Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ የሶፍትዌር መፍትሄዎች ለምርጦች ተቋማችን በቀን 20/ 10/ 2015 አ/ም ምርጥ የሶፍትዌር | Ashewa Technologies

ምርጥ የሶፍትዌር መፍትሄዎች ለምርጦች

ተቋማችን በቀን 20/ 10/ 2015 አ/ም ምርጥ የሶፍትዌር መፍትሄዎችን ለምርጦች ብሎ በደማቅ ሁኔታ በሃርመኒ ሆቴል ስራ አስጀምሯል!
ከልማት ባንክ፣ ከኢትዮጲያ ኢንተርፕራይዝ ዴቨሎፕመንት እና ከተለያዩ ባንኮች እንዲሁም የግል ድርጅት ባለቤቶች በተገኙበት ነው መርሃ ግብሩ የተካሄደው። ተቋማችን በሚያዚያ ወር ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ አድርጎ እንደነበር ይታወቃል ።
በይፋ ስራ ያስጀመርናቸው መፍትሄዎች የሶፍትዌር የማበልጸግ ስራ፣ አሸዋ ስማርት ኢአርፒ፣ እና አሸዋ ስማርት ዌብሳይት መገንቢያ ናቸው!! እነዚህ መፍትሄዎች የተቋማትን አሰራር የሚያዘምኑ፣ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ፣ ከዘመኑ ጋር አብረው እንዲራመዱ፣ ተደራሽነታቸውን የሚያሰፉ፣ ቅልጥፍ ያለ የአሰራር ስራት እንዲገነቡ እንዲሁም ትርፋማ እንዲሆኑየሚያደርጉ ናቸው።

አሸዋ ስማርት ዌብሳይት ቢውልደር ከዶሜን ስም ምዝገባ፣ ሰርቨር ጀምሮ እስከ የራስ ዌብሳይት በደቂቃዎች መስሪያ ሲሆን ይህ ለተለያዩ ተቋማት ወይም ግለሰቦች በቀላሉ፣ በአስተማማኝ መልኩ በቅናሽ ምንም ጭንቀት የማያመጣ፣ ከነሙሉ ነጻ ስልጠና እና ድጋፍ ጋር እየሰጠን የራሳቸው ፕሮፈሽናል ዌብሳይት ባለቤት የሚያደርጋቸው ሲሆን በአሸዋ ስማርት ኢአርፒ ደግሞ ተቋማት የሰው ሃብታቸዋን፣ ፋይናንሳቸውን፣ ደንብኞቻቸዉን፣ እንዲሁም ፕሮጀክት እና ኢንቨንቶሪያቸዉን የሚቆጣጠሩበት፣ የሚያስተዳድሩበት፣ ብልሃታዊ የሆነ የዉሳኔ አሰጣጥ እንዲኖራቸው የሚያደርግ፣ ለቢዝነሶች ሁሉንም በአንድ ቦታ መፍትሄ የያዘ የሰራተኛ ፊርማ በጣት አሻራ፣ በአይን ቅድብ፣ በፊት ፣ በካርድ የሚሰራ ጋራ ኢንተግሬት ተደርጎ የሚሰራ፣ እንዲሁም ከፖስ ማሽን እና ከ ኪዋርኮድ ስካነር ጋራ በአንድነት የሚሰራ ድንቅ ቴክኖሎጂ ይዘን መቅረባችንን አብስረናል።