Get Mystery Box with random crypto!

#መጎናጸፊያ_ተቀበል_ለምታስቀጥለው አንድ ብቻውን ሳለ የጠራው እንደ ምድር አሸዋ እንደማይቆጠረው | 🔴ACE SONGS #በማስተዋል ዘምሩ

#መጎናጸፊያ_ተቀበል_ለምታስቀጥለው

አንድ ብቻውን ሳለ የጠራው
እንደ ምድር አሸዋ እንደማይቆጠረው
እንደሰማይ ከዋክብት እንደማይገመተው
ገና እባርክሃለሁ ገና አበዛሃለሁ ያለው
መንገዱ ቢከብድም በቃሉ ታማኝ ነው

አብርሃም በመታዘዝ ልጁን በመሰዋት
ይስሐቅ የተደፈኑ ጉድጓዶችን በመክፈት
ያዕቆብ ታግሎ ተቀብሎ በረከት
አሸንፎ አሻገረ የአባቶቹን እምነት

ሙሴም ተተካ ሊቆም ለነፃነት
ቀኑ ጨልሞ ሰማዩ ድም በተፋበት
አዳኝ ጠፍቶ ተስፋ በጨለመበት
ብዙ አሳለፈ መከራና ጭንቀት
እጅ ሳይሰጥ ሳይንበረከክ ቆመ ለተጠራለት

የእግዚአብሔር ባሕርይ
ሲጠራ አገልጋይ
በመጀመሪያ መጨረሻውን የሚናገር ነው
የመሀሉ ጉዞ ታግሎ በማሸነፍ ነው

የእግዚአብሔር አገልጋይ ሕይወቱ
ከእግዚአብሔር የሚያታግል ለሕዝቡ
አለው መከራ ማይታለፍ ሚመስል
ጠቦት መጠበቁ ግልገልና በግ ማሰማራት
ጥበብ ይፈልጋል ያስከፍላል መስዋዕትነት
ዘጠና ዘጠኙ ተትቶ አንዱ እንዳይጠፋ
ሁሉን በፍቅር መያዙ እይታን እያሰፋ
መከራና ችግር ማጣቱ እየጎሰመ
ስጋን በጥርስ ነክሶ ይኖራል ተስፋን እያለመለመ

ጉዞው ሲከብድ አቅም ሲታጣ
መከራው ችግሩ ከብዶ ሲያንገላታ
ረሀብ ቸነፈሩ እጅጉን ሲቀጣ
ፈተናው በዝቶ እንደ ዘይት ሲያንጣጣ
እኔ አለሁልህ አይዞህ እያለ ሚያፅናና
ከመንፈሱ የሚያፈስ ጠማማውን ሚያቃና
አለ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ልቡ ለቀና

እንዲህ እያሉ ኢየሱስን አገልግለው ያለፉ
እድሜያቸውን በሙሉ በወንጌል ያሳለፉ
የመዳንን ወንጌል የሰበኩ ለጠፉ
ለኛ ለዚህ ትውልድ የሚያስተላልፉት
አለ እንድ ነገር በደማቸው የፃፉት
አለ መጎናፀፊያ ዕጥፍ ቅባት ያለበት ከኋላቸው የጣሉት
ለእውነት ወንጌል እነሱ ለተጠሩት
እንዲህ ነው ሕይወታቸው በእግዚአብሔር የተጠሩት

ብዙ ብል ብዙው ይቀራል ስለአገልጋዩ
ያሳለፈውን ባነሳ ገና ሚያሳልፈው
ገና ይቀራል /2*
የሕይወታቸው መንገድ ከየሱስ ጋር ያሳለፉት
ለኛ ለዚህ ትውልድ የሚያስተላልፉት
መጎናጸፊያ አለ በእጥፍ የተቀባ
ትውልድ ንቃና ትኩር ብለህ ተመልከት
አንተም ለምታስቀጥለው ወንጌል ለእውነት
ራስህን አዘጋጅ በልመና በፀሎት
ራስህን አዘጋጅ በእጥፍ ለመቀባት
ራስህን አዘጋጅ አንተም ለማስቀጠል

የኤልያስ ዘመን አሁን ተፈፀመ
ኤልሳዕ ተተካ በእጥፍ መንፈስ ታተመ
መጎናጸፊያው እንዳያልፍህ በርታ ተነሳ
ምታስቀጥል ትውልድ በአባቶች እጥፍ መንፈስ
ስለዚህ ንቃ በፀሎት ልብህ ይፍሰስ ተቀበል እንደ ኤልሳዕ መጎናጸፊያ
አስቀጥል በዘመንህ በሁለት እጥፍ መንፈስ።



2ኛ ነገሥት 2:11_14
ሲሄዱም፦ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።
ኤልሳዕም አይቶ፦ አባቴ አባቴ ሆይ፥ የእስራኤል ሰረገላና ፈረሰኞች፥ ብሎ ጮኸ። ከዚያም ወዲያ አላየውም፤ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ተረተረው።
ከኤልያስም የወደቀውን መጐናጸፊያ አነሣ፥ ተመልሶም በዮርዳኖስ ዳር ቆመ።
ከኤልያስም የወደቀውን መጎናጸፊያ ወስዶ ውኃውን መታና፦ የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው? አለ፤ ውኃውንም በመታ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።

ይቀላቀሉን

Share&JOIN
@aposgroup
@aposgroup
@aposligoch

#በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር Channl

Join us