Get Mystery Box with random crypto!

ይሀንን ቪዲዮ እንየው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቅርቡ ይመጣል! የእርሱ የሆኑትን ይወስዳል። ንቁ | zowey life

ይሀንን ቪዲዮ እንየው

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቅርቡ ይመጣል! የእርሱ የሆኑትን ይወስዳል። ንቁ! በእርሱ እመኑ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት ኑ የተሰጣቹን እድልም ተጠቀሙ፤ ከኃጢያት እና ሞት ካለበት የዘላለም ፍርድ አምልጡ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶላችኃል! የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለዘላለም ሕይወት፣ ፍጹም ለሆነ ደስታና ሰላም ዋስትና ነው።

ማቴዎስ 24
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴⁰ በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤
⁴¹ ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች።
⁴² ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
⁴³ ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።
⁴⁴ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።

“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”
— ሐዋርያት 4፥12

“በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
— ዮሐንስ 3፥36

◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝዎ አድርገው ካልተቀበሉ ይህንን ጸሎት ከልብዎ ይጸልዩ

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ በጌታ በኢየሱስ ስም ወደ አንተ እመጣለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ እቀበላለሁ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሞተልኝ እንደተነሳልኝም አምናለሁ። በዚህ ሰዓትም ጌታዬ አድርጌ እቀበለዋለሁ።

እግዚአብሔር አባት ሆይ ልጅህ ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ።
በጌታ በኢየሱስ ስም አሜን!

ለበለጠ መረጃ : +251 928 66 7979

Share @AgapeGLC