Get Mystery Box with random crypto!

15 አንድ የቅርብ ጓደኛዬ ስለ ተስፋ እንዳስብ አደረገኝ። ተስፋ ምንድን ነው? ተስፋ...ያልቃል? | AD

15
አንድ የቅርብ ጓደኛዬ ስለ ተስፋ እንዳስብ አደረገኝ። ተስፋ ምንድን ነው? ተስፋ...ያልቃል?

ተስፋ ለኔ በጨለማ ውስጥ መውጫ መንገድ ለመጠቆም እንደተዘጋጀች ጭላንጭል መብራት ናት። ተስፋ ስናደርግ ያቺን ብርሃን ተከትለን የመሄድ ድፍረትና ብርታት እናገኛለን። ግን አንዳንድ ጊዜ ጨለማውን ተለማምደነው ያቺን ጭላንጭል ብርሃን ማየት ከከበደን ተስፋ አለቀ ነው ማለት ነው?

=> ብዙዎች ገንዘብ እናገኛለን ብለው ተስፋ ሲያደርጉ - ገንዘብ የተትረፈረፈን ሰዎች እንኖራለን
=> ብዙዎች በቀለም ትምህርት ጎበዝ ለመሆን ተስፋ ሲያደርጉ - የተሳካልን ሰዎች እንኖራለን
=> ብዙዎች ስኬታማ ትዳር፣ ስኬታማ ጓደኝነት ለማግኘት ተስፋ ሲያደርጉ - ጥሩ ማህበራዊ ግንኙነት ያለን ሰዎች እንኖራለን
...ወዘተ

ብዙዎች በጨለማ ውስጥ ሲኖሩ (metaphorically) እኛ ለእነሱ ጭላንጭል መብራት መሆን ያቃተን ለምንድን ነው? ብንሞክር አንችልም?
.
.
.
#thoughts #questions #hope #light #dark