Get Mystery Box with random crypto!

³ ትለኛለች ደግሞ... ህይወት ስትገፋህ አይጭነቅ አይክፋህ ትለኛለች ደ'ሞ... ሁሉን ያሳ | ግዮን ቲዩብ

³
ትለኛለች ደግሞ...
ህይወት ስትገፋህ
አይጭነቅ አይክፋህ

ትለኛለች ደ'ሞ...
ሁሉን ያሳይሀል ፣ ችግር እንደ ወንፊት
በተገፋ ቁጥር ፣ ተንደርደር ወደፊት
ፆሙን ነው የሚያድረው ፣ ያልበረረ ጭልፊት።

ትለኛለች ደግሞ...
ሳታጣ አታገኝም ፣ ሳታገኝ አታጣም
ተስፋ ያልቆረጡበት ፣ ህይወት የለውም ጣ'ም።

ይሄም ጊዜ ያልፋል
በርታ ትለኛለች ፣ የሚያምር ሳቅ ሰጥታኝ
እንኳንና ምክሯ...
ፈገግታዋ ብቻ ፣ እንደሚያበረታኝ
ያላንዳች ልፋት
እንዴት ይሄ ጠፋት!

፦Ef ለእናታቹ ጋብዟት ይቺን ግጥም

@rasnflega