2023-05-11 06:11:00
ግንቦት 02/2015
የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት እና ሥራ ፕሮጀክት በባህርዳር ከተማ ለሚገኙ ሰሪ የዘርፉ ተጠቃሚዎች የንግድ ስራ ክህሎትና እቅድ ዝግጅት ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
ስልጠናው የባህርዳር ከተማ ምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍቲኔት ጽ/ቤት ከሌሎች አጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በየክፍለ ከተማው ለተለዩና 1ሺ ለሚሆኑ ሰሪ ኃይሎች በንግድ ስራ ክህሎት እና በንግድ ስራ እቅድ አተገባበር ዙሪያ የተሰጠ ሲሆን በስልጠና ማጠቃለያ መድረኩ የተሻለ ተሞክሮ ያላቸው ሰሪዎች የስኬት ጅማሮ ለተሳታፊዎቹ ቀርቧል።
ከዚህ ባለፈ የባህርዳር ከተማ ምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ጽ/ቤት በዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ዘርፍ የድጋፍ ማዕቀፍ ላይ ለመጀመሪያ ዙር ተጠቃሚዎች ውጤታማነት አመች የሆኑ ተግባራትን በማከናወን በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ስለመሆኑና ስለፕሮጀክቱ አጠቃላይ አተገባበር ዙሪያ በጽ/ቤቱ የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ባለሙያ በሆኑት በአቶ ምኒችል ጌቴ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቧል።
የንግድ ስራ ክህሎት እና የንግድ ስራ እቅድ አተገባበር ስልጠናው ተጠቃሚ የሆኑ ሰሪ ኃይሎች በበኩላቸው የምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ድጋፍ ከማግኘታቸው በፊት በከፋ የኑሮ ውጣ ውረድ ውስጥ የቆዩ መሆኑንና ሰርቶ የመለወጥ እድላቸው የተዘጋ እንደሆነ ተቀብለው በቀቢፀ ተስፋ የቆዩ መሆኑን ገልፀዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዚህ ፕሮጀክት ታቅፈው የቀጥታ ድጋፍና የልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚ ከሆኑ ጀምሮ ግን ራሳቸውን የመለወጥ ቤተሰባቸውን የመምራትና ከዚህ አልፎም ቁጠባ በመቆጠብም ሆነ በእድርና መሰል ማህበራዊ ተሳትፎዎች ጭምር በንቃት ተሳታፊ በመሆን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን በማሳደግ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በዚህ ፕሮጀክት የትግበራ ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባህርዳር ከተማ ምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት መንግስቱ እንደገለፁት የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ተጠቃሚዎች በግል ወይም በቅጥር የስራ መስኮች ተሰማርተው ገቢያቸውን እንዲያሻሽሉ እና ሀብት ንብረት በማፍራት በኑሯቸው የሚገጥሟቸውን ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በራሳቸው ሃቅም መፍታት እንዲችሉ ከማድረግ ባለፈ ለከተማ ልማት መሻሻል ያለው ፋይዳ በቀላል የሚገመት አለመሆኑን እንስተዋል።
ስለሆነም ይህ ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ህይወት መሻሻል ትልቅ ድርሻ ያለው ፕሮጀክት ለዘላቂ ልማት እንዲውል ከሰሪዎች ጀምሮ ሁሉም አጋርና ባለድርሻ አካል የጉዳዩን ሁለንተናዊ ጠቀሜታ በመረዳት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ቀጣይነት ያለው ስኬት ማስመዝገብ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.youtube.com/channel/UCNoAcvzPiExah4lyaAb6_BQ
https://t.me/Bahirdarcitycommunication
https://twitter.com/Bahirdarፐ
190 views03:11