Get Mystery Box with random crypto!

ሰራዊቱን ያዋረዱት ገዥዎቹ መሆናቸውን ማስረዳት ያስፈልጋል! ገዥዎቹ የሰራዊቱን ያህል የተጫወቱበት | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ሰራዊቱን ያዋረዱት ገዥዎቹ መሆናቸውን ማስረዳት ያስፈልጋል!

ገዥዎቹ የሰራዊቱን ያህል የተጫወቱበት የለም። ሌላው የፈለገ ቢበደል ሮሮው ይሰማም አይሰማም ይነገራል። ሰራዊቱን ግን ያለ ምንም ተቃውሞ አግኝተውት አዋርደውታል። ገዥዎቹን እቃወማለሁ የሚል አካል ከሌላው ባልተናነሰ የሰራዊቱን ችግርም ማሳየት አለበት። ሰራዊቱ በህዝብ ላይ እንዲተኩስ ይደረጋል። ነገር ግን ራሱን የሚያዋርዱት ገዥዎቹ እንደሆኑ በሚገባ ማሳየት ይገባል።

እነ ብርሃኑ ጁላ ናዝሬት የፖለቲካ ስራ እየሰሩ በህዝብ ማዕበል ያስመቱት ሰራዊት የተመታበት ቀን ትግራይ ውስጥ "ብሔራዊ በዓል" ሆኗል። ሰራዊቱ ከገዥዎቹ በላይ ጠላት እንደሌለው ማሳያ ነው። ገዥዎቹን የሚታገል ሰራዊቱ ከገዥዎቹ በላይ በቁስሉ የሚቀልድ፣ ክብሩን የሚያዋርድ እንደሌለ ሊያውቅ ግድ ነው።

ከዚህ ጥቃት የተረፈው ጓዶቹን አጥቷል። ቆስሏል። አካሉን አጥቷል። ይህን ውርደት በሚገባ እንዲያውቀው ማድረግ ያስፈልጋል። ገዥዎቹ በንፁሃን ላይ ሲያዘምቱት የተዋረደበት ዕለት የሌሎች የክብር ቀን ሆኖ መዋሉን ማሳየት ያስፈልጋል። ውርደቱን ክብሩ፣ ሞቱን መዳኛቸው፣ የወንድሞቹን ሞትና የእሱን ቁስል መቀለጃ እንዲሆን የተደረገው በገዥዎቹ መሆኑን ለሚገባው ማስረዳት ያስፈልጋል።