Get Mystery Box with random crypto!

“የአማራ ህዝብ የሚደርስበትን የዘር ማፅዳትና ማጥፋት እንዳመጣጣቸው በመደራጀት እንደ እስራኤላዊያን | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

“የአማራ ህዝብ የሚደርስበትን የዘር ማፅዳትና ማጥፋት እንዳመጣጣቸው በመደራጀት እንደ እስራኤላዊያን ባንድነት በመቆም መታገል ይጠበቅበታል፡፡” ባልደራስ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል
ሚያዚያ 10 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ

አማራን ለማጽዳት የሚካሄዱ እርምጃዎችን ህዝቡ እንደ አመጣጣቸው መልሶ እንደ እሰራኤላውያን ታላቅነቱን ያሳያል።

ህወሓት መራሹ ሥርዓት የጎሳ ፓለቲካን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከተከለበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ዜጎቻችን ለዘር መፅዳት እና ለዘር መጥፋት ተዳርገዋል። በተለይ ደግሞ ላለፉት አምስት ዓመታት ያለሟቋረጥ የንፁሃን አማራዎች ደም በወለጋ፣ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ፣ በምእራብ ሸዋ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሀረር፣ በሻሸመኔ፣ በአጣዬ፣ … ያለ ማንም ከልካይ እየፈሰሰ ይገኛል። ዛሬም የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ እንዲጠፋ ስልታዊ በሆነ መንገድ በኦህዲድ/ኦነግ የብልፅግና መንግሥት ሴራ እየተፈፀመበት መሆኑን ለመረዳት የፖለቲካ ልሂቅ መሆንን አይጠይቅም፤ ነገሮች ግልፅ እየሆኑ መጥተዋልና።

በወልቃይት ከሚገኙት ከአራት የአማራ ልዩ ኃይል ብርጌዶች ሦስቱ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን፣ ‹‹ልዩ ኃይሉን መልሶ ለማደራጀት ነው›› የሚባለው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እውነትነት እንደሌለው እና ህዝቡ ለፅንፈኛ ኃይሎች እየተጋለጠ እንደሆነ ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ የአማራ ልዩ ኃይልን መፍረስ እና መበተን ተከትሎ በጎንደር ፍየል-ውሀ እና በማይጠምሪ አካባቢ ህወሓት ኃይሏን እያስጠጋች መሆኗን ከሚደርሱን መረጃዎች ለማረጋገጥ ችለናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በጭልጋ አካባቢ የቅማንት ፅንፈኛ አካል ኃይሉን እያደራጀ ሲሆን፣ የአገው ሸንጎንም በኦህዲድ/ኦነግ ብልፅግና መንግሥት ድጋፍ እየተደራጀ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በአጠቃላይ የኦህዲድ ብልፅግና መራሹ ሥርዓት የጎሳ ፓለቲካ ሀ፣ሁን ካስተማረው ከህወሓት እና ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ከሌሎች የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር የአማራን ህዝብ ድምጥማጡን ለማጥፋት ቀን ከሌት እየባዘነ ይገኛል፡፡ ሚያዚያ 05/2015 ዓ.ም. ከደሴ ወደ ሸዋ ሮቢት ሲጓዙ የነበሩ ትጥቃቸውን የፈቱ የአማራ ልዩ ኃይሎች ላይ ፅንፈኛው የኦነግ-ሸኔ ታጣቂ ግፍ በተሞላበት መንገድ ያደረሰው ጭፍጨፋ በአስረጅነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በወለጋ በአንገር ጉተን ወረዳ ሚያዚያ 05/2015 ዓ.ም. ኦነግ ሸኔ ተብሎ በዳቦ ስሙ በሚጠራው የብልፅግና ኦህዲድ/ኦነግ የጫካ ክንፍ ከአራት መቶ በላይ አማራዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ ለሠላሳ ሁለት ዓመታት በዚህ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እና ማፅዳት ሲፈፀም አማራ ባይሆን ማን ይችለው ነበር? ገዥው ብአዴን ባይሆን ማን ህዝቡን እንዲህ ያስጨፈጭፈው ነበር? ግፉ በዝቷል፣ በቃ ማምረር ይገባል፡፡

በመሆኑም፦

➣የኦህዴድ ብልፅግና መራሹ ሥርዓት በአማራ ክልል ለዘመናት ተዋደውና ተከባብረው የሚኖሩትን ብሔረሰቦች የፅንፈኝነት አስተሳሰብ በማላበስ በአማራው ላይ በጠላትነት እንዲነሱ በማድረግ እና ክልሉን በማዳከም በኢትዮጵያ በአንደኛ ደረጃ የሚገኘውን የአማራ ህዝብ ቁጥር ወደ አናሳ /minority/ ቁጥር ማውረድ ተቀዳሚ ዓላማ ነው፡፡ መላው የአማራ ህዝብም ይህንን የገዥውን ፓርቲ ዓላማ ተረድቶ ትግሉን ህዝባዊ እንዲያደርግ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

➣ ህወኃት በሰሜን እዝ ላይ በፈፀመው ግፍ ለፍርድ መቅረብ ሲገባው የኦህዲድ ብልፅግና መንግሥት ግን ከተቀበረበት ጉድጓድ አውጥቶ ለሥልጣን አብቅቶታል፡፡ የህወኃት እና የኦህዲድ ብልጽና ጋብቻ የሚያመለክተው ሥርዓቱ ለመከላከያ ኃይል ደህንነት እና መስዋዕትነት ቅንጣት ያህል ስሜት እንደሌለው ነው፡፡ ስለዚህ የመከላከያ ሠራዊት በወገንህ ላይ ምንም አይነት ቃታ እንዳትስብ እናሳስባለን፡፡

➣የብልፅግና መንግሥት የፅንፈኛ ኦነጋውያንን አስተሳሰብ ስለሚያራምድና አድሎአዊ ስለሆነ የአማራን ህዝብ ለመጠበቅ የሚያስችል ቁመና የለውም፡፡ በመሆኑም የአማራ ህዝብ ለፅንፈኞች ተጋላጭ እንዳይሆን ፋኖ፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ትጥቃችሁን መፍታት እንደሌለባችሁ ደግመን እናስገነዝባለን፡፡

➣የአማራ ህዝብ ሆይ - ለሠላሳ ሁለት ዓመታት የሚወክልህ ዕውነተኛ የመንግሥት ተጠሪ ስለሌለህ ከብአዴን/ብልፅግና የሚወጡ ፕሮፓጋንዳዎችን ማዳመጥ የለብህም፡፡ እግር ከወረች አስሮ የሚያስጨፈጭፍህ ብአዴን/አማራ ብልፅግና እንደሆነ አውቀህ የአማራ ክልል ባለሥልጣናት እስካሁን ባንተ ላይ ያደረሱብህን በደልና ግፍ ቆጥረህ በህግ ተጠያቂ እንደምታደርጋቸው ልታሳውቃቸው ይገባል። በሰላማዊ መንገድ የጀመርከውን ትግል ውጤት እስከምታገኝበት ድረስ ባለማቋረጥ እንድታቀጣጥለው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

➣ሰላማዊ ዜጎችን የሚጨፈጭፍና የተረፉትንም የሚያፈናቅል፣ ንብረትን የሚያወድምና ከተሞችን የሚያነድ ኦነግ-ሸኔን አሽሞንሙኖ የያዘ ክልል፣ ሀገርን የታደጉትን ፋኖን እና ልዩ ኃይልን ሊያወግዝ የሚያስችል የሞራል ብቃት እንደሌለው በመረዳት የአማራ ትግል መዳረሻ ሥርዓቱን እና ባለስልጣናቱን ሙሉ በሙሉ መቀየር እንደሆነ በማለም ለየትኛውም ፈተና ሸብርክ እንዳትል እና ገዥዎች ለማጭበርበሪያ የሚጠቀሙበትን የሽምግልና ሥርዓት እንዳትቀበል እናሳስባለን፡፡

➢የብልፅግና መንግሥት ዕድሜውን ለማራዘም ከሚጠቀምባቸው ስልቶች መካከል አንዱ የሰሜኑን ክፍል (አማራን እና ትግሬን) ማጋጨት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ይህ እኩይ ዓላማው እንዳይሳካ ለማድረግ የሁለቱ ክልል ነዋሪዎች፣ የታችኛው የመንግሥት አመራሮች፣ ምሁራን እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቅባችሁን ሓላፊነት እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

➢በአማራ ህዝብ ላይ ለዘመናት ሲደርስበት የነበረውን እና እየደረሰበት ያለውን ግፍ ለመቋቋም የአማራ ህዝብ ለሚያደርገው ትግል መላው ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ እንጠይቃለን፡፡

➢የአማራ ህዝብ የሚደርስበትን የዘር ማፅዳትና ማጥፋት እንዳመጣጣቸው በመደራጀት እንደ እስራኤላዊያን ባንድነት በመቆም መታገል ይጠበቅበታል፡፡

➢የህወኃት ርዕዮት ዓለም ወራሽ የሆነው የብልፅግና መንግሥት - ታሪክ እና ቅርስ ጠል፣ አድሎአዊ፣ ጠባብ ብሔርተኛ፣ የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ መብቶች ረጋጭ፣ ጨፍጫፊ፣ … አምባገነን ሥርዓት መሆኑን ያሳለፍናቸው አምስት ዓመታት ምስክሮች ናቸው፡፡ እነዚህ በአመራሩ ላይ ያሉ ሀገር አፍራሽ ፋሽስታዊ ስብስቦች የትኛውንም ማኅበረሰብ ስለማይወክሉ የኦሮሞ ህዝብ አብሮህ ከኖረው እና ከሚኖረው ከአማራ ወገኖችህ ጋር በመቆም ይህን ዘረኛ ሥርዓት እንድትታገለው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ