Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛ ገነት አስማማው በፀጥታ ሃይሎች ድብደባና እንግልት ደረሰባት ትናንት መጋቢት 28/2015 | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ጋዜጠኛ ገነት አስማማው በፀጥታ ሃይሎች ድብደባና እንግልት ደረሰባት

ትናንት መጋቢት 28/2015 ዓ/ም የየኔታ ሚዲያ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ተይዛ በምትወሰድበት ወቅት ድብደባና እንግልት እንዲሁም የፀጥታ ሃይሎቹ የወከሉትን ሃገራዊ የፀጥታ ተቋሙን የማይመጥን ፀያፍ ስድብ ሲሰድቧት እንደነበር ከተገኘው የድምፅ ቅጂ ለመረዳት ተችሏል።

ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ከቢሮዋ በምትወሰድበት ወቅት በፀጥታ ሃይሎች እየተወሰደች መሆኗን ለሌ ሰው እያሳወቀች ባለችበትና ጋዜጠኛ መሆኗን እየገለፀች በነበረበት ወቅት ነው ድብደባ የተፈፀመባት።

በወቅቱም በአካባቢው ሰው ከቦ እንደነበረና የፀጥታ ሃይሎቹም እንደበተኗቸው ሮሃ ቲቪ ለማወቅ ችላለች።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በጋዜጠኞችና በመብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጽሙትን አፍኖ መሰወር፣ ሕገ ወጥ እሥር፣ ድብደባ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ ሊያቆሙ ይገባል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተከላካይ ማዕከል አቶ ያሬድ ሃይለማሪያም ናቸው።

አቶ ያሬድ " ትላንት ከሥራ ቦታዋ ታፍና እና ድብደባ እየተፈጸመባት በታጣቂዎች የተወሰደችው የየኔታ ሚዲያ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው የአያያዟን ሁኔታ የሚያስደምጠው የስልክ ንግግርና የድምጽ ቅጂ የአገዛዝ ሥርዓቱ ወደ መጥፎ አቅጣጫ እያመራ መሆኑን ከሚያሳዩ በርካታ ምልክቶች አንዱ ነው። በቅርቡ በተመሳሳይ ሁኔታ ታፍኖ የተወሰደውና ድብደባ የተፈጸመበት ጋዜጠኛ ንጉሴ እና መምህር ታዬ ላይ የተፈጸመውም ድርጊት እንዲሁ ተጨማሪ ማሳያዎች ናቸው።" ብለዋል

ገነት አስማማውን ጨምሮ በተከታታይ ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች ይፈቱ ብለዋል አቶ ያሬድ።
ሮሀ ሚዲያ