Get Mystery Box with random crypto!

የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ | የአስተሳሰብ ለውጥ✊

የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እነሆ "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ።

የሱና ወንድማችን አብዱ ሰይድ ይባላል። በልጅነቱ በሆነ አጋጣሚ በተፈጠረ አደጋ አንድ አይኑን አጥቶ ሲኖር የነበረና በችግርና በመከራ ውስጥም ቢሆን አግብቶ ሁለት ልጆችን ወልዷል።አላህ አግርቶሎት በቀረችው በአንድ አይኑ #ቁረአንም_ሀፍዟል እስካሁን በቆየበትም ጊዜ ለሱና ባለው ጉጉትና ፍላጎት የተነሳ ከቤተሰቦቹ ተገሎና ርቆ ምንም እገዛ እንኳን የማያደርጉለትና ዘወር ብለው የማያዩት ሲሆን ስራም ትንሽም ቢሆን የቀን ስራ እየሰራ ቤተሰቦችን ያስተዳድር ነበር ። አሁን ግን መስጊድ ቁጭ ብሎ ቁረአን ሲቀራ ነው የሚውለው ።

ሆኖም አሁን ደግሞ የአሏህ ውሳኔ ሆነና በሚኖርበት ግቢ በተፈጠረ የእሳት አደጋ ምክንያት እሳቱን ለመከላከል ጥረት በሚያደርግበት ወቅት የኤሌክትሪክ መብራት ይዞት ጭንቅላቱን ክፉኛ የተመታ ሲሆን ይህ አደጋም የቀረችው አንድኛው አይኑ ላይም ተፅእኖ በመፍጠሩ ከፍተኛ ህመም ሲፈጥርበት ዶክተሮችም በፍጥነት አድስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመሄድ ህክምና ካልወሰድክ የአይንህ ነርቭ በመነካቱ ሁለተኛውንም አይንህን ልታጣው ትችላለህ ብለውታል።

ስለዚህ ይህ የሱና ወንድማችን የቀረችውን አንድ አይኑን ለማትረፍ ህክምናውን ለመጀመር በትንሹ 70,000ሺ ብር( ሰባ ሺ ብር) እንደሚያስፈልገው በዶክተሮች ተነግሮታል ።ይሄንን ብር ደግሞ አይደለም በአንድ ጊዜ በአንድ አመትም ማገኘት ስለማይችል የኛ የወንድምና የእህቶቹ እገዛና እርዳታ ያስፈልገዋል

ያ አሏህ... ተመልኩቱ አንዷንም የተረፈችዋንም አይኑን ሊያጣት ነው ሲደመር ችግር ፣ ድህነት ፣ ልጆች ማሳደግ ፣ ስራ ማጣት ፣ ከቤተሰብ መገለል እያሰቃየው ነው።

እኛ ደግሞ ሁለቱም አይኖች አሉን። #አልሀምዱሊላህ ፣ አሏህም በቁረአኑ እንዲህ ብሎናል (أَلَمْ نَجْعَل لَّهُۥ عَيْنَيْنِ) "ለእርሱ(ለሰው ልጅ) ሁለት አይኖችን አላደረግንለትምን?"( ሱረቱል በለድ ፣ 8) ይላል። ታዲያ አሏህ እንዲህ አይነት ፀጋ ሲውልልን ምስጋናችን ከምንገልፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ እንዲህ በአይናቸው የተፈተኑ ሰዎችን በማገዝና በመርዳት አሏህ የኛንም አይኖች እንዲጠብቅልን ዱዓ በማድረግ ነው።

ውድ ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች ፣ ለዚህ ለተጨነቀ ወንድማችን ትንሽ ትልቅ ሳንል የህክምና ወጪውን በመሸፈን ካለበት ጭንቀት ወጥቶ ለቤተሰቡም ለድኑም የሚያገለግል ወንድማችን እንዲሆን የአቅማቹህን እንድታበረክቱ ስንል ለሁሉም ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች የእርዳታ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በገንዘብ መርዳት ባትችሉ share በማድረግ ተባበሩት።

ወንድማችንን ለመርዳት የተቋቋመ የባንክ አካውንት ቁጥር :- የኢትዮ ንግድ ባንክ
#1000034096008
#የአካውንቱ ስም :- አብዱ ሰይድ መሀመድ

ለበለጠ መረጃ የወንድማችን ስልክ
ስልክ: #0914324157

"በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ።

ይሄንን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ በተለያዩ ቻናሎች ግሩፖች ሸር እንዲታደርጉልን ።