Get Mystery Box with random crypto!

በተለየ ሁኔታ ሳላመሰግናችሁ የማላልፍችሁ የየካምፓስ ተ/ህብረት ፕሬዝደንት ለነበራችሁ፣ የአገር አቀ | Arba Minch University Students`Union

በተለየ ሁኔታ ሳላመሰግናችሁ የማላልፍችሁ የየካምፓስ ተ/ህብረት ፕሬዝደንት ለነበራችሁ፣ የአገር አቀፍ ተ/ህብረት ስራ አስፈጻሚዎች፣ 08 ባች ጓደኞቼና የሙያ አጋሮቼ ሜዲካል ኢንተርን ሀኪሞች፣ የህክምና አስተማሪዎቼ እንዲሁም እጅግ በጣም የማከብራችሁ ዶ/ር ታምሩ ሽብሩ (የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር)ና ዶ/ር የቻለ ከበደ (የቀድሞው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት)፣ ስማችሁን የዘነጋዋችሁ አካላት በተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንትነት የሀላፊነት ጊዜዬና በትምህርት ሁኔታየ እያገዛችሁኚና እየመከራችሁ ከባዱን የሀላፊነት ጊዜ እንድወጣው ስላስቻላችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

በመጨረሻም ለአዲስ ተመራጪ የህብረቱ ፕሬዝደንት ተማሪ ደሳለው ቆለጪ የ4ኛ ዓመት የኤሌክትሪካል ምህንድስና ተማሪና አመራር ስራ አስፈጻሚዎቹ፣ ኦዲተሮች እንዲሁም ለጠቅላላ ጉባኤው መልካም የስራና የትምህርት ጊዜ እንዲሆንላችሁ ስንመኝ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች፡ አመራሮችና የጠቅላላ ማህበረሰቡ ድጋፍ እንደማይለያችሁ በመተማመን እና ተማሪዎቻችሁና ዩኒቨርስቲው የጣለባችሁን ትልቅ ሀላፊነት በአገልጋይነት መንፈስ ከትምህርታችሁ ጋር በብቃት እንደምትወጡት በማመን ነው፡፡

የተማሪዎች ህብረት የተማሪ አገልጋይ ነው፡፡
መልካም የስራ ጊዜ፡፡
እናመሰግናለን፡፡

ዶ/ር አንድነት ደስታው (ኢንተርን)
የአ/ም/ዩ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት (የቀድሞው)

@amuSUinfo
@AMUSU_bot