Get Mystery Box with random crypto!

ድጋሚ የተደረገ የመጨረሻ ጥሪ በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም ላላችሁ የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽ | Ashewa Technologies

ድጋሚ የተደረገ የመጨረሻ ጥሪ

በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም ላላችሁ የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ባለአክሲዮኖች ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከዉል እና ማስረጃ ጋር በመተባበር ለባለአክሲዮኖች ህጋዊ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ የሰጠን መሆኑ  ይታወቃል።

ሆኖም በተለያየ ምክንያት እስካሁን ማድረግ ያልቻላችሁ ባለአክሲዎኖች ቦሌ ቅርንጫፍ ውልና ማስረጃ  ብርሃኔ አደሬ አጠገብ ያለው ህንጻ  3ኛ ፎቅ መስኮት ቁጥር 13 ላይ በመገኘት በስራ ሰአት በመሄድ መፈረም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ።
“በመሆኑም ባለክሲዮኖች በእለቱ ሲመጡ ማሟላት ያለበቸው ነገሮች”

1. መታወቂያ ወይንም መንጃፈቃድ ወይንም   ፓስፓርት ከነዚህ አንዱን መያዝ ይቻላል የታደሰ እና ዋናውንና ኮፒ በማድረግ መያዝ
2. ከቢሮም ሆነ ከባንክ ሲገዙ የተዋዋሉቡትን ውል እና የከፈሉበትን ደረሰኝ
3. በውክልና የተገዛ ከሆነ የውክልና ሰነዱንና የተወካይ መታወቂያ
4. ለልጆች የተገዛ ከሆነ የልደት ሰርቲፊኬትና የወላጅ ወይንም ህጋዊ አሳዳጊ መታወቂያ
5. በድርጅት ስም የተገዛ ከሆነ የድርጅቱን ሰነዶች

ሌላው ቀሪክፍያ ያልከፈሉ መክፈል የሚችሉ በመክፈል ከላይ በተቀሰው ቦታ ላይ መፈረም እንደሚቻል እናሳውቃለን ።

ለማንኛውም አይነት ሀሳብ አስተያየት ይደውሉልን። 0976005100