Get Mystery Box with random crypto!

#በጣም_ያሳዝናል #አማኝ_የሆነ_ሁሉ_መልዕክቱን_ሼር_ያድርግ... ክራይስት ጅሰስ ኢንተርናሽናል ቸር | zowey life

#በጣም_ያሳዝናል
#አማኝ_የሆነ_ሁሉ_መልዕክቱን_ሼር_ያድርግ...
ክራይስት ጅሰስ ኢንተርናሽናል ቸርች በተለያዬ ጊዜ ነፍሳት ወደጌታ የሚጠሩበት፣ ወንጌል የሚሰበክበት፣ ብዙዎች ከአጋንንትና ከበሽታ እስራት የሚፈቱበት ታላላቅ ኪሩሴዶችን በአዲስ አበባና በተለያዮ የሀገራችን ክፍሎች ስታደርግ ቆይታለች። ዘንድሮም በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም ታላቅ ኪሩሴድ ለማድረግ ህጋዊ ፈቃድ አግኝታ ማስታወቂያወች በቴሌቪዥኖች፣ በfm ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ በማህበራዊ ድህረገፆች እየተላለፉ ታላላቅ ቢልቦርዶችም ከተሰቀሉ በኋላ ፕሮግራሙ ጥቂት ቀናት ሲቀረው የወንጌላውያን ጥላቻ ባላቸው አካላት በዕለቱ ስቴዲየሙ ላይ የወጣት ሴት ቡድኖች ልምምድ ስለሚያደርጉ ፕሮግራሙን ማድረግ አትችሉም ብለው ከልክለዋል። አስቡት ትሬኒንግ ካለ እንኳን ጠዋት መደረግ ይችል ነበር። ነገር ግን የፕሮቴስታንት ጥላቻ ባላቸው የመንግስት መዋቅር ውስጥ ባሉ ጥቂት ሰዎች ብዙ የተለፋበት ፕሮግራም ተሰርዞ በብዙ ጭቅጭቅና ትግል ገና ወደመታደስ ላይ ባለው አዲስ አበባ ስቴዲየም ተዘዋውሯል። እነዚህ ሰዎች ወንጌልን ያስቆሙ መስሏቸው ባለቀ ሰአት የወንጌል እንቅፋት ለመሆን ቢሞክሩም ወንጌላችን ግን እንደተለመደው እያሸነፈ ይቀጥላል። የፊታችን ሚያዝያ 22 ቅዳሜ ወዳጅ ጓደኞቾን ጋብዘው አዲስአበባ ስቴዲየም እንገናኝ....