Get Mystery Box with random crypto!

Asrat tv Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ asrattv12 — Asrat tv Ethiopia A
የቴሌግራም ቻናል አርማ asrattv12 — Asrat tv Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @asrattv12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የ አስራት ቲቪ ትክክለኛ የቴልግራም ቻናላችን ነው

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-08-26 21:43:01

13.9K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-16 20:03:48
19.1K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-15 18:34:58 ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፤ ቁጥር ፪ (ከአሥራት ሚድያ)

፩፤ የአሥራት ሚድያ ምን አዳዲስ ክንውኖችን ከውኗል?
• የሒሳብ ዝርዝር ዘገባ (“Financial Report”) በባለሙያዎች እንዲጠናቀር አስደርጓል።
• ተቋሙን ለማጠናከርና ለማስቀጠል ይመለከተናል ካሉ ስብስቦች ጋር ሁሉ የተለያዩ ምክክሮች አካሂዷል።
• በተደጋጋሚ በተገለጠው መሠረት የገጠመውን የፋይናንስ ችግር ተወጥቶ ተቋሙን ለማስቀጠል አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ አድርጓል፤ በማድረግም
ላይ ይገኛል።
• ለወጭ ቅነሳ ሲባል የሳተላይት ለውጥ አድርጓል፤ ሠራተኞችን ቀንሷል፤ በዚህም የዋሽንግተን ዲሲ ስቱዲዮው እንዲዘጋ ግድ ሆኗል።
• አዳዲስ የጠቅላላ ጉባዔና የቦርድ አባላትን ጨምሯል።
• በአስር ላይ የሚገኙ የአሥራት ሚድያ ባለሙያዎች እንዲፈቱ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
• ለወደፊት ተቋሙ በምን ዓይነት አደረጃጀትና የአገልግሎት አድማስ መቀጠል እንዳለበት ጥልቅ ምክክር እያደረገ ይገኛል።

፪፤ የሒሳብ ዝርዝር ዘገባው በምን ሂደት ተጠናቀረ? ውጤቱስ ለአሥራት ቤተሰቦችና ደጋፊዎች በምን መልክ ተሰራጨ? ለማኅበራትስ?
አሥራት ሚድያ የሕዝብ አንደመሆኑ መጠን፤ ለአገልግሎት አንዲውል የተሰበሰበውን ገንዘብ በአግባቡ አገልግሎት ላይ ለመዋሉ ማሳያ የተሰተካከለና ግልጽነት ያለው የሒሳብ አያያዝ አንዲኖር በማሰብ፣ ጠቅላላ ጉባኤው አስራት ሚዲያ ሀውስ በውጭ አና በውስጥ አካላት በማንኛውም ወቅት የሒሳብ ሰነድ ሲጠየቅ ዝግጁ እንዲሆን በመወሰኑ ከጠቅላላ ጉባኤው 3 ግለሰቦችንና በበጎ ፈቃደኘነት 4 የሂሳብ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ የአሥራት የሒሳብ ሪፖርትን በዝርዝር አዘጋጅቷል። ይህም ሪፖርት አሥራት ሚድያ እሁድ ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. (16 August 2020) በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ኮሚቴው ዝርዝር ሪፖርቱን አቅርቧል። ይህ የሒሳብ ሪፖርት አስራት ከጀመረበት ግዜ አንስቶ የተደረጉትን የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ያካተተ ሲሆን ማናቸውም የአማራ ማኅበራትና አደረጃጀቶች ይህንን የሒሳብ ሪፖርት ተረክበው ለማየት፣ ለመመርመር፤ ጥያቄያቸውንም በማንኛውም ወቅት ለአሥራት ሚዲያ ማቅረብ እንደሚችሉ ለመግለጽ አንወዳለን።

፫፤ የአሥራት ሚድያ ወቅታዊ የፋይናንስ ሁኔታ ምን ይመስላል? ያለውን ሁኔታ ለመለወጥስ ምን ማድረግ ይቻላል? አሥራት በነበረበት ደረጃ አገልግሎት እየሰጠ ለማስቀጠል ምን ያህል ቋሚ ገቢ ያስፈልገዋል?
አሥራት ሚድያ (ለምሳሌ ያህል) ባለፈው ጥርና የካቲት ይሰጠው የነበረውን አገልግሎት እየሰጠ እንዲቀጥል ለማድረግ በወር ከ$25,000.00 እስከ $35,000.00 ያስፈልገናል።
በአማካይ፤ $30,000.00 ብለን ብናስብ፤
3,000 ደጋፊዎች በአማካይ በወር $10.00፤
2,000 ደጋፊዎች በአማካይ በወር $15.00፤ ወይም
1,500 ደጋፊዎች በአማካይ በወር $20.00 ቢያዋጡ አሥራትን በነበረበት ማስቀጠል ይቻላል። ሕዝባችንንም በተሻለ ማገልገል ይቻላል።

፬፤ የአሥራት ሚድያን በወርኃዊ ድጋፍ የበኩሌን ለማድረግ ልጠቀምባቸው የምችልባቸው የኢንተርኔት ገጾች ምንድን ናቸው?
https://asratmediahouse.org ላይ በሚገኙት፤ በግብረ-ሠናይ ‘gofundme’፣ በ‘PayPal’ ወይም በ‘Stripe’ በኩል መደገፍ ይቻላል።

፭፤ የአሥራት ሚድያን ለአንድ ጊዜ ድጋፍ ለማድረግ ልጠቀምባቸው የምችልባቸው የኢንተርኔት ዘዴዎች ምንድን ናቸው?
1) https://asratmediahouse.org ላይ በሚገኙት፤ በ‘PayPal’ ወይም በ‘Stripe’ የአንድ ጊዜ ክፍያ መንገዶች፤
2) አዲስ በተከፈተው የ‘gofundme’ ገጽ https://www.gofundme.com/f/ussygd-amhara-satellite-radio-and-television-asrat፤
3) በአሜሪካ ለሚኖሩ ደጋፊዎች፤ በ ‘finance@asratmediahouse.org’ የኢሜይል አድራሻ በ‘Zelle Transfer’፤ ወይም
4) በ ‘Bank of America, Acct#: 138117039920; Routing#: 125000024(paper & electronic)/ or 026009593 (wire)’።

፮፤ በእስር ላይ ስለሚገኙ የአሥራት ባለሙያዎች የሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ ምን እያደረገ ይገኛል?
የአሥራት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድና ጠቅላላ ጉባዔ፤ በኢ-ሕጋዊ መንገድ በቁጥጥር ሥር የዋሉ የአሥራት ሚድያ ባለሙያዎች ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈቱ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት፣ እንዲሁም ለሚመለከታቸው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥሪውን አቅርቧል። በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚገኙ መስመሮችም ቅሬታውን እያቀረበ ይገኛል። የአሥራት ቤተሰቦች ለአማራ ሕዝብና ለተገፉ ወንድምና እህት ወገኖቹ ድምፅ ሲሆኑ ለበደል ለተጋለጡ ባለሙያዎች መፈታት ተገቢውን ግፊት፤ እና ለቤተሰባቸው የሞራል ድጋፍ እንድታደርጉላቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን።

፮፤ አዲስ የተከፈተው የጎፈንድሚ ዘመቻ ዓላማ ምንድን ነው?
አዲስ የተከፈተው የ‘gofundme’ ዘመቻ (በ ‘ https://www.gofundme.com/f/ussygd-amhara-satellite-radio-and-television-asrat’ ላይ የሚገኘው)፤ ገቢ በሀገር ቤት ላሉ ባለሙያዎች (በእስር ያሉትን ጨምሮ) ደመወዝ ክፍያና ለተለያዩ የሥራ ማስኬጃዎች የሚውል ይሆናል። እንደምናገኘው ድጋፍ፤ ለሌሎች የአሥራት አስፈላጊ ወጭዎችም የሚውል ይሆናል።

እናመሰግናለን!
53.8K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-15 18:33:57 ይህ የአሥራት ሚዲያ የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ትኩስና ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ያገኛሉ።

አሥራት የእናንተው እውነተኛ ድምፅ!

በዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/c/ASRATMEDIA?sub_confirmation=1

በፌስቡክ:
https://www.facebook.com/ASRATMEDIAHOUSE

ያገኙናል።
35.4K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-10-10 07:31:27

112.5K views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-10-03 09:50:10

97.3K views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ