Get Mystery Box with random crypto!

ቻርለስ ሪባኖ .... ከሲዳማ ቡና ደጃፍ .. ወደ ባህርዳር ዕቅፍ ገብቷል በዘንድሮው የው | ባህር ዳር ከነማ

ቻርለስ ሪባኖ ....

ከሲዳማ ቡና ደጃፍ .. ወደ ባህርዳር ዕቅፍ ገብቷል

በዘንድሮው የውድድር አመት ለአዲስ አበባከ ከተማ የተጫወተው ቻርለስ ሪባኖ ከሲዳማ ቡና ጋር ቢስማማም ሳይጠበቅ ለባህርዳር ከተማ ለሁለት አመት ለመጫወት ተስማማ።

የተጨዋቹ ወኪል ሳምሶን ነስሮ ከሳምንታት በፊት የተሻለ ወዳቀረበው ሲዳማ ቡና እንዲገባ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ባለፉት ጥቂት ቀናቶች ግን የተጨዋቹ ልብ ወደ ባህርዳር ከተማ በማዘንበሉ የተጨዋቹ ወኪል የባህርዳር ከተማን ዝውውር ለመጨረስ ችሏል።

ከክለቡ የውስጥ አዋቂ በተገኘ መረጃ አሰልጣኙ አብርሃም መብራቱ መሆኑና ከርሱ ጋር መስራት መፈለጉ የክለቡ አጥቂ ማውሊ የተጨዋቹ ጓደኛ መሆኑ የቻርለስ ሪባኖ ልብ ወደ ቢዲዎች መንደር ለመግባት እንዲጓጓ አድርጎታል።

በዘንድሮ የውድድር አመት በመጨረሻዎቹ ሳምንታት ፍልሚያ ከመውረድ የተረፈውን ባህር ዳር ከተማን ለማጠናከር ክለቡ ጠንካራ ዝውውር እያደረገ መሆኑ ታውቋል።