Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት ዙር ብቻ በቀረው የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና ይሳተፉ። ስቴም ፓወ | Awaqi

ሁለት ዙር ብቻ በቀረው የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና ይሳተፉ።

ስቴም ፓወር (STEMpower) ከቪዛ (Visa) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና ላለፉት ሁለት ዓመት ከሶስት ወር ሲካሄድ ቆይቷል።

በእነዚህም ጊዜያት ሰባት ዙር ስልጠናዎች ተካሂደው ወደ 2100 የስራ ፈጠራ ፍላጎት ያላቸው እና በተለያየ የስራ ዘርፍ  ሰልጣኞች የሰለጠኑ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ከ45 በላይ የሚሆኑት ስራ ፈጣሪ Startups እንዲመሰረቱ እና እንዲጠነክሩ እገዛ ተደርጎላቸዋል።

አሁን የ9ተኛ ዙር ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን፣ እርሶም ከታች የተያያዘውን ማስፈንጠርያ በመጫን ይመዝገቡ።

ስልጠናው #በነጻ የሚሰጥ ሲሆን በዚህኛው ዙር ለ 200 ሰልጣኞች ስልጠናው ይሰጣል።

መመዝገቢያ ሊንክ፡ https://forms.office.com/r/BniiDzNp64

@awaqiethiopia