Get Mystery Box with random crypto!

እየተቃለዱ ሳለ ሜሪ አጠገቧ ያለውን እቃ አቀብለኝ ትለዋለች አጠገብሽ አይደል እንዴ አንስተሽ አትወ | ኤሽ ጣፋጭ ታሪኮች

እየተቃለዱ ሳለ ሜሪ አጠገቧ ያለውን እቃ አቀብለኝ ትለዋለች አጠገብሽ አይደል እንዴ አንስተሽ አትወስጂም ሲፎካከሩ እንደቀልድ ነገሩ እየከረረ መጣ

፠ ቆይ ለኔ በብትሰጠኝ ምንህ ይቀንስብሃል

፠ አጠገብሽ አይደል እንዴ ያለው ምን ሆነሻል አንቺ ልጅ?

፠ ጭራሽ

፠ እንደዛ የሚያምር ውሎ ውለን ባለቀ ሰአት የማይሆን ነገር ውስጥ እንዳንገባ

፠ እንግባ ታድያ

፠ እሺ በቃ አታኩርፊ ነይ ብሎ ሊያባብላት ሲል

፠ አንተ እኮ ለኔ ......

፠ አቦ ኤጭ እንግዲ ለዚህ ኑሮ ነው እንዲ ስጓጓለት የነበረው

፠ ምን? እኔ እኮ ይሄን ሂወት ነው ስናፍቀው የነበረው አንተ ጭራሽ .....

እንደቀልድ የተናገረውን ነገር ከቁም ነገር ይዛ አምርራ ታለቅስ ጀመረ ናቲ ግራ ግብት አለው እንደምንም አድርጎ አባብሎ ሊያሳድራት ምከረ። ጠዋት በጊዜ ተነስታ ያለመደባትን ወደ ቤት ካልሄድኩ አለችው ናቲም ኩርፊያው እንዳለቀቃት ቢገባውም አሺ አላት እና ተያይዘው ወጡ።

፠ ታክሲ የት ነው የምይዘው ወደ መነሀሪያ

፠ እዛ ጋር ተሻግረህ ጠይቃቸው
ብላ ስትመልስለት የለሌ ተናዶ በቆመችበት ቻው እንኳ ሳይላት ጥሏት ሄደ።

እቤት ከገባ በሃላም በንዴት ገንፍሎ ሳይደውልላት አደረ።
....... " ምንም ብታደርግህ አይፈረድባትም እኮ ካአንተም ብሶ በእሷ ትጮሀለህ አታፍርም ስንት ነገርህን ችላ በኖረች" አያለ ህሊናው ሲጮህበት ግን ከሁለት ቀናት ቆይታ በሃላ እንደተለመደው ቢደውልም ከወትሮው በተለየ ተናዳ ስለነበር ስልኩን አላነሳ አለችው።

የሚቀርባት ጓደኛዋ ጋርም ቢደውልላትም እሷም አላነሳ አለችው በጣም ደነገጠ። ሳምንቱን ሙሉ ቢደውልም ሜሪ ስልኳን አላነሳ ብላው በጭንቀት ጭንቅላቱ ሊፈነዳበት ጥቂት ቀረው። ሁሉም ነገር ተበላሽቶ ሜሪን ላለማጣት በሂወቱ ሊያደርገው አይደለም ሊያስበው የማይፈልገውን ነገር ለማድረግ ተገደደ
.
.
.
ይቀጥላል