም የሌላቸውና ጓዳቸው የጎደለባቸውን ሰዎች በመጎብኘት ሕመምተኞችን በመጠየቅ ሲያሳልፍ የነበረ በቡልቡላ ወጣቶች የተጀመረ አንድ ማሕበር አለ።

ይህ ማህበር በተለያዩ በአላት ላይ ሳያጓድል እንደየአባላቱ አቅም ገንዘብም ሆነ ማቴሪያል በማሰባሰብ የቡልቡላ ውስጥ እያንዳንዱ ጥጋጥግ ውስጥ ያሉ ምስኪን ቤተሰቦችን እያስታወሰ ምርቃትም እየተቀበለ ዛሬ ላይ ደርሷል።

ይህም ተንቀሳቃሽ ማህበር ለማንኛውም ሰው ክፍት ሲሆን ለአቅመደካሞች ወይንም ኑሮአቸው ከኛ በታች ለሆኑ ሰዎች የሚሆን አሮጌ አልባሳት ፡ ሳሙና ፡ፓስታ፡ ሞኮሮኒ፣ ዱቄት፣ ዘይት እንዲሁም ለልጆቻቸው ደብተር አልያም ለናንተ ለማግኘት ቀለል የሚል ነገር ከርስዎ አልያም ከጎረቤትዎ በመሰብሰብና አቅመደካሞችን በማሰብ አዲሱን ዓመት እንቀበለው በሚል መልዕክታቸውን የማሕበሩ አባላት ለመላው የቡልቡላ አባላት ያስተላልፋሉ።

በዚህ በጎ ተግባር ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በማቴሪያልም ሆነ በሌ ባላችሁ የትኛውም አቅም አልያም በአዲስ ዓመት ዋዜማ ለ ቤተሰቦች በየቤቱ እየተዞረ ለሚደረገው የመርዳትና እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት የማስተላለፍ አስደሳች ተግባር ላይ መቀላቀል ትችላላችሁ

አስተባባሪዎች
0920140708 ማንቼ ቡልቡላ የትኛውም ቦታ

0929420387 ታዴ፡ ኮንዶሚንየም

0920212693 ፍቅሩ፡ መከላከያ አከባቢ

0941977110 ስዩም ሕትመት፡ ቢጫ ፎቅ ደውላችሁ በዚህ መልካም ተግባር ላይ መሳተፍ ትችላለችሁ።

#አዲስ_ዓመት_አዲስ_ተስፋ

@BBN_info
575 viewsedited  15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 16:30:23
ማስታወቂያ

ለአውዝሊየም ካቶሊክ ትምህርት ቤት የኬጂ ተማሪ ወላጆች
435 viewsedited  13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ