Get Mystery Box with random crypto!

መስቀል በኢትዮጵያ ✞ ተወዳጆች በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን!!! አደረ | ፩ ሃይማኖት

መስቀል በኢትዮጵያ


✞ ተወዳጆች በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን!!! አደረሳችው ✞


❖ "ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ" ገላ 6፥14 ❖

  @And_Haymanot

ኢትዮጵያ ሃገራችን የክርስቲያን ደሴት ከመባሏም በላይ የእግዚአብሔር ቸርነት ያላት የበረከት የረድኤት ሀገር ናት ይኽም የጌታ ግማደ መስቀል በ14ኛው ክፍለ ዘመን በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል

☞ አመጣጡም የኢትዮጵያ ነገሥታት የግብጽ ካሊፋዎች ሀገረ ገዥዎች በኃይል ይጋፏቸው ስለነበር የግብጽ ሀገር ገዥዎች ደግሞ የግብጽን ክርስቲያኖች (ኮፕታውያን) ያሰቃዩአቸው ነበር ስለዚህ ይህ አለመግባባት እንዲወገድና የግብጽ ክርስቲያኖች ዕረፍት እንዲያገኙ በማሠብ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ ከግብጽ የአህናስ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስንና አባ ማዕምር የሚባሉ ሉዑካን ወደ ኢትዮጵያ መጡ በዚያን ጊዜ አጼ ሠይፈ አርዕደ አርፈው የልጃቸው ልጅ አጼ ዳዊት ነግሠው ነበር እነዚህ ልዑካን በኢትዮጵያውያንና በግብጻውያን ነገስታት መካከል ያለውን ቅራኔ አስወግደው ሲመለሱ አጼ ዳዊት በነበራቸው ቀና መንፈስ አቡነ ዮሐንስ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ እሌኒ ንግስት አስቆፍራ ከአስወጣችው ከጌታ ግማደ መስቀል ክፋይ ለበረከት እንዲልኩላቸው ወርቅ፣ አልማዝ፣ ገጸ በረከት አስጭነው ወደ ኢየሩሳሌም መልዕክተኞችን ላኩ መልእክተኞቹም ኢየሩሳሌም ደርሰው ገጸ በረከቱን ለፓትርያርኩ ከሰጡ በኃላ ፓትርያርኩ፦

፩፦ የጌታን ግማደ መስቀል፣ የቀኝ በኩሉን ክፋይ
፪፦ ጌታ ላይ አይሁድ የጫኑበትን (ያረጉለት) አክሊለ ሶኩን
፫፦ ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ የእመቤታችን ስዕል ላኩላቸው።

መልዕክተኞቹም ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ አጼ ዳዊት መልእክተኞቹን ለመቀበል ሲሄዱ የተቀመጡባት ባዝራ ፈረስ ጥላቸው መሞታቸውን ታሪካቸው ይናገራል መስቀሉ ወደ ሀገራችን የገባው #መስከረም 10 ቀን ነው መስቀሉ የተቀመጠው መስከረም 21 ቀን በወሎ ክፍለ ሃገር በግሸን ማርያም ነው

በዚህ ሁኔታ የገባው የጌታ መስቀል ዛሬም ድረስ ተአምራዊ ነው ይህም ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመስቀል ያላትን ታላቅ አክብሮትና ፍቅር የገለጸችበት አብይ ምስክር ነው ሕዝቡም ለመስቀል ያለውን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽ ይነቀሰዋል፣ በልብሱ ላይ ይጠልፈዋል ይህ ደግሞ የሚያሳየው መስቀል በኢትዮጵያውያን ዘንድ ምን ያህል ክብር እንዳለው ነው።


☞ ከተለያዩ ማዕድናት የሚሰራው መስቀል ትርጉም፦

መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ሊሰራ ይችላል መስቀሉ የሚሰራባቸው ማዕድናት የራሳቸው ባህርያት እንዳላቸው ሁሉ ምሳሌውን ለመግለጽ ብቁ ናቸው ብለው አባቶች ያስቀመጡትን ማየት ይገባል።

ከብረት ቢሰራ ክርስቶስ የተቸነከረበትን ችንካር ለማመልከት ነው
ከወርቅ ቢሰራ ወርቅ ንጹህ እንደሆነ ክርስቶስን ንጹሀ ባህርይ እድፈት የሌለብህ ጽኑ አንተ ነህ ብሎ ለመመስከር ነው
ከእንጨት ቢሰራ ክርስቶስ የተሰቀለው በዕጽ በእንጨት ላይ መሆኑን ለማመልከት ነው
ከብር ቢሰራ ተስፋን፣ ዕድልን ያመለክታል ይኸውም ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ ቤዛን በደሙ ከፍሏልና በእርሱ ተስፋ እንድናደርግ ያመለክተናል


መስቀል ለእኛ ክርስቲያኖች ኃይላችን፣ ጽንዐችን፣ ቤዛችን፣ መድኃኒታችን ነው "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና" /1ኛ ቆሮ 1፥18/ ለቅዱስ መስቀል ክብርና ስግደት ይገባል ምክንያቱም በመዝ 131፥7 ላይ "እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን" ተብሎ ተጽፏልና።

❖ ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናከያቸው
❖ በዓለም ጥበብ ለሚኖሩ እውነት ተስኗቸው
❖ ለጠቢብ ሰው በመንፈስ የሚኖር
❖ የመዳን ቀን እውነተኛ አርማ ነው
❖ ከገሃነም እሳት የሚያድን ነው

ያለ መስቀል ክርስትና ያለ ተጋድሎ ቅድስና የለም!!!

✞ አምላከ ቅዱሳን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ጽላት ላይ ይጻፍልን!!! አሜን ✞✞✞

ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት  
          
   አንድ ሃይማኖት
        `ተዋህዶ´´´
   @And_Haymanot
           JOIN
   @And_Haymanot
   @And_Haymanot
     ~Share~
   @And_Haymanot
   @And_Haymanot
      ~JoIN~
   @And_Haymanot
   @And_Haymanot
         ፩  ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
      @And_Haymanot
  የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡