Get Mystery Box with random crypto!

ለይለቱል ቀድር ========== ክፍል:-① #ሼር_አድርጉት ለይለቱ-ልቀድር ማለት ምን ማለት ነው | ♡በረካ♡ መልቲ ♡ሚድያ♡

ለይለቱል ቀድር
==========
ክፍል:-①
#ሼር_አድርጉት
ለይለቱ-ልቀድር ማለት ምን ማለት ነው?
«ለይለተል ቀድር ማለት በአጭሩ የመወሰኛይቱ ሌሊት ማለት ነው፣ ይች ለሊት ትልቅ ቀድር ወይም ደረጃ ያላት ለሊት ናት በተጨማሪም ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ናት።||

የለይለቱል-ቀድር ደረጃዎች:-
①) ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرٌِ۝
እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (1)

②) በርሷ ላይ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች በተለየና ምንዳው የበለጠ ነው።
አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፡-

لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٌٍ۝
መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (3)

③) በርሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፡-

تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٌٍ۝
በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (4)

④) ለሊቷ ዒባዳህ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-

سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرٌِ۝
እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (5)

⑤) የተባረከች ለሊት ናት።
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ ۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينٌَ۝
እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አድዱኻን (3)

⑥) በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜ እና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል፡፡
አላህም እንዲህ ብሏል፡-

فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٌٍ۝
በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አድዱኻን (4)

⑦) በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው፡፡

⑨) ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት
ነች፡፡
ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
«ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል»፡፡
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል፡፡
ኢብኑልቀይም (ረሒመሁላህ) ይችን ንግግር ተናገሩ:-
«ለይለተልቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እርሷን
ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር፡፡ #በረመዳን አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? እንዴት እዘናጋለሁ?!» አሉ።

ለይለቱልቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?
ለይለተልቀድር የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው፣ ከረመዳንም ደግሞ በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ነው፡፡ ይህንንም የሚያስረዳን ነብዩ (ሰለላሁ
ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸው ነው፡-

«ይቺን ለሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፣ ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፣ ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ "እሷ በርግጥም
የመጨረሻው አስር ላይ ናት" ተባለኝ» ማለታቸው ነው፡፡
*
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡-
«በሱ (በረመዳን) ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች፣ የርሷን ኸይር
የተነፈገ በእርግጥም "ትልቅ ነገር" ተነፍጓል»፡፡
አስ-ሶሒሕ

ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጥር ይገባል፡፡
ፁሁፍ ሲንዛዛ አልወድም እንዳላበዛባችሁ
ክፍል:-② ይቀጥላል
④) ለይለቱል ቀድርና ምልክቶቹ?
⑤) ለይለተልቀድር በአይን ትታያለች?
⑥) የዚያች ምሽት ተወዳጅ ዱዓእ ምንድነው?
ሌላም ሰው እንዲቀላቀለን ሊንኩን ሳታጠፉ ሼር አድርጉት
#join. @back_to_alllah